translation
translation
{ "en": "Free Zone9 Tumblr collage. Images used with permission. Join Global Voices bloggers for a worldwide, multilingual tweetathon in support of the ten bloggers and journalists facing terrorism charges in Ethiopia.", "amh": "የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ይፈቱ ከሚለው የተምብለር ዘመቻ በፍቃድ የተወሰደ በአወዛጋቢው የጸረ ሽብር አዋጁ እና ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ በመሞከር ወንጀሎች ስልጣን ላይ ባለው የኢትዮጵያ መንግስት ተጠርጥረው በእስር ላይ ለሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ድጋፍ እና አጋርነት ለማሳየት ሀምሌ 24 የትዊተር ላይ ማራቶን ተዘጋጅቷል:: ይህንንም ማራቶን በመቀላቀል ለጦማርያኑ እና ለ ጋዜጠኞቹ ያሎትን አጋርነት በተግባር ያሳዩ::" }
{ "en": "The Global Voices community and our network of allies are demanding justice for these men and women, all of whom have worked hard to expand spaces for social and political commentary in Ethiopia through blogging and journalism. We believe their arrest is a violation of their universal right to free expression, and that the charges filed against them are unjust.", "amh": "የአለም አቀፍ የጦማርያን ማህበረሰብ የሞያ አጋሮቻችን የሆኑት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች በሀገራቸው ጉዳዮች ላይ የሰለጠነ ማህበራዊ ተዋስኦ እንዲኖር ጠንክረው ከመስራት ባለፈ ምንም የሰሩት ወንጀል ስለሌለ ፍትህ እንዲያገኙ አጥበቀን እንጠይቃለን:: የአጋሮቻችን እስር በአለም አቀፍ ደረጃ ስምምነት የተደረሰባቸውን ሰበአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን የሚደፈጥጥ ከመሆኑ ባሻገር ጦማሪያኑ እና በጋዜጠኞቹ ላይ የተመሰረቱባቸው ክሶች ኢፍትሀዊ ናቸው ብለን እናምናለን:: የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች የፍርድ ሂደት እየተከታተለ የሚዘግብ ድረገጽን በመመልከት ስለ ጉዳዩ ያሎትን ግንዛቤዎት ያስፉ::" }
{ "en": "Until then, and beyond, they will need all the support they can get. So this Thursday, we as a global community of bloggers, writers, activists, and social media experts will share this message around the world, tweeting in our native languages at community leaders, government and diplomatic officials, and mainstream media to draw public attention to the case.", "amh": "ጦማሪያኑ እና ጋዜጠኞቹ ሀምሌ 28 2006 በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ:: ፍርድ ቤት እስከ መገኛቸው ቀን እና ከዚያም በኋላ ባሉት ግዚያት የሞያ አጋሮቻችን የኛን ከፍተኛ ድጋፍ ይሻሉ:: በመሆኑም ሀሙስ ሀምሌ 24 2006 በመላው አለም የምንገኝ ጦማሪያን: ጻህፍት እና የማህበራዊ ሚዲያ ባለሞያዎች ይህንን የድጋፍ መልእክት በየቋንቋችን ትዊተርን በመጠቀም ለማህበረሰብ መሪዮች: ለመንግስት ባለስልጣናት እና ለዲፕሎማሲያዊ ማህበረሰብ አባላት እናስተላልፋለን:: ይህንንም በማድረግ የተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡት እናደርጋለን::" }
{ "en": "Six of the detained bloggers in Addis Ababa.", "amh": "ይህንን የትዊተር ላይ ማራቶን ሃሙስ ለት መቀላቀል ይፈልጋሉ ?" }
{ "en": "Photo used with permission.", "amh": "ወይ ዜናውን ለወዳጅ ዘመዶዎ ማጋራት ይፈልጋሉ?" }
{ "en": "#FreeZone9Bloggers: A Tweetathon Demanding the Release of Jailed Ethiopian Bloggers", "amh": "ስሞዎትን እና የትዊተር አዳራሻዎን በማህበረሰባችን የእቅድ ገጽ ላይ ማስፈር ይችላሉ::" }
{ "en": "Date: Thursday, July 31, 2014", "amh": "የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች ፍትህ ይገባቻዋል!" }
{ "en": "Hashtag: #FreeZone9Bloggers", "amh": "ስለ ሚያገባን እንጦምራለን::" }
{ "en": "Add your name and Twitter handle to our community planning sheet.", "amh": "የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች መታሰር የአፍሪካ የሰብአዊ እና የህዝቦች መብቶች ቻርተር መጣስ ነው::" }
{ "en": "Blogger arrests in #Ethiopia violate the International Covenant on Civil and Political Rights #FreeZone9Bloggers http://bit.ly/1g1MUNM", "amh": "የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች መታሰር አለም አቀፉን የሲቪል እና የፓለቲካ መብቶች ስምምነት መጣስ ነው::" }
{ "en": "Tweet until your fingers hurt and demand justice for the Zone9 bloggers!", "amh": "ጣቶች እስኪዝሉ እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች ፍትህ እስኪያገኙ ትዊቶች ለመጻፍ አይታክቱ:: ፍትህ ለዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ጋዜጠኞች !" }
{ "en": "Zone9 members together in Addis Ababa, 2012.", "amh": "የዞን ፱ አባላት አብረው አዲስ አበባ ውስጥ ሳሉ፣ እ." }
{ "en": "Photo used with permission.", "amh": "2012 ዓ." }
{ "en": "This post was jointly published with the World Policy Journal blog.", "amh": "ፎቶ ጥቅም ላይ ለማዋል ፍቃድ ተሰጥቷል።" }
{ "en": "The international human rights system is broken – or perhaps it never worked at all.", "amh": "ይህ ልጥፍ ከWorld Policy Journal ጦማር ጋር በመተባበር የታተመ ነው።" }
{ "en": "In case after case, citizens’ human rights are violated under the national laws of their respective countries, despite the existence of international human rights commitments in the United Nations’ Universal Declaration, and by the Organization for Security and Cooperation in Europe, the Organization of American States, the African Commission, and others.", "amh": "በብዙ ጉዳዮች ላይ እንደታየው ከሆነ የዜጎች ሰብዓዊ መብቶች በየአገራቸው ብሔራዊ ህጎች ይጣሳሉ፣ ምንም እንኳ በተባበሩት መንግስታት ሁለገብ አዋጅ (United Nations’ Universal Declaration)፣ እና በአውሮፓ የደህንነት እና የትብብር ድርጅት፣ በየአሜሪካ አገራት ድርጅት፣ በአፍሪካ ኮሚሽን እና በሌሎች ውስጥ ያሉ ቃል የተገባባቸው የአለምአቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ቢያካትቱም።" }
{ "en": "The International Criminal Court has little say concerning any but the most egregious of international human rights violations, and member states have wide latitude to dispense justice as they see fit.", "amh": "የአለምአቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤቱ አይን ካወጡት በስተቀር ማንኛውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ማድረግ የሚችለው ነገር የለም፣ እና አባል አገራት ፍትህ በመሠላቸው መልኩ የመስጠት ሰፊ ነጻነት አላቸው።" }
{ "en": "For those who live in countries that fail to provide or enforce their own laws protecting freedom of expression, international principles have rarely provided actual recourse.", "amh": "ሐሳብን የመግለጽ መብትን የሚጠብቁ የገዛ ህጎቻቸውን ማክበር ወይም ማስፈጸም ባልቻሉ አገሮች ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች አለምአቀፍ መርሖዎች እውነተኛ መፍትሔ ቢሰጣቸውም ከስንት አንዴ ነው።" }
{ "en": "Today, this is the case with the independent Ethiopian blogger collective known as Zone9.", "amh": "ዛሬ ዞን ፱ ተብሎ በሚታወቀው ነጻ የኢትዮጵያውያን ጦማሪያን ቡድን ላይ እየሆነ ያለውም ይኸው ነው።" }
{ "en": "In April of this year, the government of Ethiopia arrested six members of Zone9 along with three affiliated journalists in Addis Ababa.", "amh": "ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት ስድስት የዞን ፱ አባላትን ሶስት ቅርበት ካላቸው ጋዜጠኞች ጋር በአዲስ አበባ ውስጥ አስሯል።" }
{ "en": "They were held for months without a formal charge and were denied the ability to communicate.", "amh": "ምንም ክስ ሳይመሰረትባቸው ለወራት የተያዙ ሲሆኑ ከሌሎች ጋር እንዳይገናኙም ተከልክለዋል።" }
{ "en": "Testimony from Befeqadu Hailu, one of the accused bloggers who was smuggled out of prison in August, as well as statements in court, allege mistreatment and frequent beatings.", "amh": "ሐምሌ ላይ ከእስር ቤት የወጣው የበፍቃዱ ኃይሉ ማስታወሻ እና እንዲሁም በፍርድ ቤት ውስጥ የተሰጡ ቃሎች በደል እና ተደጋጋሚ ድብደባዎች እንደደረሰባቸው ያስረዳሉ።" }
{ "en": "Informally, the nine were held on accusations of working with foreign organizations that claim to be human rights activists and…receiving finance to incite public violence through social media.”", "amh": "እነዚህ ዘጠኝ ሰዎች «የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንደሆኑ ከሚያስመስሉ የውጪ ድርጅቶች ጋር አብሮ በመስራት." }
{ "en": "In July, the Zone9 prisoners were charged under Ethiopia’s Anti-Terrorism Proclamation of 2009 for receiving support from political opposition organizations, defined formally by the government as terrorists, and receiving training from international activists in email encryption and data security from the Tactical Technology Collective, a group that helps journalists and activists protect themselves from digital surveillance.", "amh": "ሐምሌ ላይ የዞን ፱ እስረኞች መንግስት በይፋ አሸባሪዎች ብሎ ከሰየማቸው የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች ድጋፍ በመቀበል እና በአለምአቀፍ ተሟጋቾች ታክቲካል ቴክኖሎጂ ኮሌክቲቭ (Tactical Technology Collective) ከተባለው ጋዜጠኞች እና ተሟጋቾች እራሳቸውን ከዲጂታል ክትትል እንዲጠብቁ ከሚያግዛቸው ቡድን በኢሜይል ኢንክሪፕሽን እና ዳታ ሴኩሪቲ ስልጠና በመቀበል በ2001 ኢትዮጵያ ጸረ-ሽብር አዋጅ ተከስሰዋል።" }
{ "en": "The Zone9 bloggers joined other media outlets targeted under similar laws, including Eskinder Nega, who had reported on recent Arab uprisings and the possibility of similar uprisings taking place in Ethiopia.", "amh": "የዞን ፱ ጦማሪያን በቅርብ ጊዜ በነበረው የአረብ አመጾች ላይ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ሊከሰቱ በሚችሉ ተመሳሳይ አመጾች የዘገበው እስክንድር ነጋን ጨምሮ በተመሳሳይ ህጎች ከተነጣጠሩ ሌሎች የሚዲያ ድምጾች ጋር ተቀላቅለዋል።" }
{ "en": "He was arrested and charged with the planning, preparation, conspiracy, incitement and attempt” of terrorism and sentenced to 18 years in prison.", "amh": "በቁጥጥር ስር ውሎ በ«ሽብርን በማቀድ፣ ዝግጅት በማድረግ፣ በማሴር፣ በማሳመጽ እና ሙከራ በማድረግ» ተከስሶ የ18 ዓመት እስር ተፈርዶበታል።" }
{ "en": "International appeals from human rights advocacy organizations have had little effect on the case.", "amh": "የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ያደረጓቸው አለምአቀፍ ስሞታዎች በጉዳዩ ላይ ተጽዕኖ አልነበረውም።" }
{ "en": "In May, UN High Commissioner for Human Rights Navi Pillay issued a statement explaining,", "amh": "ግንቦት ላይ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ኮሚሽነር ናቪ ፒሌይ እንዲህ ብላ የሚያብራራ ቃል ሰጥታለች፣" }
{ "en": "The fight against terrorism cannot serve as an excuse to intimidate and silence journalists, bloggers, human rights activists and members of civil society organizations.", "amh": "በሽብርተኝነት ላይ የሚደረገው ዘመቻ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አባላትን ለማስፈራራት እና ድምጽ ለማጥፋት እንደ ሰበብ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም።" }
{ "en": "And working with foreign human rights organizations cannot be considered a crime.", "amh": "እና ደግሞ ከውጪ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጋር አብሮ መስራት እንደ ወንጀል ተደርጎ ሊቆጠር አይገባም።" }
{ "en": "Additionally, seven international human rights and press freedom organizations pressed the African Commission and the United Nations in an urgent appeal to intervene in the case against Zone9.", "amh": "በተጨማሪም፣ ሰባት የአለምአቀፍ ሰብዓዊ መብቶች እና የፕሬስ ነጻነት ድርጅቶች በላኩት አስቸኳይ ጥያቄ የአፍሪካ ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት በዞን ፱ ላይ በተከፈተባቸው ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቀዋል።" }
{ "en": "The appeal focused on the lack of clear charges and failure to allow the defendants adequate legal representation.", "amh": "ጥያቄው ጉድለት ባለው የክሶቹ ግልጽነት እና ተከሳሾቹ በቂ የህግ ምክር የማግኘት መብት ላይ ያተኮረ ነው።" }
{ "en": "Nani Jansen, a lawyer for the Media Legal Defence Initiative and the lead signatory in the appeal, writes in an email that both the African Commission and the UN operate under the cover of confidentiality in the early stages of these matters.", "amh": "የሚዲያ ህግ መከላከያ ተነሳሽነት (Media Legal Defence Initiative) ጠበቃ እና የጥያቄው መሪ ፈራሚ የሆነችው ናኒ ጃንሰን በኢሜይል ውስጥ ሁለቱም የአፍሪካ ኮሚሽን እና ተመድ «በእነዚህ ጉዳዮች ቀዳሚ ደረጃዎች ላይ በሚስጥራዊነት ስም ነው የሚሰሩት» ብላ ጽፋለች።" }
{ "en": "She continues:", "amh": "እንዲህ ብላ ትቀጥላለች፦" }
{ "en": "When they follow up with a Government, this is done without informing the outside world.", "amh": "ከአንድ መንግስት ጋር አንድ ጉዳይ ሲከታተሉ የውጪውን ዓለም ሳያሳውቁ ነው።" }
{ "en": "Only months and months (often over a year) later, these exchanges with a Government get published in the mechanism's report to its supervisory body.", "amh": "ብዙ ወራት (አብዛኛው ጊዜ ከዓመት በላይ) ካለፉ በኋላ ብቻ ነው ከአንድ መንግስት ጋር የተደረጉት እነዚህ ልውውጦች ለበላይ አካሉ በሚደረገው የእንቅስቃሴ ስልት ሪፖርት ላይ የሚታተመው።" }
{ "en": "Thus any intervention joins the rest of those in the cone of silence that is Zone9—hidden from public scrutiny or participation.", "amh": "ስለዚህም፣ ማንኛውም ጣልቃ መግባት ዞን ፱ በሚወክለው የድምጽ ማፈኛ ስርዓት ውስጥ ይገባል—ከሕዝባዊ እይታ ወይም ተሳትፎ ተደብቆ።" }
{ "en": "Even if these bodies do follow up with the Ethiopian government, their recourse is limited.", "amh": "እነዚያ አካላት ጉዳዩን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ቢከታተሉትም እንኳ ያላቸው አማራጭ የተገደበ ነው።" }
{ "en": "In an article on the urgent appeal, Jansen notes that the African Commission can condemn the arrests in a resolution, that both organizations' rapporteurs can request official visits to Ethiopia to investigate, and that Ethiopia, as a member of the UN Human Rights Council, would be obligated to honor such a request.", "amh": "በአስቸኳይ ጥያቄው ላይ በጻፈችው ጽሑፍ ጃንሰን የአፍሪካ ኮሚሽን እስራቶቹን በአቋም ማውገዝ እንደሚችሉ፣ የሁለቱም ድርጅቶች ሪፖርት ጸሐፊዎች ምርመራ ለማካሄድ ወደ ኢትዮጵያ ኦፊሴላዊ ጉብኝቶችን እንዲያደርጉ መጠየቅ እንደሚችሉ፣ እና ኢትዮጵያ የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል እንደመሆኗ መጠን እንደዚህ ያለ ጥያቄ የማክበር ግዴታ እንዳለባት አውስታለች።" }
{ "en": "But even should such requests be made, and investigations conducted, there is little chance of enforcement of hypothetical findings on the Ethiopian government.", "amh": "ነገር ግን እንደዚህ ያሉ ጥያቄዎች ቢቀርቡ እና መርመራዎች ቢካሄዱም እንኳ ሊገኙ ይችላሉ ተብሎ የሚገመቱት ውጤቶች በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የማስፈጸም ዕድሉ በጣም አነስተኛ ነው።" }
{ "en": "Since the appeal, the Ethiopian government has proceeded with charges against the accused.", "amh": "ጥያቄው ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት በተከሳሾቹ ላይ በክሱ እንደቀጠለበት ነው።" }
{ "en": "The latest details on the trial can be found on the Trial Tracker Blog, a site run by people close to the defendants.", "amh": "በችሎቱ ላይ ያሉ የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ለተከሳሾቹ ቅርብ በሆኑ ወዳጆች በሚሄድ የችሎት መከታተያ ጦማር (Trial Tracker Blog) ላይ ማግኘት ይቻላል።" }
{ "en": "Public attempts to highlight the Ethiopian government's transgressions against human rights such as the #Freezone9bloggers social media campaign have an indirect effect.", "amh": "እንደ የ#Freezone9bloggers የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ያሉ የኢትዮጵያ መንግስት በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚፈጽማቸው ጥሰቶችን ይፋ ለማውጣት የሚደረጉ ይፋዊ ጥረቶች ቀጥተኛ ያልሆነ ውጤት ነው ያላቸው።" }
{ "en": "They seek to shame the Ethiopian government to ensure better treatment for the prisoners.", "amh": "ለእስረኛዎቹ የተሻለ አያያዝ እንዲኖር ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ መንግስትን ለማሳፈር ያለሙ ናቸው።" }
{ "en": "They also seek to pressure international organizations and Ethiopia's allies such as the United States, for whom Ethiopia is a critical military and security partner.", "amh": "እንዲሁም በአለምአቀፍ ድርጅቶች እና እንደ ለኢትዮጵያ መንግስት ወሳኝ የጦር እና የደህንነት አጋር በሆነችው አሜሪካ ያሉ ተባባሪዎች ላይ ጫና ለማሳረፍም ያለሙ ናቸው።" }
{ "en": "The hope is that those organizations will in turn apply political pressure on Ethiopia to free the Zone9 defendants.", "amh": "ተስፋ የሚደረገው እነዚያ ድርጅቶች በተራቸው ኢትዮጵያ የዞን ፱ ተከሳሾችን ነጻ እንድታወጣ የፖለቲካ ጫና እንዲያሳርፉ ነው።" }
{ "en": "The implementation of international commitments seems to rest primarily upon a negotiated process of politics, not a functioning and enforceable system of law.", "amh": "እንግዲህ በአለምአቀፍ ደረጃ ቃል የተገባባቸውን ነገሮች መተግበር የሚወሰነው እየሰራ እና ተፈጻሚነት ባለው የህግ ስርዓት ሳይሆን በዋነኝነት በድርድር የሚካሄድ የፖለቲካ ሂደት ነው የሚመስለው።" }
{ "en": "Considering the ease with which national law in Ethiopia is employed or ignored for political ends, it is a grim irony that only political pressure can hope to resolve the case in their favor.", "amh": "ኢትዮጵያ ውስጥ ለፖለቲካዊ ዓላማ ሲባል ህጉ ምን ያህል በቀላሉ ስራ ላይ እንደሚውል ወይም ችላ እንደሚባል ሲታይ ጉዳዩ ለእነሱ እንዲፈታላቸው ያለው ተስፋ ፖለቲካዊ ጫና ብቻ መሆኑ ሲታይ ነገርየው ከባድ ምጸት ነው።" }
{ "en": "Students mourning at Haromaya University.", "amh": "የሀረማያ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ሐዘናቸውን እየገለጹ፡፡" }
{ "en": "Photo shared widely on social media.", "amh": "ፎቶው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት የተሰራጨ ነው፡፡" }
{ "en": "Over the past two weeks, students in Ethiopia’s largest regional state, Oromia, have been protesting against a government plan to expand the area of the capital, Addis Ababa, into Oromia.", "amh": "ባለፉት ሁለት ሳምንታት፣ በኢትዮጵያ ትልቁ የሆነው ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ያሉ ተማሪዎች መንግሥት ዋና ከተማዋ አዲስ አበባን ወደ ኦሮሚያ አካባቢዎች ለማስፋፋት ያወጣውን ዕቅድ እየተቃወሙ ነው፡፡" }
{ "en": "Reports suggest security forces used violence including live ammunition to disperse crowds of peaceful demonstrators in the compounds of universities in Oromia.", "amh": "ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት የፀጥታ አባላት የጥይት ተኩስ ሳይቀር ባካተተ ኃይል የተቀላቀለበት መንገድ በሠላማዊ ሁኔታ ተቃውሟቸውን ሲገልጹ የነበሩትን የኦሮሚያ ዩንቨርስቲዎች ተማሪ ሠልፈኞችን በትነዋል፡፡" }
{ "en": "According to Human Rights Watch, at least three students were killed and hundreds were injured across the region as security forces used excessive force to disperse student protesters.", "amh": "እንደ ሰብኣዊ መብቶች ታዛቢ ፖሊስ ተቃዋሚዎቹን ለመበተን በወሰደው ያልተመጣጠነ ኃይል ምክንያት፣ በክልሉ ቢያንስ ሦስት ተማሪዎች ሲገደሉ፣ ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተጎድተዋል፡፡" }
{ "en": "Other reports put the number of students killed up to ten.", "amh": "ሌሎች ሪፖርቶች ደግሞ የተገደሉትን ተማሪዎች ቁጥር ዐሥር ያደርሱታል፡፡" }
{ "en": "Although protesters are primarily university students, in some instances, high school and primary school children were also reportedly involved in intense confrontations with government forces.", "amh": "ምንም እንኳን ዋነኞቹ ተቃዋሚዎች የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ቢሆኑም፣ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችም ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ውጥረት የተሞላ ፍጥጫ ውስጥ እንደገቡ ተዘግቧል፡፡" }
{ "en": "At least nine students were killed by government forces in May 2014 while protesting over the same issue.", "amh": "በግንቦት 2006 ተነስቶ በነበረው የተመሳሳይ ጉዳይ ተቃውሞ ቢያንስ ዘጠኝ ተማሪዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል፡፡" }
{ "en": "The persecution of Oromo people", "amh": "የኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚፈፀም የመብት ጥሰት" }
{ "en": "The students argue that the controversial plan, known as the Master Plan, to expand Addis Ababa into Oromia state would result in mass evictions of farmers mostly belonging to the Oromo ethnic group.", "amh": "ተማሪዎቹ የሚሟገቱት፣ ማስተር ፕላን” በመባል የሚታወቀው እና አዲስ አበባን ወደኦሮሚያ ክልል ለመለጠጥ የወጣው ዕቅድ ውጤቱ የኦሮሞ ብሔር አባላት የሆኑ ገበሬዎችን በገፍ መፈናቀል ያስከትላል በሚል ነው፡፡" }
{ "en": "It wouldn't be the first time the government has uprooted members of an ethnic group.", "amh": "የአንድ ብሔር አባላትን መንግሥት ሲያፈናቅል ይህ የመጀመሪያው አይሆንም፡፡" }
{ "en": "Thousands of ethnic Amharas in western Ethiopia were expelled from the country's Benishangul Gumuz region in 2013 in what critics called ethnic cleansing.", "amh": "ተቺዎች የዘውግ ማጥራት” እያሉ በጠሩት ክስተት በሺሕዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ በ2005 እንዲፈናቀሉ ተገድደው ነበር፡፡" }
{ "en": "The students have other demands such as making Oromo a federal language.", "amh": "ተማሪዎቹ ኦሮምኛን የፌዴራሉ የሥራ ቋንቋ የማስደረግ ሌላም ፍላጎት አላቸው፡፡" }
{ "en": "Oromo, the language of the Oromo people, is the most widely spoken language in Ethiopia and the fourth largest African language.", "amh": "ኦሮምኛ፣ በተናጋሪዎች ብዛት በኢትዮጵያ ወደር የሌለው እና በአፍሪካም አራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የኦሮሞ ሕዝብ ቋንቋ ነው፡፡" }
{ "en": "However, it is not the working language of the federal government.", "amh": "ነገር ግን የፌዴራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ አልሆነም፡፡" }
{ "en": "According to Ethiopian Constitution, Oromia is one of the nine ethnically based and politically autonomous regional states in Ethiopia.", "amh": "እንደኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ ኦሮሚያ፣ በዘውግ ላይ ከተመሠረቱት ዘጠኝ የፖለቲካ ነጻነት ያላቸው የክልል መንግሥታት አንዱ ነው፡፡" }
{ "en": "Oromo people make up the largest ethnic group in Ethiopia.", "amh": "የኦሮሞ ሕዝብ በሕዝብ ብዛት በኢትዮጵያ ትልቁ ብሔር ነው፡፡" }
{ "en": "However, the group has been systematically marginalized and persecuted for the last 24 years.", "amh": "ይሁን እንጂ፣ የክልሉ ሕዝብ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ በተቀነባበሩ መገፋቶች እና የመብት ጥሰቶች ውስጥ አልፏል፡፡" }
{ "en": "By some estimates, there were as many as 20,000 Oromo political prisoners in Ethiopia as of March 2014.", "amh": "እስከ መጋቢት 2006 ድረስ 20,000 የሚገመቱ ኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ አንዳንድ ግምቶች ያስረዳሉ፡፡" }
{ "en": "A 2014 Amnesty International report on repression in the Oromia region noted:", "amh": "በ2006 ኦሮሚያ ውስጥ ስላለው ጭቆና በማተት የወጣ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል አንድ ሪፖርት እንዲህ ይላል:" }
{ "en": "Between 2011 and 2014, at least 5000 Oromos have been arrested based on their actual or suspected peaceful opposition to the government.", "amh": "በ2002 እና በ2006 መካከል፣ ቢያንስ 5,000 ኦሮሞዎች በሠላማዊ የመንግሥት ተቃውሟቸው ሳቢያ ታስረዋል፡፡" }
{ "en": "These include thousands of peaceful protestors and hundreds of opposition political party members.", "amh": "ይህ እንግዲህ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሠላማዊ ሰልፈኞችን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላቶችን ይጨምራል፡፡" }
{ "en": "The government anticipates a high level of opposition in Oromia, and signs of dissent are sought out and regularly, sometimes pre-emptively, suppressed.", "amh": "መንግሥት በኦሮሚያ ከፍተኛ ተቃውሞ ስለሚገጥመው የተቃውሞ ጭላንጭሎችን፣ አንዳንዶቹ መታየት ከመጀመራቸው በፊት ይጨፈልቃቸዋል፡፡" }
{ "en": "In numerous cases, actual or suspected dissenters have been detained without charge or trial, killed by security services during protests, arrests and in detention.", "amh": "ለበርካታ ጊዜያት፣ የተጠረጠሩ ተቃዋሚዎች ክስ ሳይመሰረትባቸው ይታሰራሉ፣ ወይም በእስር ወቅት ወይም በተቃውሞ ሰልፎች ጊዜ በፀጥታ ኃይሎች ይገደላሉ፡" }
{ "en": "The ruling elite of Ethiopia are mostly from the Tigray region, which is located in the northern part of the country.", "amh": "ኢትዮጵያን የሚመሯት ልሒቃን ምንጫቸው በኢትዮጵያ ሰሜን ከምትገኘው ትግራይ ክልል ነው፡፡" }
{ "en": "Social media fills in the gaps", "amh": "ማኅበራዊ ሚዲያ ክፍተቱን እየሞላ ነው" }
{ "en": "Even as the Ethiopian drought and impending food crisis makes a rare appearance in local—and some international—headlines, little attention is being paid to the student protests in Ethiopian media.", "amh": "ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ እና የተጋረጠው የምግብ እጥረት ቀውስ በአገር ውስጥ - እና ዓለም ዐቀፍ- ዜናዎች ላይ ርዕስ የመሆናቸው ዕድል ውስን በመሆኑ፣ የተማሪዎቹ ተቃውሞም እንደዚሁ በኢትዮጵያ ሚዲያ ትኩረት አላገኘም ማለት ይቻላል፡፡" }
{ "en": "But despite Ethiopia’s highly controlled online environment and the government’s firm grip on communications infrastructure, social media users are reporting on the issue, particularly on Facebook, with additional coverage coming from diaspora-based media.", "amh": "ነገር ግን፣ ከፍተኛ ቁጥጥር ካለበት እና ከመንግሥት የግንኙነት መሠረተ ልማቶች ጥብቅ ገደብ ተሻግሮም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በተለይም ፌስቡክ ላይ ሁሉንም ነገር ከዳያስፖራ ሚዲያዎች የዜና ሽፋን በተጨማሪ ሪፖርት በማድረግ ክፍተቱን ሞልተዋል፡፡" }
{ "en": "Photo widely circulated on social media, taken from the Facebook page of Jawar Mohammed.", "amh": "ይህ ፎቶ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው ተሰራጭቶ ከጃዋር መሐመድ የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ ነው፡፡" }
{ "en": "One Facebook user, for example, hoped for the world to hear stories of the student protesters' inspiring actions:", "amh": "አንድ የፌስቡክ ተጠቃሚ፣ ለምሳሌ፣ የተማሪዎቹን የተቃውሞ መንስኤ ዓለም እንዲሰማለት ተስፋውን ገልጧል:" }
{ "en": "The silence has truly been deafening.", "amh": "ዝምታው የውነት ያደነቁራል፡፡" }
{ "en": "We need to see and hear the inspiring actions undertaken by huge numbers of ‪#‎Oromo‬ in ‪#‎Ethiopia‬.", "amh": "ብዙ ቁጥር ባላቸው ኦሮሞዎች እየተካሄደ ያለውን የሚያነቃቃ ተግባር ማየትና መስማት አለብን፡፡" }
{ "en": "Tell their story, enable the world to be swept up in their story.Considering the complete absence of freedom to criticize the government or report opposition stories from within the country, people around the world reading about it can help greatly by doing everything possible to amplify this story.", "amh": "ታሪካቸውን እንናገር፣ ዓለም በታሪካቸው እንዲጥለቀለቅ ማስቻል አለብን፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ መንግሥትን የመተቸት ወይም የተቃውሞ ታሪኮችን ሪፖርት የማድረግ ነጻነት ካለመኖሩ አንጻር በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ሊያነቡት እና ዜናውን የቻሉትን በሙሉ በማድረግ ሊያስተጋቡት ይችላሉ፡፡" }
{ "en": "Another Facebook user, Aga Teshome, took note of the political power of Oromo youth:", "amh": "አጋ ተሾመ የተባለ ሌላ የፌስቡክ ተጠቃሚ የኦሮሞ ወጣቶች የፖለቲካ አቅምን በተመለከተ የሚከተለውን ዕይታውን አስፍሯል:" }
{ "en": "...‪#‎OromoProtests‬ a call for all oppressed people in ‪#‎Ethiopia‬ to support the ongoing protest against ‪#‎landgrabing‬ ....the Oromo youth are a powerful political entity capable of shaking mountains.", "amh": "…የኦሮሞ ተቃውሞ ሁሉንም የተጨቆኑ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በመሬት መቀራመት ላይ ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ …. የኦሮሞ ወጣቶች ተራራ ማንቀጥቀጥ የሚችል አቅም ያላቸው የፖለቲካ አካላት ናቸው፡፡" }
{ "en": "This powerful political entity is hell bent on exposing the EPRDF government’s atrocious human rights record and all round discriminatory practices.", "amh": "ይህ አቅም ያለው የፖለቲካ አካል የኢሕአዴግ መንግሥት የሰብኣዊ መብትን ደረጃ እና አግላይ ሥራዎችን የማጋለጥ ሚና ይጫወታል፡፡" }
{ "en": "While Desu Tefera said:", "amh": "ደሱ ተፈራ ደግሞ ይህን ይላል:" }
{ "en": "We call upon the media to investigate the conditions that these students died trying to expose and resist, to draw attention to these concerns.", "amh": "ሚዲያዎች እነዚህ ጉዳዩን ለመቃወም በመሞከራቸው የተገደሉ ተማሪዎች የሞቱበትን ሁኔታ መርምረው እንዲያጋልጡ ጥሪ እናደርጋለን፡፡" }
{ "en": "Oromia needs a new kind of reporting by the international media, which gives voice to the voiceless Oromo people, who for a very long time have been killed, mistreated, abused, neglected and repressed in Ethiopia.", "amh": "ኦሮሚያ በዓለም ዐቀፉ ሚዲያ ለድምፅ አልባው፣ ለረዥም ጊዜ የተገደሉ፣ የተንገላቱ፣ የተዘነጉ እና የተጨቆኑ የኦሮሞ ሕዝቦች ድምፅ የሚሆን አዲስ ዓይነት ዘገባ ያስፈልጋታል፡፡" }
{ "en": "Going forward with the current plan, which ends up displacing tens of thousands of poor farmers, destroying their livelihood and depriving their identity, is a tragedy.", "amh": "በዐሥር ሺሕዎች የሚቆጠሩ ገበሬዎችን የሚያፈናቅል፣ ኑሯቸውን የሚያጠፋ እና ማንነታቸውን የሚያንኳስሰውን ይህንን ዕቅድ ይዞ መቀጠል በጣም የሚያሳዝን ነው የሚሆነው፡፡" }
{ "en": "It deserves attention.", "amh": "ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡" }
{ "en": "These students put their lives on the line to draw attention to the farmers’ plight.‪#‎OromoProtests‬", "amh": "እነዚህ ተማሪዎች ለገበሬዎቹ ጥቅም ሲሉ ነው ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ያስቀመጡት፡፡" }
{ "en": "Although social media reports are pivotal in letting the world know about the protests, they miss a huge chunk of nuance that would help observers understand how this dispute is unfolding.", "amh": "ምንም እንኳን ማኅበራዊ ሚዲያዎች ተቃውሞውን በመዘገብ ረገድ ማዕከላዊ ሚና ቢጫወቱም፣ ታዛቢዎች ግጭቱ በምን ምክንያት እንደተከሰተ በማብራራቱ ረገድ ትልቅ ነገር ይጎድላቸዋል፡፡" }
{ "en": "Notably, the fact that the student protests combine delicate ethnic politics, urban land grabbing and Ethiopia’s diaspora community’s involvement in home country politics.", "amh": "በተለይም ደግሞ፣ የተማሪዎቹ ተቃውሞ የዘውግ ፖለቲካን እና የከተማ መሬት መቀራመትንም ያዋሀደ መሆኑና የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች በአገር ውስጥ ፖለቲካ ጉዳይ መሳተፋቸው ነገሩ መብራራት እንዲያስፈልገው ያደርጋል፡፡" }
{ "en": "Given Ethiopia’s highly controlIed environment, one might wonder how the students managed to get organized to express their grievance in the mid of highly controlled environment.", "amh": "የኢትዮጵያ ምኅዳር ቁጥጥር የበዛበት ከመሆኑ አንጻር፣ ተማሪዎቹ እንዴት ብሶታቸውን ለመግለጽ ነገሮችን ማስተባበር ቻሉ የሚለው ያጠያይቃል፡፡" }
{ "en": "Despite the firm grip on communication infrastructure there are constant update on Facebook and Twitter about the protest.", "amh": "ከምኅዳሩ መጥበብ እና ከመሠረተ-ልማቱ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር መዋል በላይ ፌስቡክ እና ትዊተር ስለ ተቃውሞው የመረጃ ምንጭ ሆነዋል፡፡" }
{ "en": "Dubious development practices", "amh": "አጠራጣሪ የልማት ሥራ" }
{ "en": "The story is unpleasantly familiar, as students are protesting for the second time in less than two years.", "amh": "ጉዳዩ በማያስደስት ሁኔታ የተለመደ ሆኗል፤ ምክንያቱም ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተመሳሳይ ተቃውሞ ሲከሰት ይህ ሁለተኛው ነው፡፡" }
{ "en": "In April and May 2014, the protests began in response to the government’s plan to implement the Integrated Masterplan for Addis Ababa”.", "amh": "በሚያዝ እና ግንቦት 2006፣ ተቃውሞዎቹ የጀመሩት መንግሥት የአዲስ አበባን የተቀናጀ ማስተር ፕላን” ሊተገብር መሆኑን ተከትሎ ነበር፡፡" }
{ "en": "As Addis Ababa, the capital of Ethiopia, is an enclave within Oromia regional state, students primarily from Oromia state accused the Ethiopian government of attempting to take over land owned by local farmers in the name of integrating adjacent Oromia towns into the sprawling city of Addis.", "amh": "አዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ የተከበበች ከተማ እንደመሆኗ ተማሪዎቹ መንግሥትን አጎራባች ከተሞችን ከአዲስ አበባ ጋር በማቀናጀት ሥም የገበሬዎችን መሬት ለመቀማት በማሰብ ይከስሱታል፡፡" }
{ "en": "The students further alleged that if implemented, the Masterplan would result in Addis Ababa further encroaching into the territory of Oromia.", "amh": "ተማሪዎቹ በተጨማሪም፣ ማስተር ፕላኑ ተግባር ላይ ከዋለ የኦሮሚያን አካባቢዎች ጠቅልሎ ለመውሰድ ያልማል በሚል መንግሥትን ይወነጅላሉ፡፡" }
{ "en": "The government rejected the accusation, claiming that the Masterplan was intended only to facilitate the development of infrastructure such as transportation, utilities, and recreation centers.", "amh": "መንግሥት ውንጀላውን የሚያጣጥለው ማስተር ፕላኑ የትራንስፖርት፣ የመዝናኛ እና መሰል የልማት መሠረት ልማቶችን ለመዘርጋት እንዲያስችል የተቀረፀ ነው በማለት ነው፡፡" }

Dataset Card for MAFAND

Dataset Summary

MAFAND-MT is the largest MT benchmark for African languages in the news domain, covering 21 languages.

Supported Tasks and Leaderboards

Machine Translation

Languages

The languages covered are:

  • Amharic
  • Bambara
  • Ghomala
  • Ewe
  • Fon
  • Hausa
  • Igbo
  • Kinyarwanda
  • Luganda
  • Luo
  • Mossi
  • Nigerian-Pidgin
  • Chichewa
  • Shona
  • Swahili
  • Setswana
  • Twi
  • Wolof
  • Xhosa
  • Yoruba
  • Zulu

Dataset Structure

Data Instances

>>> from datasets import load_dataset
>>> data = load_dataset('masakhane/mafand', 'en-yor')

{"translation": {"src": "President Buhari will determine when to lift lockdown – Minister", "tgt": "Ààrẹ Buhari ló lè yóhùn padà lórí ètò kónílégbélé – Mínísítà"}}


{"translation": {"en": "President Buhari will determine when to lift lockdown – Minister", "yo": "Ààrẹ Buhari ló lè yóhùn padà lórí ètò kónílégbélé – Mínísítà"}}

Data Fields

  • "translation": name of the task
  • "src" : source language e.g en
  • "tgt": target language e.g yo

Data Splits

Train/dev/test split

language Train Dev Test
amh - 899 1037
bam 3302 1484 1600
bbj 2232 1133 1430
ewe 2026 1414 1563
fon 2637 1227 1579
hau 5865 1300 1500
ibo 6998 1500 1500
kin - 460 1006
lug 4075 1500 1500
luo 4262 1500 1500
mos 2287 1478 1574
nya - 483 1004
pcm 4790 1484 1574
sna - 556 1005
swa 30782 1791 1835
tsn 2100 1340 1835
twi 3337 1284 1500
wol 3360 1506 1500
xho - 486 1002
yor 6644 1544 1558
zul 3500 1239 998

Dataset Creation

Curation Rationale

MAFAND was created from the news domain, translated from English or French to an African language

Source Data

Initial Data Collection and Normalization

[Needs More Information]

Who are the source language producers?

Annotations

Annotation process

[Needs More Information]

Who are the annotators?

Masakhane members

Personal and Sensitive Information

[Needs More Information]

Considerations for Using the Data

Social Impact of Dataset

[Needs More Information]

Discussion of Biases

[Needs More Information]

Other Known Limitations

[Needs More Information]

Additional Information

Dataset Curators

[Needs More Information]

Licensing Information

CC-BY-4.0-NC

Citation Information

@inproceedings{adelani-etal-2022-thousand,
    title = "A Few Thousand Translations Go a Long Way! Leveraging Pre-trained Models for {A}frican News Translation",
    author = "Adelani, David  and
      Alabi, Jesujoba  and
      Fan, Angela  and
      Kreutzer, Julia  and
      Shen, Xiaoyu  and
      Reid, Machel  and
      Ruiter, Dana  and
      Klakow, Dietrich  and
      Nabende, Peter  and
      Chang, Ernie  and
      Gwadabe, Tajuddeen  and
      Sackey, Freshia  and
      Dossou, Bonaventure F. P.  and
      Emezue, Chris  and
      Leong, Colin  and
      Beukman, Michael  and
      Muhammad, Shamsuddeen  and
      Jarso, Guyo  and
      Yousuf, Oreen  and
      Niyongabo Rubungo, Andre  and
      Hacheme, Gilles  and
      Wairagala, Eric Peter  and
      Nasir, Muhammad Umair  and
      Ajibade, Benjamin  and
      Ajayi, Tunde  and
      Gitau, Yvonne  and
      Abbott, Jade  and
      Ahmed, Mohamed  and
      Ochieng, Millicent  and
      Aremu, Anuoluwapo  and
      Ogayo, Perez  and
      Mukiibi, Jonathan  and
      Ouoba Kabore, Fatoumata  and
      Kalipe, Godson  and
      Mbaye, Derguene  and
      Tapo, Allahsera Auguste  and
      Memdjokam Koagne, Victoire  and
      Munkoh-Buabeng, Edwin  and
      Wagner, Valencia  and
      Abdulmumin, Idris  and
      Awokoya, Ayodele  and
      Buzaaba, Happy  and
      Sibanda, Blessing  and
      Bukula, Andiswa  and
      Manthalu, Sam",
    booktitle = "Proceedings of the 2022 Conference of the North American Chapter of the Association for Computational Linguistics: Human Language Technologies",
    month = jul,
    year = "2022",
    address = "Seattle, United States",
    publisher = "Association for Computational Linguistics",
    url = "https://aclanthology.org/2022.naacl-main.223",
    doi = "10.18653/v1/2022.naacl-main.223",
    pages = "3053--3070",
    abstract = "Recent advances in the pre-training for language models leverage large-scale datasets to create multilingual models. However, low-resource languages are mostly left out in these datasets. This is primarily because many widely spoken languages that are not well represented on the web and therefore excluded from the large-scale crawls for datasets. Furthermore, downstream users of these models are restricted to the selection of languages originally chosen for pre-training. This work investigates how to optimally leverage existing pre-trained models to create low-resource translation systems for 16 African languages. We focus on two questions: 1) How can pre-trained models be used for languages not included in the initial pretraining? and 2) How can the resulting translation models effectively transfer to new domains? To answer these questions, we create a novel African news corpus covering 16 languages, of which eight languages are not part of any existing evaluation dataset. We demonstrate that the most effective strategy for transferring both additional languages and additional domains is to leverage small quantities of high-quality translation data to fine-tune large pre-trained models.",
}
Downloads last month
227

Models trained or fine-tuned on masakhane/mafand