id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-44843966
https://www.bbc.com/amharic/news-44843966
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ መከላከያና ፌደራል ፖሊስ ግጭቶችን እንዲያስቆሙ አዘዙ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን የመከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ በማርገብ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡና ተጠያቂዎቹንም ለፍርድ እንዲያቀርቡ አዘዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሦስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት መጠናቀቅን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ነው። • የፕሬስ ነፃነት እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ "በየትኛውም ቀጠና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ፣ የሰው ህይወት የሚያጠፉና የሚያጠፋ ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ ግለሰቦችና ቡድኖች ከህግ ፊት እንድታቀርቡ። መሀል ገብታችሁ ሃገራዊና ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ" ብለዋል። በተጨማሪም "ሥራችሁን በምትሰሩበት ወቅት ጥፋትና ተጨማሪ ኪሳራ እንዳይኖር ሙያዊ፣ ጥበባዊና በመረጃ የታገዘ ሥራ በመስራት ህዝብ ሳይሞትና ንብረት ሳይወድም ሰላም የሚወርድበትን መንገድ በመፍጠር ብቃታችሁን ማሳየት ይገባል።" ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአላስፈላጊ ግጭቶች ምክንያት የሰው ህይወት እየጠፋ እንደሆነ ጠቅሰው፤ በቅርቡም በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች የብዙ ሰዎች ህይወት መቀጠፉ ማሳያ እንደሆነ ጠቅሰዋል። • የዐብይ ቀጣይ ፈተናዎች ለዚህ ተጠያቂ ያደረጓቸው በቀጥታ የሚሳተፉትን ብቻ ሳይሆን ራቅ ብለው ግጭቱንም የሚያቀጣጥሉትንም አውግዘዋል። በግጭቱና በቀውሱ ግለሰቦችና ቡድኖችም ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል። "እኛ ዝቅ ብለን ህዝባችንን ከፍ ማድረግ እንጂ ህዝባችን ጫንቃ ላይ ተጭነን ለመንገሥ የምናደርገው ማንኛውም ትናንሽ ሙከራዎች ሄደው ሄደው በታሪክ አስወቃሽ መሆናቸው አይቀርም" ብለዋል። የመብት ተሟጋቾች፣ አርቲስቶችና ባለሙያዎች "ቆስቃሽና የሚያጋጩ ጉዳዮችን ከማድረግ ይልቅ ሰላምን ላይና የሚያቀራርቡ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ" አደራ ብለዋል። • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እርምጃዎች የት ድረስ? በሶማሌና በኦሮሚያ ክልል ብቻ ሳይሆን በተለያዩ አካባቢዎች ህዝቦችን የሚያጋጩ ሙከራዎች ትርፍ እንደሌላቸው በተጨማሪ ተናግረዋል። "ሰው ይሞታል፤ ሁሌም ሟች ደሃ ነው። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምንናገር ሰዎች ሳንሆን በየሰፈሩ ያለ ደሃ እኛን አምኖና ሰምቶ ህይወቱን ባልተገባ ሁኔታ ስለሚገብር ሰዎች እንዳይሞቱና ንብረት እንዳይወድም፤ ሁላችንም ተባብረን መስራት ይገባናል"ብለዋል። ሀገሪቷ በአንድነት የምትቆምበት ጊዜ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው "ቀስቅሶ ሰውን ከሰው፣ ቡድንን ከቡድን ማጣላት አዲስ ነገር አይደለም። የኖርንበት የምናቀው ነው፤ የማይበጀንን አምጥታችሁ በስሜት እየተነዳችሁ ህዝብን ከምታባሉ ስሜታችሁን አሸንፋችሁ ህዝብን ብታስታርቁ፤ ህዝብን የሚያገናኝ ድልድይ ብትሰሩ ከታሪክ ተወቃሽነት ትድናላችሁ" ብለዋል። የጠቅላይ ሚንስትሩን መግለጫ ተከትሎ የኦሮሚያ እና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መስተዳደሮች ግጭት በሚከሰትባቸው የሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ድንበር ላይ የፌደራል ፖሊስ አንዲሰፍር መስማማታቸውን ብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል። • የጠቅላይ ሚኒስትሩ 100 ቀናት ከዚህም በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግለሰቦች እጅ ያለን የውጭ ምንዛሬ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ባንክ ሄደው እንዲመነዝሩ ያሳሰቡ ሲሆን "በርከት ያለ የውጭ ምንዛሬ እያስገባን ስለሆነ፤ ራሳችሁን ከኪሳራ ልትታደጉ ይገባል" ብለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የመንግሥትና የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሬም ሆነ ከፍተኛ ብር ይዘው ለሚመጡ ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ያለማንገራገር አገልግሎት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። "ከጥቂት ሳምንት በኋላ የተከማቹ ገንዘቦች ላይ የሚደረጉ ዘመቻዎች ስላሉ፤ ያ ከመፈፀሙ በፊት በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ ገንዘባቸውን እንዲያስገቡና የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመፍጠር የምናደርገውን ጥረት በማገዝ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አደርጋለሁ" ብለዋል። በተጨማሪም የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ገልፀው፤ ለእንግዳ ተቀባዩ ሕዝብ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል። በሁለቱ ሃገራት መካከል ሊናድ የማይችል ግንኙነት እንደተመሰረተ ጠቅሰው ቀጣዩ ሥራ የሁለቱንም ህዝቦች ህይወት ማሻሻል እንደሆነ ተናግረዋል። የኢትዮጵያና ኤርትራን የአብሮነት እርምጃ ምን ይፈትነዋል? ለሃያ ዓመታት ተዘግቶ የነበረው የኤርትራ ኤምባሲም ሥራ መጀመሩ ለወደፊቱ ግንኙነት ትልቅ እመርታ እንደሆነም ተናግረዋል። ሁለቱ ሃገራትም ወደፊት ትልቅ ተስፋ አላቸው ብለዋል።
news-50909605
https://www.bbc.com/amharic/news-50909605
በጋምቤላ ክልል በመንግሥት መኪና የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎችን ሲያዘዋውሩ ያገኛቸውን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ኦፒያንግ ኦቻን ለቢቢሲ ገለፁ።
ሕገ ወጥ መሳሪያዎቹ የተያዙት በግልና በመንግሥት መኪኖች መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነር ኦፒያንግ መኪናውን ለአጣቢ ሰጥቶ የሚያጥበው ልጅ ያለ ሹፌሩ እውቅና ይዞ መሄዱን ይናገራሉ። የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ የፀጥታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ኦታዎ ኦኮት በበኩላቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት 12 ክላሽንኮቮችና 471 ጥይቶች መሆናቸውን አረጋግጠዋል። አክለውም አቶ ኦታዎ የመንግሥት መኪናውን ሲያሽከረክር የነበረው የክልሉ አፈ ጉባኤ ሹፌር ነው ብለዋል። • የጦር መሳሪያዎቹ ምንጫቸው የት ነው? • ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መበራከት ምንን ያመለክታል? • አሳሳቢው የሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዝውውር በኢትዮጵያ የመንግሥት መኪና ሲያሽከረክር የነበረው ግለሰብ ያለ ኃላፊው እውቅና ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ መኪናውን ይዞ መውጣቱን ተናገሩት የፀጥታ ኃላፊው፣ በቁጥጥር ስር የዋለው የግል መኪና ግን ማለዳ 12 ሰዓት አካባቢ መያዙን ያስረዳሉ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰኞ ታህሳስ 13 ምሽት መሆኑንም ገልፀዋል። መሳሪያውና ጥይቶቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኢታንግ አካባቢ በሚገኝ ኬላ ላይ መሆኑን የተናገሩት አቶ ኦታዎ እስካሁን ድረስ ሦስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጨምረው አስረድተዋል። የተጠርጣሪዎቹ ምርመራ በሒደት ላይ መሆኑን የተናገሩት ኮሚሽነሩ አስፈላጊው ምርመራ እንደተጠናቀቀ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ገልፀዋል። በጋምቤላ ክልል በላፉት ሶስት ወራት ብቻ 47 ሕገወጥ የጦር መሳሪያዎች ወደ ክልሉ ሲገቡ መያዛቸውን የጠቀሱት አቶ ኦታዎ ኦኮት ትናንት ከተያዙት ጋር በአጠቃላይ 59 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎች መያዛቸውን አስረድተዋል። "ሕገ ወጥ መሳሪያዎቹ የሚመጡት በደቡብ ሱዳን በኩል ነው" በማለት የተናገሩት ደግሞ ኮሚሽነር ኦፒያንግ ናቸው። በኢትዮጵያ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ዝውውር እጨመረ መምጣቱንና የጸጥታ ኃይሎችም ከፍተኛ መጠን ያለቸውን መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ በተለያዩ ጊዜ መዘገቡ ይታወሳል።
news-56714415
https://www.bbc.com/amharic/news-56714415
ኢራን በኒውክሌር ተቋሟ ላይ 'እስራኤል ፈጸመች' ያለችውን ጥቃት እንደምትበቀል ዛተች
የኢራን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል በአገራቸው የኒውክሌር ማዕከል ላይ ለፈፀመችው ጥቃት "የበቀል እርምጃ" እንወስዳለን ሲሉ ዛቱ።
የኢራን ባለሥልጣናት ናታንዝ የዩራኒየም ማበልፀጊያ እሁድ ዕለት መጀመሪያ የኃይል መቋረጥ አጋጥሞት ነበር ቢባልም በኋላ ግን "በኒውክሌር አሸባሪዎች" ጥቃት ደርሶበት ነበር ብለዋል። ለዚህ ጥቃትም ባለሥልታነቱ ዋነኛ ጠላታችን የሚሏትን እስራኤልን ተጠያቂ አድርገዋል። አዲስ የተገነባው የዩራኒየም ማበልጸጊያ ጥቃቱ ሲገጥመው ገና ሥራ መጀመሩ ነው። እስራኤል በጉዳዩ ላይ አስተያየቷን ባትሰጥም የአገሪቱ የሕዝብ ሬዲዮ የደኅንነት ምንጮችን በመጥቀስ የተፈጸመው ጥቃት በአገሪቱ የስለላ ተቋም ሞሳድ አማካይነት በመረጃ መረብ ላይ የተካሄደ ተልዕኮ ነው ብሏል። እንደ ሬዲዮው ከሆነ ኢራን ከገለፀችው በላይ የከፋ ጉዳት ማብላያው ላይ ደርሷል። የአሜሪካ የደኅንነት ባለሥልጣናት ለኒውዮርክ ታይምስ እንደነገሩት ከሆነ ከፍተኛ ፍንዳታ ከመሬት በታች ለሚገኘው ማዕከል ኃይል የሚያቀርበውን ውስጠኛ ሥርዓትን ሙሉ በሙሉ አውድሞታል። በስፍራው ማብላያውን ዳግም ወደ ሥራ ለማስገባት ዘጠኝ ወራት ያስፈልጋሉም ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። ኢራን እኤአ በ2015 ከቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሩሲያ እና ዩናይትድ ኪንግደም ጋር የኒውክሌር ፕሮግራሟን ለመገደብ እና አሜሪካ የጣለችባት ማዕቀቦች እንዲነሱላት ስምምነት አድርጋ ነበር። ነገር ግን የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ አሜሪካ ከዚህ ስምምነት ወጥታ ቆይታለች። አዲሱ የጆ ባይደን መንግሥት ወደዚህ ስምምነት ለመመለስ እንደሚፈልግ ተገልጿል። እስራኤል ግን ስለ ኢራን ስለምታካሂደው የኒውክሌር ፕሮግራም ማስጠንቀቂያዎችን ስትሰጥ ቆይታለች። የደረሰው ምን ነበር? ኢራን ውስጥ አዲስ የዩራኒየም ማብላያ መሳሪያ ይፋ በተደረገ ማግሥት የኒውክለር ተቋሟ "አሻጥር" እንደተሰራበት አንድ የአገሪቱ ከፍተኛ የኒውክሌር ባለሥልጣን ነበር የተናገሩት። ይህ የሆነው እሁድ ዕለት ሲሆን በአገሪቱ ዋና ከተማ ቴህራን ደቡባዊ ክፍል የሚገኘው ናታንዝ በተሰኘው ተቋም ላይ የኤሌትሪክ ኃይል መቋረጥ አጋጥሞ ነበር ተብሏል። የኢራን አቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊ አሊ አክባር ሳሌሂ ይህንን የኤሌትሪክ ኃይል እንዲቋረጥ ያደረገው "የሽብር ተግባር" ያሉትን ማን እንደፈፀመው ይፋ አላደረጉም። የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ግን የደኅንነት ምንጮችን ጠቅሰው እስራኤል ባደረሰችው የሳይበር ጥቃት የተከሰተ ነው ሲሉ ዘግበዋል። እስራኤል ስለክስተቱ በይፋ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥባለች። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢራን ስለምታካሂደው የኒውክሌር ፕሮግራም ማስጠንቀቂያ ስትሰጥ እንደነበር ይታወሳል። ይህ ክስተት የተፈጠረው በ2015 ተገብቶ የነበረውን የኒውክሌር ስምምነት በ2018 በትራምፕ አስተዳደር ከተገፋ በኋላ ዳግም ለማስቀጠል በሚታሰብበት ወቅት ነው። ቅዳሜ ዕለት የኢራን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሃኒ በናታንዝ አዲስ ማብላያ ሲመረቅ ተገኝተው ነበር። ማብላያው የበለፀገ ዩራኒየም ለማምረት የሚረዳ ሲሆን ይህም ለነዳጅ ምርት ካልሆነም ደግሞ የኒውክሌር መሳሪያ ለማምረት ያገለግላል። ይህ የኢራን ድርጊት አገሪቱ በ2015 የገባችውን ስምምነት የሚጥስ ሲሆን በወቅቱ የተወሰነ መጠን ያለው የበለፀገ ዩራኒየም ለማምረትና እና ለማከማቸት ብቻ ስምምነት ላይ ደርሳ ነበር። ይህ የምታመርተው ዩራኒየምም ለተወሰኑ የኃይል ማምረቻዎች እንደ ነዳጅ በመሆን እንዲያገለግል ታቅዶ ነበር። እሁድ ዕለት የኢራን አቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ቃል አቀባይ ቤህሮዝ ካማልቫንዲ እንዳሉት "ክስተቱ" ያጋጠመው ጠዋት በኒውክሌር ማምረቻው የኃይል ኔትወርክ ላይ ነው። ካልቫንዲ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡ ሲሆን ነገር ግን ለኢራን ፋርስ የዜና ኤጀንሲ "ምንም አይነት አደጋ ወይንም ያመለጠ ነገር የለም" ሲሉ ተናግረዋል። በኋላም ላይ የአገሪቱ ቴሌቪዥን ከመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ አሊ አክባር ሳሌሂ የተሰጠ መግለጫ ያቀረበ ሲሆን ድርጊቱን "አሻጥር" እና "የኒውክሌር ሽብርተኝነት" ሲል ገልፀውታል። በመግለጫው ላይ አክለውም "ይህንን አሳፋሪ ተግባር እያወገዝን እስላማዊ ሪፐብሊክ ኢራን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ከኒውክሌር ሽብርተኝነት ጋር እንዲያዩት እንደምትፈልግ እንጠይቃለን" ብለዋል። የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ክስተቱ ስለመፈጠሩ መረጃ እንደደረሰው ገልጾ፣ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። ባለፈው ሐምሌ ወር በናታንዝ በሚገኘው ተቋም ላይ በተከሰተ እሳት የማዕከላዊ ማብላያውን መገጣጠሚያ ወርክሾፕ ያቃጠለ ሲሆን የአደጋው መንስኤ አሻጥር መሆኑ ተገልጾ ነበር። እኤአ በ2015 ኢራን እና ስድስት አገራት ስምምነት ላይ ደርሰው የነበረ ሲሆን በዚህ ስምምነት ላይም ኢራን የተወሰኑ የኒውክሌር ተግባራቷን ለማቋረጥ ስትስማማ በምላሹም ምጣኔ ኃብቷን እየጎዳው ከሚገኘው የተጣለባት ቅጣት ወይንም ማዕቀብ እንደሚላላ አልያም እንደሚነሳ ተቀምጧል። የእስራኤል መገናኛ ብዙኀን፣ ካን ስሙን ያልገለፀው አንድ የደህንነት ምንጭ ጠቅሶ በተቋሙ ላይ ያጋጠመው የኃይል መቋረጥ የእስራኤል ሳይበር ኦፕሬሽን በወሰደው እርምጃ ነው ብሏል። ሮን ቤን ዪሻሂ የተሰኙ የመከላከያ ተንታኝ ለ ዋይኔት የዜና ድረገጽ እንዳሉት ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመታጠቅ እያደረገች ያው ግስጋሴ ስጋት ነው ብሎ ለማሰብ በቂ ነው ካሉ በኋላ፣ የኃይል መቋረጡ በአደጋ የተፈጠረ ላይሆን ይችላል ብለዋል። አክለውም " . . .የኒውክሌር ሩጫ ግስጋሴን ለማስቆም ከአሜሪካ ጋር በተደረገ ስምምነት ይኹነኝ ተብሎ በተሰራ አሻጥር " ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል። ኢራን ከስድስቱ አገራት ጋር የገባችው ስምምነት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገራቸው ከስምምነቱ መውጣቷን ካስታወቁ በኋላ ውጥረት አስከትሏል። አዲሱ የባይደን አስተዳደር ዳግም ስምምነቱን ለመመለስ የሚያስችል ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን ጀምሯል። ነገር ግን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ባለፈው ሳምነት ስምምነቱ ዳግም ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት አስመልክተው ያስጠነቀቁ ሲሆን አገራቸው ከቴህራን ጋር በአዲስ ስምምነት እንደማትፈራረም አስታውቀዋል።
news-55962231
https://www.bbc.com/amharic/news-55962231
ፕሬዝደንት ባይደን፡ ለትራምፕ የአገር ምስጢር መነገር የለበትም
ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የአገር ሚስጥር ለቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ መነገር የለበትም አሉ።
ጆ ባይደን የቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የአገር ሚስጥር መስማት የለባቸውም ያሉት ትራምፕ “የማይገመት ባህሪ” ስላላቸው ነው ብለዋል። አሜሪካ በተቀማጩ ፕሬዝደንት ፍቃድ ለቀድሞ የአገሪቱ ፕሬዝደንቶች አገራዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ የማደረግ ልምድ አላት። ባይደን አስተዳደራቸው ለቀድሞ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የጸጥታ ጉዳዮችን በተመለከተ ገለጻ እንደሚያደርግ ሲጠየቁ፤ “ይህ የሚሆን አይመስለኝም” ሲሉ መልሰዋል። ባይደን የትራምፕን “መገመት የማይቻል ባህሪ” ከግምት በማስገባት ክልከላ እንዳደረጉ ተናግረዋል። ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ትራምፕ ሚስጥራዊ ጉዳዮች ገለጻ ቢደረግላቸው ምን ይፈጠራል ብለው እንደሚሰጉ ሲጠየቁ ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ይሁን እንጂ ባይደን ትራምፕ አገራዊ ሚስጥር ቢነገራቸው፤ ሚስጥሩን ለሌሎች ሳያጋሩ ይዘው ይቆያሉ ብሎ መገመት እንደማይቻል ጠቁመዋል። “ለእርሳቸው የደህንነት ገለጻ ማድረጉ ጥቅሙ አይታየኝም። ለእርሳቸው ገለጻ ማድረጉ ምን የሚጨምረው ፋይዳ አለ? አምልጧቸው የሆነ ነገር ካላሉ በስተቀር” ሲሉ ፕሬዝደንት ባይደን ተናግረዋል። ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው ከአገሪቱ ደህንነት ሰዎች ጋር እስጠ አገባ ውስጥ ቆይተዋል። በአራት ዓመት የፕሬዝደንትነት ዘመናቸው ስድስት የብሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተሮችን ቀያይረዋል። ትራምፕ የአገራቸው ደህንነት ኤጀንሲ ሩሲያ በ2016 የአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ ገብታለች ማለቱ አበሳጭቷቸው ነበር። የአሜሪካ ደህንነት በኢራን ላይ በቂ እርምጃ አልወሰደም ሲሉም በተደጋጋሚ ተችተዋል። እአአ 2017 ላይ ደግሞ ትራምፕ የኢስላሚክ ስቴት ኦፕሬሽንን በተመለከተ ለሩሲያ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ጥብቅ ሚስጢራዊ መረጃን አሳልፈው ሰጥተዋል። ይህም በበርካታ የአሜሪካ ደህንነት ሹሞች ዘንድ እንደ ክህደት ተቆጥሮ ነበር።
48565577
https://www.bbc.com/amharic/48565577
የዓለም ጤና ድርጅት፡ 'በየቀኑ አንድ ሚሊየን ሰው በአባላዘር በሽታ ይያዛል'
የዓለም ጤና ድርጅት በዓለማችን ላይ በየዕለቱ አንድ ሚሊየን ሰው በግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚተላለፉ የአባላዘር በሽታዎች እንደሚያዝ አስታወቀ።
በግብረ ሥጋ ግንኙነት ከሚተላለፉት አራት ኢንፌክሽኖች መካከል፣ ክላይሜዲያ፣ ጨብጥ፣ቂጥኝና የብልት በሽታ (ትራይኮሞኒያሲስ)፣ በአንዱ የሚያዙ 376 ሚሊየን ሰዎች አሉ ይላል ሪፖርቱ። የዓለም ጤና ድርጅት አባላዘር በሽታዎችን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ፍሬ አለማፍራቱን በመጥቀስ የአሁኑ መረጃ የማንቂያ ደወል ይሆናል ብሏል። • ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው? • የወሲብ ቪዲዮ ህይወቷን ያሳጣት ወጣት የዘርፉ ባለሙያዎች ደግሞ መድሃኒትን የሚቋቋም የአባላዘር በሽታ መከሰት ይበልጥ አሳስቧቸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት አራቱን በግብረ ሥጋ የሚተላለፉ በሽታዎች በየጊዜው ያሉበትን ደረጃ ይፈትሻል። በየሃገራቱ በበሽታው ላይ የሚደረጉ ምርምሮችንና የሚታተሙ ጥናታዊ ጽሑፎችን ይመረምራል። ድርጅቱ በ2012 ካደረገው ፍተሻ በኋላ ያለውን ሲመዝን ምንም የበሽታው ሥርጭት የመቀነስ አዝማሚያ አለመታየቱን ይፋ አድርጓል። ከ25 ሰዎች አንዱ ከእነዚህ አራት አባላዘር በሽታዎች መካከል በአንዱ፣ ከአንድ በላይ በሆነ ተያያዥ ኢንፌክሽን ይያዛል ሲል ይፋ አድርጓል። በ2016 ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 49 በሆኑ ሰዎች ላይ በተሰበሰበ መረጃ የብልት በሽታ (ትራይኮሞኒያሲስ) በወሲብ ወቅት በጥገኛ ተዋህሲያን የሚተላለፍ ሲሆን ክላይሜዲያ፣ ጨብጥና ቂጥኝ በባክቴሪያ ኢንፌክሽን የሚተላለፉ ናቸው። ትልቅ ቀውስን እየተጋፈጥን ይሆን? በግብረ ሥጋ የሚተላለፉ የአባላዘር በሽታዎች ሽንት በሚሸናበት ወቅት ማቃጠል፣ ፈሳሽ መኖር፣ በወር አበባ መካከል መድማት ምልክቶቻቸው ናቸው። ቢሆንም እንኳን በርካቶቹ በሽታዎች ምልክቶች የላቸውም። የእነዚህ በሽታዎች የተባባሱ ጤና መታወኮች የዳሌ አጥንት አካባቢ የሚኖር መቆጥቆጥ፣ ክላይሜዲያና ጨብጥ ደግሞ ሴቶችን ለመካንነት ሊዳርጓቸው ይችላሉ። በቂጥኝ የተያዘ ሰው በፍጥነት ሕክምና ካላገኘ ከልብና ከነርቭ ሕመም ጋር ተያያዥ ለሆኑ የጤና ችግሮች ሊጋልጥ ይችላል። አንዲት ሴት ነፍሰጡር እያለች በቂጥኝ ከተያዘች ፅንሱ ሊሞት አልያም ያለ ጊዜው ቀድሞ ሊወለድ፣ የሕፃኑ ክብደት ሊቀንስ፣ የሳንባ ምች፣ ዓይነ ስውርነት እና ለአዕምሮ እድገት ውስንነት ሊያጋልጠው ይችላል። የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው ሰዎች ጥንቃቄ የተሞላበት ወሲብ መፈፀም እንዲሁም ኮንዶም መጠቀም አለባቸው ሲል ይመክራል።
news-49889110
https://www.bbc.com/amharic/news-49889110
ጋናውያኑን ያስቆጣው መሠረታዊ ስነ ወሲብ ትምህርት
በጋና ዕድሜያቸው ከአራት አመት ጀምሮ ላሉ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ለመስጠት ታቅዶ የነበረው መሠረታዊ የስነ ወሲብ ትምህርት ከወላጆችና ከክርስቲያን ቡድኖች በገጠመው ተቃውሞ ምክንያት ተቋረጠ።
የጋና የትምህርት ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ የዩኔስኮ ፕሮግራም ተማሪዎች ስለ ወሲብ እና ስነ ተዋልዶ ጉዳዮች አጠቃላይ መረጃ እንዲኖራቸው ያደርጋል። የጋና ትምህርት አገልግሎት ዳይሬክተር እንዳሉት ይህ መሰረታዊ የስነ ወሲብ ትምህርት ተማሪዎቹ "በጎ የሆነ አመለካከት እንዲያዳብሩ፣ ለራሳቸውና ለሌሎች ክብር እንዲኖራቸው፣ አእምሯቸውን እንዲያዘጋጁ፣ ሌሎች ላይ እንዳይፈርዱና የስነተዋልዶና ወሲብ ጉዳዮች ላይ ኃላፊነት አንዲሰማቸው ያደርጋል" ብለዋል። • የሳዑዲው ልዑል ኢራን ለዓለም ነዳጅ ምርት ስጋት ናት አሉ • "ስትፀልይም፤ ስታነብም ትደበደባለህ" በናይጀሪያ ሕንፃ ታጉረው ከነበሩት አንዱ • በአሜሪካ ወታደራዊ ካምፕ ላይ አልሻባብ ጥቃት መሰንዘሩ ተነገረ ይህንን መርሀ ግብር የተቃወሙ አካላት ሕፃናቱ ስለተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እየተዋወቁ ነው ሲሉ ይከስሳሉ። " ይህ ስልት ነው፤ ዕቅድ አላቸው። ግልፅ ሆኖ እንዲታይ ያልተፈለገ ነገር አለ" ይላል የስነወሲብና ቤተሰብ ጉዳዮች በአግባቡ መሰጠት አለባቸው ሲል የሚከራከረው ጥምረት መሪ የሆነው ሞሰስ ፎህ አሞኒንግ፤ እርሱ እንደሚለው የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት "ሀጥያት" ነው። ወላጆችና ክርስቲያን ቡድኖች ልጆቹ ለአካለ መጠን ሳይደርሱ ለምን ስለ ወሲብ እንዲማሩ ተፈለገ ሲሉ በመጠየቅ እቅዱን "ሰይጣናዊ" ሲሉ ይቃወሙታል። የጋና መምሕራን ማህበር በበኩሉ በዚህ መርሀግብር ማንም እንዳላማከረው ገልጿል። ይህ መሰረታዊ የስነ ወሲብ ትምህርት ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ከተደረገበት በኋላ መሰጠት ይጀምራል ተብሏል።
news-53496112
https://www.bbc.com/amharic/news-53496112
የውጭ ጉዳይ ሚንሰትሩ ኢትዮጵያ የአባይን 'ሐይቅ' ለፈለገችው ዓላማ ልትጠቀም ትችላለች አሉ
የኢትዮጵያ የውጨ ጉዳይ ሚንሰትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ የአባይን 'ሐይቅ' ለፈለገችው ዓላማ ልትጠቀም ትችላለች አሉ።
የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ይህንን ያሉት በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት አጭር መልዕክት ሲሆን ኢትዮጵያ የአባይን ውሃ አስፈላጊ ነው ላለችው ዓላማ ልትጠቀምበት እንደምትችል አመልክተዋል። ባሰፈሩት ጽሁፍ "አባይ ወንዝ ነበር ተገርቶ ወንዝም ሐይቅም ሆነ" ያሉት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ፤ "ከእንግዲህ በወንዝነቱ ይፈሳል። በሐይቅነቱ ኢትዮጵያ ለፈለገችው ልማት ሁሉ ለመዋል እጅ ሰጥቷል። እውነትም አባይ የእኛ ሆነ!!" ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ይህን ያሉት፤ ኢትዮጵያ ትናንት ምሽት በመጀመሪያው ዓመት ለመሙላት የታቀደው የውሃ መጠን መሞላቱን ይፋ ካደረገች በኋላ ነው። አሁን ያለው የዝናብ ሁኔታ የህዳሴ ግድቡን በውሃ ለመሙላት አመቺ እንደነበረና በመጀመሪያው ዓመት ለመሙላት የታቀደው የውሃ መጠን ሞልቶ በግድቡ አናት ላይ እየፈሰሰ መሆኑን የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ማስታወቁ ይታወሳል። የጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ እንደተገለጸው፤ በዚህ ዝናባማ ወር ውስጥ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በነበረው መልካም የዝናብ ሁኔታ በመጀመሪያው ዓመት ለመሙላት የታቀደው የውሃ መጠን ሞልቶ፤ ውሃው በግድቡ አናት ላይ እየፈሰሰ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የግድቡ የውሃ ሙሌት ሐምሌ አጋማሽ ላይ እንደሚጀምር ቁርጠኝነቱን ሲያሳውቅ ነበር። ግብጽ እና ሱዳን በበኩላቸው በግድቡ ዙሪያ ሙሉ ስምምነት ሳይደረስ ውሃ መሙላት መጀመር ለድርድር ሂደት እክል ይሆናል እያሉ ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል። የሦስቱ አገራት መሪዎች እና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሰብሳቢ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ የሚመሩት ውይይት አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቦ መጠናቀቁ ተነግሯል። ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ ውይይቶችን በማድረግ አጠቃላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተስማምተዋል ብሏል መግለጫው። የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳም የተካሄደው ውይይት ውጤታማ እንደነበረ ጠቅሰው፤ የሦስቱ አገራት ውይይት ይቀጥላል ካሉ በኋላ፤ የአፍሪካዊያንን ችግር በአፍሪካ መፍትሄ ለመስጠት በሚደረገው ጥረት በስበሰባው የተሳተፉትን አካላት አመስግነዋል። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንሰትር አብደላ ሃምዱክ በተመሳሳይ የተደረገው ውይይት ስኬታማ እንደነበረ ገልጸዋል። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር ግድቡ የሚሞላበትን እና የሥራው ሂደት በተመለከተ ድርድሮች እንዲቀጥሉ ተግባብተናል ብለዋል። አሃረም ኦላይን የፕሬዝደንት አል-ሲሲን ቢሮ ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ግብጽ ከኢትዮጵያ እና ከሱዳን ጋር ግድቡ የሚሞላበት እና የግድቡን አሰራር በተመለከተ ከስምምነት ለመድረስ ተስማምታለች ብሏል። መግለጫውን ተከትሎ በርካቶች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የእንኳን ደስ አለን መልዕክት ሲለዋወጡ አምሽተዋል። በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍጹም አረጋ፤ ግድቡ ውሃ መያዝ መጀመሩን በመግለጽ በፌስቡክ ገጻቸው የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላለፈዋል። የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ 6ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት በአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ይሆናል። 65 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንም የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደሚያገኙ ይታመናል።
news-51797891
https://www.bbc.com/amharic/news-51797891
ኢቲ 302 ቦይንግ 737፡ ልክ የዛሬ አንድ ዓመት በኢትዮጵያው አውሮፕላን ላይ ምን ተከሰተ?
ዕሑድ መጋቢት 1 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ለኢትዮጵያዊያን አስደንጋጭ ዕለት ነበር።
እርግጥ 'የኢትዮጵያ'' ታሪኩ የከፍታ ነው። የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ሲንደፋደፍ 'ET' ከፍ ብሎ በሯል፤ያውም ለዘመናት። በትርፍም፣ በአውሮፕላን ብዛትም፣ በበረራ ስፋትም፣ በመስተንግዶ ጥራትም ሞገስ ተለይቶት አያውቅም። በጥቅሉ ከፍ እንጂ ዝቅ ብሎ አያውቅም። በዚያች ሰንበት ግን 'ማክስ-8' ጎንበስ ካለበት ቀና አልል አለ። አብራሪዎቹ የቻሉትን ሞከሩ። አልሆነም። • ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በመግለጫ ምልልስ እየተወዛገቡ ነው የአውሮፕላኑ ሠሪዎች ጥፋቱን በአብራሪዎች ለመደፍደፍ የቀደማቸው አልነበረም። መጀመርያ ጥርጣሪያቸውን አስቀደሙ፤ ቀጥለው የሚዲያ ዘመቻ ከፈቱ። ችግሩ ከአብራሪዎቹ ካልሆነ ከአውሮፕላኑ ፈጣሪዎች እንደሚሆን አላጡትም። ጣት ወደነርሱ ሲቀሰር ደግሞ ሌላ ቁስል ይቀሰቅሳል፤ ኢንዶኒዢያ። ያን ቁስል መልሶ መነካካት የቦይንግን ስምና ዝና ጠራርጎ የሚወስድ ችግር ያስከትላል። ስለዚህ በቻሉት ሁሉ ነገሩን ከነገርሱ ማራቅ ነበረባቸው። ያን ዕለት ማለዳ ምን ሆነ? ከራሱ አልፎ ለአህጉሪቱ አየር መንገዶች በክፉ ጊዜ ደርሶላቸዋል። በዚህ ከፍታ ላይ እያለ ነበር ክፉው አጋጣሚ የተከሰተው። በማለዳ ዘመናዊውን ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ወደ ናይሮቢ አሰማራ። ብዙ ጊዜ ሙሉ በሚባል ደረጃ ተጓዦችን የሚያስተናግደው የናይሮቢው በረራ 149 መንገደኞችን አሳፍሮ ነበር። ተጨማሪ 8 የአውሮፕላኑ ሠራተኞችም ነበሩበት። የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ወደ ናይሮቢ ኬንያ ለመብረር እንዲያኮበኩብ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን መልካም ፈቃድ ያገኘው ከጠዋት 02 ሠዓት ከ37 ደቂቃ ነበር። አውሮፕላኑ ክንፉን ዘርግቶ ተንደርድሮ ተነሳ። ልክ ከአንድ ደቂቃና ከ10 ሰከንዶች በኋላ ከተለመደው የተለየ ሁኔታ እንዳጋጠመ በአብራሪዎቹ ታወቀ። ረዳት አብራሪው ለዋና አብራሪው ይህንኑ አሳወቀ። ዋና አብራሪውም ችግሩን ለማስወገድ በማለት አውሮፕላኑ በራሱ ሥርዓት እንዲበር ጥረት ማድረግ ጀመረ። አብራሪዎቹ የገጠማቸውን ችግር ለማስተካከል ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም እንዳሰቡት ሊሳካላቸው አልቻለም። ወዲያውኑ ረዳት አብራሪው ስላጋጠማቸው ነገር ለአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ሪፖርት አደረገ። ረዳት አብራሪው ለአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች አውሮፕላኑን የመቆጣጠር ችግር እንደገጠመው አሳወቁ። ብዙም ሳይቆዩ አውሮፕላኑ ከአብራሪዎቹ ቁጥጥር ውጪ እየሆነ መጣ። አፍንጫውን ወደ ምድር እያገደለ አስቸገረ። አብራሪዎቹ ይህንን ለማስተካከል በከፍተኛ ጥድፊያ ጥረት እያደረጉ ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር በመገናኘት 14ሺህ ጫማ ላይ መቆየት እንደሚሹ ገለጹ። አውሮፕላኑ ቀና ሊል አልቻለም። ጭራሽ አልታዘዝ አለ። የጀመሩት በረራ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ስላጋጠመው ወደ ተነሱበት ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ መመለስ እንደሚፈልጉ አሳወቁ። ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ወዲያውኑ ፍቃድ አገኙ። ይህ ሁሉ የሆነው በደቂቃዎች ልዩነት ነበር። አሁንም አብራሪዎቹ አውሮፕላኑ ካዘቀዘቀበት ከፍ ለማድረግ ጥረታቸው አልተቋረጠም፤ አውሮፕላኑ ግን በስሪቱ ግድፈት እንደሆነ በሚገመት መልኩ አሻገረኝ አለ። ይባስ ብሎ ቁልቁል መምዘገዘግ ጀመረ። በመጨረሻም አብራሪዎቹ ከበረራ ተቆጣጣሪዎች ጋር የነበራቸው ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ። የአቶ ተወልደ ትዝታ ከ150 በላይ ሰዎችን የያዘው የኢቲ302 የአውሮፕላን ሳይከሰከስ እንዳልቀረ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ስጋት ቢገባቸውም ለደቂቃዎች ተስፋ አልቆረጡም ነበረ። ከደቂቃዎች በኋላም የአሰቃቂው አደጋ መከሰት የማይሸሹት እውነት ሆነ። የአደጋውን መከሰት ቀድመው የሰሙት የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሰንበት ቅዳሴን እየታደሙ ነበር። "የአደጋውን መድረስ ዜና የሰማሁት ጧት ነው። በእርግጥም በጣም ክው አድርጎኛል። በጣም፤ እጅግ በጣም ነው ያሳዘንኩት" ሲሉ መጋቢት አንድ ቀን ጠዋት የተፈጠረባቸውን ስሜት ያስታውሳሉ። እሁድ ረፋድ ላይ የአደጋውን መከሰት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጽህፈት ቤት በማኅበራዊ ገጹ ላይ አረዳ። በደረሰው አደጋም ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም ሐዘኑን ገለጸ። ከዚህ በኋላ አደጋው የዓለም መገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ርእስ ሆነ፤ የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ብርክ ያዘው። ተመሳሳይ አውሮፕላን የገዛ ሐሳብ ገባው። ሊገዛ ያሰበ ቀብዴን መልሱልኝ ማለት ጀመረ። የቦይንግ ገበያ ምስቅልቅል ውስጥ ገባ። በተለይ ከዚህ አደጋ ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ የኢንዶኔዢያ ላየን ኤር አየር መንገድ አሰቃቂና በባህሪው ተመሳሳይ አደጋ አጋጥሞት እንደነበር ሲታወስ ነገሮች ወዴት እያመሩ እንደሆነ ግልጽ ነበር። ለአደጋው ምክንያት ተለያዩ መላ ምቶች ቢቀርቡም በአውሮፕላኑ ላይ ያለ ችግር ሊሆን እንደሚችል በመገለጹ ጥያቄዎች በአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ ላይ በረታ። ይህንንም ተከትሎ ሌላ አደጋን ለማስቀረት እጅግ ዘመናዊ እንደሆኑ የተነገረላቸው ቦይንግ 737 ማክስ 8 ስሪት አውሮፕላኖች ከበረራ ውጪ የማድረግ እርምጃን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ አየር መንገዶች ወሰዱ። በኢትዮጵያ አውሮፕላን ላይ የደረሰው አደጋ እጅግ የከፋ ስለነበረ አንድም ሰው ከአደጋው አልተረፈም። ከአዲስ አበባ በ40 ኪሎ ሜትሮች አካባቢ ርቀት ላይ ከምትገኘው ቱሉ ፈራ ሜዳ ላይ የወደቀውን የአውሮፕላኑን ስብርባሪና የአደጋውን ሰለባዎች አካል ለማግኘት የቀናት ቁፋሮ አስፈልጎ ነበር። ለሟች ቤተሰቦች ሐዘኑ ድርብ ሆነ። ከአደጋው ጋር በተያያዘ አንዳንድ ወገኖች የአብራሪዎች ችግር አድርገው ለማቅረብ ቢሞክሩም የአደጋው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ግን አብራሪዎቹ ክስተቱን ለማስቀረት መጣራቸውንና በአውሮፕላኑ ላይ የተገጠመው የመቆጣጠሪያ ሥርዓት ለአደጋው ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አመልክቶ ነበር። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማሪያምም ከመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ጋር በተያያዘ "ፓይለቶቹ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው የሚጠበቅባቸውን ተገቢ እርምጃ በመውሰድ ያላቸውን ከፍ ያለ ሙያዊ ብቃት በማስመስከራቸው" አየር መንገዱ እንደሚኮራባቸው መስክረዋል። አደጋው በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ሕይወት ከማሳጣቱ ባሻገር ዘመናዊ የተባለውን አውሮፕላን ባመረተው ቦይንግ ኩባንያ ላይ ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎችን አስከትሏል። በኩባንያው ላይ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ዋና ሥራ አስፈጻሚውም ከሥራቸው ተባረዋል። ተመሳሳዩን አውሮፕላን እንዲያመርትላቸው ያዘዙ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶችም ትዕዛዛቸውን ከመሰረዝ አልፈው ሥራ ላይ የነበሩትን ከበረራ ውጪ አደረጓቸው። በዚህም ባለዝናው የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ በወራት ጊዜ ውስጥ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ኪሳራ አጋጠመው። ጉዳዩም ዛሬም ድረስ መቋጫ አላገኘም። ጥቁሩ ሳጥን፤ በአውሮፕላኖች ላይ የሚደርስ አደጋን ለሚደረግ ምርመራ ጠቃሚ መረጃን የሚይዝ ኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ነው።
news-52932150
https://www.bbc.com/amharic/news-52932150
ለጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ደማቅ ሽኝት ተደረገ
በነጭ ፖሊስ በግፍ ለተገደለው ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ደማቅ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ተደርጎለታል። ስመ ጥር የጥቁር መብት ተሟጋቾች በሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር አድርገዋል።
ለጆርጅ ፍሎይድ በተደረገው መታሰቢያ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገኝተዋል የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰብ ጠበቃ "ደንበኛዬን ለሞት ያበቃው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ነው ይላሉ፤ በዘረኝነት ወረርሽኝ መሞቱን ማን በነገራቸው. . ." ሲል ስሜታዊ ንግግር አሰምቷል። በሟች ጆርጅ ፍሎይድ የሽኝትና መታሰቢያው ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙ ሁሉ ተነስተው እንዲቆሙና ለ8 ደቂቃ ከ46 ሴኮንዶች የሕሊና ጸሎት እንዲያደርጉ የተደረገ ሲሆን፤ ይህም ነጩ የፖሊስ ባልደረባ ዴሪክ ሟች ፍሎይድ አንገት ላይ በጉልበቱ ቆሞ ትንፋሹን እስኪያጣ የቆየበትን ጊዜን ለመዘከር የተደረገ ነበር። የጆርጅ ፍሎይድ የሕይወት ታሪክም በታዋቂው የጥቁር መብት አቀንቃኝ ሬቭ አል ሻርፐን አማካኝነት ተነቧል። አል ሻርፐን ባደረጉት ንግግር በመላው አሜሪካ የምትገኙ ጥቁር ወንድሞቼ፣ አሁን ሁላችንም "ከአንገቴ ጉልበትህን አንሳልኝ" የምንለበት ሰዓት ላይ ደርሰናል ብለዋል። የጆርጅ ፍሎይድ የመጨረሻ ሰዓት ትንቅንቅ በቪዲዮ ተቀርጾ ማኅበራዊ ድር አምባው በከፍተኛ ፍጥነት ከተጋራው በኋላ በአሜሪካ አብዛኞቹ ግዛቶች ለቀናት የዘለቀ ተቃውሞን ቀስቅሶ ቆይቷል። ተቃውሞቹን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስጋትም ሆነ የሰዓት እላፊ ገደብ ሊያቆማቸው አልቻለም ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሽኝት ሥነ ሥርዓቱ ከሚካሄድበት ቅርብ ርቀት በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ላይ ተባባሪነት አሳይተዋል የተባሉት ሦስት ተጨማሪ የፖሊስ ባልደረቦች ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ተመስርቶባቸዋል። የዋስ መብታቸው እንዲከበር 1 ሚሊዮን ዶላር እንዲያቀርቡ የተጠየቁ ሲሆን ይህም የገንዘብ መጠን የጦር መሣሪያዎቻቸውን በፈቃዳቸው ከመለሱና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን ካሟሉ ወደ 750 ሺህ ዶላር ዝቅ ሊል እንደሚችል ተነግሯቸዋል። በጆርጅ ፍሎይድ አንገት ላይ ለደቂቃዎች በመቆም ሕይወቱ እንዲያልፍ አድርጓል በሚል የተጠረጠረው የቀድሞው ፖሊስ ባልደረባ ዴሪክ ቾቪን ሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። በሽኝት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰብ አባላት፣ እውቁ የመብት ታጋይ ጄሴ ልዊስ ጃክሰን፣ የሜኔሶታ ገዢ ቲም ዋዝ፣ የሚኒያፖሊስ ከንቲባ ጃኮብ ፍሬይ እና ሌሎች በርካታ ሰዎች ታድመዋል። የጆርጅ ፍሎይድ ወንድም ፍሎናይዝ ፍሎይድ በበኩሉ ባደረገው ንግግር የልጅነት አስተዳደጋቸው ምን ይመስል እንደነበር አስታውሷል። "ድሆች ከመሆናችን የተነሳ ልብሳችንን በሳፋ አጥበን በምድጃ እሳት ሙቀት ነበር የምናደርቀው…" ሲል በስሜት የታጀበ ንግግር አድርጓል። የወንድሜ ሕይወቱ ሳይደምቅ ሞቱ በዚህ ደረጃ መድመቁ ይደንቀኛል ሲልም ተናግሯል። የመብት ታጋዩ አል ሻርፕተን በበከላቸው ለፍሎይድ ሞት ተጠያቂ መኖር አለበት ሲል አሳስቧል። "የፍትህ ሥርዓቱ መልክ እስኪይዝና እኩልነት እስኪያንጸባርቅ ድረስ ዝም አንልም" ሲል ተቃውሞው ወደፊትም እንደሚቀጥል ጥቆማ ሰጥተዋል። "የፍሎይድ ሕይወት የመላው ጥቁሮችን ሕይወት ይወክላል፤ ሞቱም ሕይወቱም የእኛው ሞትና ሕይወት ነው" ብለዋል። "በእርሱ የደረሰው ነገር በሁሉም ጥቁር አሜሪካዊያን እየደረሰ ያለው ነው፤ በትምህርት፣ በጤና፣ በፍትህ ሥርዓት መበደል ፍሎይድ የደረሰበት ብቻ ሳይሆን የእኛም ሕይወት ነው፤ አሁን ጊዜው 'አንተ ነጭ ጉልበትክን ከአንገቴ አንሳልኝ' የምንልበት ነው" ብለዋል። ለጆርጅ ፍሎይድ የሚደረገው የሽኝት ሥነ ሥርዓት በትወልድ ቦታው ኖርዝ ካሮላይና ቅዳሜ፣ እንዲሁም ባደገበት ሂውስተን ደግሞ ሰኞ ይቀጥላል።
news-56021640
https://www.bbc.com/amharic/news-56021640
'በትግራይ የተመለከትኩት ነገር በእጅጉ አሳስቦኛል'' የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር
የዓለም ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማህበራት ፌደሬሽን በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በግጭቱ ተጎጂ ለሆኑት ተጨማሪ እርዳታ እንዲደርስ ጥሪ አቅርቧል።
የፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት ፍራንሴስኮ ሮካ በጉብኝታቸው ወቅት የተመለከቱት ነገር በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ጦርነቱን ተከትሎ ለንጹሀን ዜጎች የሚደረገውን እርዳታ የሚያስተባብሩ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ እንዳይንቀሳቀሱ ከልከሏል የሚል ክሰ ሲቀርብበት ነበር። መንግሥት በበኩሉ እርዳታ ወደ ክልሉ እንዲገባ ከፍተኛ ትብብር እንደሚያደርግ አስታውቋል። የትግራይ ክልል ዋና ከተማን የጎበኙት ፕሬዝዳንቷ በጦርነቱ ምክንያት በደረሰው ጉዳት ከፍተኛ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ህጻናት፣ ሴቶችና አረጋውያን መሆናቸውን አስታውቀዋል። አክለውም ሆስፒታሎች አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸው መሰረታዊ የህክምና መስጫ ቁሳቁሶች እንኳን እንደሌላቸው ገልጸው በተጨማሪ ደግሞ የምግብ እጥረት አካባቢውን እንደሚያሰጋውም አስታውቀዋል። የዓለም ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማህበራት ፌደሬሽን ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ላይ በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ግጭት በርካታ ንጹሀን ዜጎችን ተጋላጭ እንዳደረገና ችግሩ በጎረቤት አገራትም ተጽዕኖ እንደፈጠረ መግለጹ የሚታወስ ነው። ሌላው ቀርቶ ግጭቱ ከመጀመሩ በፊት እንኳን አካባቢው በምግብ እጥረት፣ የበረሃ አንበጣ መንጋ ወረራ እና ኮቪድ-19 ወረርሺኝ ሲጠቃ ነበር ብሏል ድርጅቱ። በሚቀጥሉት ሳምታት ውስጥ በተለይ የምግብ እርዳታ ወደ ክልሉ በቶሎ የማይገባ ከሆነ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለከፍተኛ ረሃብ ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ ድርጅቱ አሳስቧል። መንግሥት በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴ መፍቀድ የማይፈልገው ክልሉን ገና ሙሉ በሙሉ ባለመቆጣጠሩ ምክንያት እንደሆነና ምግብ በበቂ ሁኔታ እንዳይገባ የሚያደርገውም በሽሽት ላይ የሚገኙት መሪዎች እጃቸውን እንዲሰጡ ለማድረግ እንደሆነ አንዳንድ ተንታኞች ይገልጻሉ። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀው መቃቃርና አለመግባባት ተካሮ የህወሓት ኃይሎች የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የፌደራሉን ጦር ወደ ትግራይ ማዝመታቸው ይታወሳል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በክልሉ ያለውን የሰብአዊ ሁኔታ "የከፋ" ሲል ገልጾታል። በተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰውና የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል እንደሚለው በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል። የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ የተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶች ህዝቡን መደረስ እንዳልቻሉም ሲናገሩና መንግሥት እንዲያመቻች ሲጠይቁም ተሰምተዋል። በክልሉ ውስጥ ያለው ሁኔታ አስከፊ እንደሆነና "በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ምክንያት ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ" አንድ የመንግሥት ባለስልጣን መናገራቸውን ከእርዳታ ሠራተኞች ጋር ከተደረገ ስብሰባ ላይ ሾልኮ የወጣ ማስታወሻ ላይ የሰፈረ ጽሁፍ ማመልከቱ የሚታወስ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ጦርነት በተካሄደባቸው የትግራይ ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ደኅንነትና ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና የሰብአዊ ቀውስን ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገልጿል። ከሰሞኑም እንዲሁ በክልሉ ምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችና የሕክም አቅርቦቶች የሰብዓዊ ድጋፍ ለ1.8 ሚሊዮን ሰዎች መድረሱን የሠላም ሚኒስቴር ገልጿል። ሚኒስቴሩ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሰዎች እየቀረበ ያለውን እርዳታ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ ከተጠቀሱት ሰዎች በተጨማሪ በክልሉ 2.5 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን አመልክቷል።
news-53075008
https://www.bbc.com/amharic/news-53075008
የኮሮናቫይረስ ጽኑ ህሙማንን ህይወት ይታደጋል የተባለውን መድኃኒት የዓለም ጤና ድርጅት ተቀበለው
በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ዴክሳሜታሶን በተባለው መድኃኒት ላይ የተደረገው ሙከራና ያስገኘውን ውጤት በበጎ እንደሚመለከተው የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
በሙከራው ይህ መድኃኒት በኮሮናቫይረስ በጽኑ ከታመሙ ሰዎች የአንድ ሦስተኛውን ሕይወት መታደግ እንደሚችል እና በወረርሽኙ ሰበብ ኦክስጂን በሚያስፈልጋቸው ሰዎች ላይ የሚያጋጥምን ሞት በአንድ አምስተኛ ሊቀንስ እንደሚችል ለድርጅቱ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ግኝት አመልክቷል። ድርጅቱ እንዳለው የዴክሳሜታሶን ጠቀሜታ በኮቪድ-19 በጸና በታመሙ ሰዎች ላይ እንጂ ቀለል ያለ ህመም ባለቸው ላይ እንዳልሆነ አመልክቷል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም እንዳሉት "ይህ ኦክስጂንና የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ ለሚያስፈልጋቸው የኮሮናቫይረስ ህሙማን ላይ የሚያጋጥምን ሞት የሚቀንስ የመጀመሪያው መድኃኒት ነው" ብለዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ይህም ታላቅ ዜና መሆኑን ጠቅሰው የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥትንና ይህንን ህይወትን የሚታደግ የመጀመሪያ ግኝት ላይ በመሳተፍ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ለኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ፣ ለሆስፒታሎችና ለህሙማን የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ዴክሳሜታሶን ከ1960ዎቹ (እአአ) ጀምሮ በተለያዩ ህመሞች ምክንያት የሚያጋጥሙ እብጠቶችን ለመቀነስና የተወሰኑ አይነት የካንስር ህመሞችን ለማከም ጥቅም ሲውል ቆይቷል። በርካሽ ዋጋና በስፋት የሚገኘው ዴክሳሜታሶን በኮቪድ-19 በጽኑ የታመሙ ሰዎች ሕይወት አድን መሆኑን የዩናይትድ ኪንግደም ባለሙያዎች ገለፁ። መድኃኒቱን በአነስተኛ መጠን በመስጠት ማከም ይህንን ገዳይ ቫይረስ በመዋጋት ረገድ ወሳኝ መሆኑን ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። ተመራማሪዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንደተከሰተ በዩናይትድ ኪንግደም መድኃኒቱ በስፋት ቢገኝ ኖሮ እስካሁን ድረስ የ5000 ሰዎችን ሕይወት ማዳን ይቻል ነበር ብለዋል። ምክንያታቸው ደግሞ ርካሽ መሆኑ ሲሆን ከፍተኛ የኮቪድ-19 ሕሙማን ባሏቸው ደሃ አገራት ውስጥም ቢሆን በርካታ ጥቅም እንዳለው ያስረዳሉ። ዴክሳሜታሶን ለጽኑ ሕሙማን በደም ስር የሚሰጥ ሲሆን፣ ሕመማቸው ላልፀናባቸው ደግሞ በክኒን መልክ እንዲወስዱት ይደረጋል ተብሏል። መድኃኒቱ ከ1977 ጀምሮ በተለያየ መልኩ ተዘጋጅቶ አስፈላጊ ከተባሉ የዓለም ጤና ድርጅት የመድኃኒቶች ዝርዝር ውስጥ የገባ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከባለቤትነት መብት ነጻ ከመሆኑ በተጨማሪ በብዙ አገራት ውስጥ በቀላሉ ይገኛል ተብለወል። ተመራማሪዎች የመጀመሪያ ደረጃ ሙከራ ውጤታቸውን ለዓለም ጤና ድርጅት ያሳውቀው በቀጣይ ቀናትን ስለዴክሳሜታሶን ያለው ሙሉ መረጃ ተተንትኖ እንደሚቀርብ እየተጠበቀ ነው። በቀጣይም ድርጅቱ ስለመድኃኒቱ ተጨማሪ መረጃዎችን እንደሚያቀርብና ስለመድኃኒቱ አጠቃቀም ያለው መመሪያ ላይ መሻሻል ያደርጋል ተብሏል።
news-52597598
https://www.bbc.com/amharic/news-52597598
የኢትዮጵያ ሠራዊት የኬንያን አውሮፕላን በስህተት መትቶ መጣሉን አመነ
የኢትዮጵያ ሠራዊት ሶማሊያ ውስጥ የኬንያን የጭነት አውሮፕላን መትቶ መጣሉን በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል - አሚሶም አስታወቀ።
የአሚሶም ኃይል አባል አይደለም የተባለው የኢትዮጵያ ሠራዊት ሶማሊያ ውስጥ አውሮፕላኑን መትቶ የጣለው ከአጥፍቶ ጠፊ ተልዕኮ ጋር ተመሳስሎበት ነው ተብሏል። አምስት ሰዎችን ጭኖ ሲበር የነበረ አውሮፕላን በሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ግዛት የተመታው ሰኞ ሚያዚያ 26/2012 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ነበር። አውሮፕላኑ ባርዳሌ በምትባል ከተማ በሚገኝ አየር ማረፊያ አቅራቢያ የተመታ ሲሆን የሁሉም ተሳፋሪዎች ሕይወት አልፏል። አውሮፕላኑ ተመቶ የወደቀበት ቦታን ተቆጣጥሮ የሚገኘው የአሚሶም ሴክተር ሦስት ኃይል ኮማንደር የሆኑት ብርጋዲዬር ጀነራል አለሙ አየነ እንዳሉት ጦራቸው ስለ በረራው ቀድሞ መረጃ እንዳልነበረው እና አውሮፕላኑ ለማረፍ የሄደበት አቅጣጫ አጠራጣሪ ስለነበር ተመትቷል ብለዋል። በአካባቢው በሚገኘው አየር ማረፊያ አንድ አውሮፕላን ለማረፍ የሚሄድበት አቅጣጫ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ሲሆን፤ ይህ በኢትዮጵያ ጦር ተመትቶ የወደቀው አውሮፕላን ግን ለማረፍ ሲበር የነበረው በተቃራኒ አቅጣጫ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ነበር ተብሏል። ብርጋዴየር ጀነራል አለሙ አየነ በባርዳሌ የጦር ካምፕ ጥበቃ ላይ ያለው ጦራቸው አውሮፕላኑን መትቶ የጣለብትን ሦስት ምክንያቶች ገልጸዋል። አውሮፕላኑ ወደ ባርዳሌ ከተማ እንደሚበር መረጃ እንዳልነበራቸው፣ አውሮፕላኑ ከተለመደው ውጪ ወደ ምድር ቀርቦ እየበረረ እንደነበር እንዲሁም በካምፑ የሚገኘው ጦር አውሮፕላኑ ከተለመደው ውጪ ዝቅ ብሎ የሚበረው የአጥፍቶ መጥፋት ዒላማ እየፈለገ እንደሆነ በመረዳታቸው መትተው መጣላቸውን አስታውቀዋል። እንደ አሚሶም መግለጫ ከሆነ አውሮፕላኑ ለማረፍ ያደረገው ጥረት ባለመሳካቱ ለሁለተኛ ጊዜ ለማረፍ ሙከራ ሲያደርግ መመታቱ ተጠቁሟል። የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ-አሚሶም እንዳለው አውሮፕላኑ ምንም እንኳ አየር ላይ ሳለ በኢትዮጵያ ሠራዊት ቢመታም፤ ለማረፍ በሚያደርገው ጥረት በጣም ወደ ምድር ተጠግቶ እየበረረ ስለነበረ ጎማዎቹን ለመዘርጋት በቂ ጊዜ ስለማይኖረው ያለችግር የማረፍ እድል አልነበረው ብሏል። አሚሶም በመረጃ ክፍተት አውሮፕላኑ ተመቶ ወድቋል ካለ በኋላ አውሮፕላኑ ከአሚሶም ውጪ ባሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች መመታቱን አስታውሷል። አሚሶም በመግለጫው በጉዳዩ ላይ ዝርዝር እውነታውን ለማወቅ የኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ መንግሥታት በጣምራ በአደጋው ዙሪያ ምርመራ እንዲያደርጉ ጠይቋል። የሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ምክትል የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ሐሳን ሁሴን ለቢቢሲ እንደገለጹት ከአምስቱ ሟቾቹ መካከል ሁለቱ ሶማሊያውያን ሲሆኑ ሦስቱ ደግሞ ኬንያውያን ናቸው። ንብረትነቱ የአፍሪካን ኤክስፕረስ ኤርዌይስ የሆነው አውሮፕላን አደጋ እንዳጋጠመው በተነገረበት ወቅት በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በኢትዮጵያ ጦር ተመትቶ መውደቁን ገልጸው የነበረ ቢሆንም፤ ይህ በአሚሶም፣ በኢትዮጵያ፣ በኬንያ እና በሶማሊያ መንግሥታት ሳይረጋገጥ ቆይቷል። የአፍሪካን ኤክስፕረስ ኤርዌይስ የኬንያ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሲሆን ዋና መቀመጫው በመዲናዋ ናይሮቢ ነው። አውሮፕላኑ ንብረትነቱ የአፍሪካን ኤክስፕረስ ኤርዌይስ የተባለ የኬንያ አቪዬሽን ድርጅት እንደሆነና በወቅቱ የሰብዓዊ እርዳታ ቁሳቁሶች የሆኑ መድሃኒቶችንና የወባ መከላከያ አጎበር ጭኖ እንደነበር ተገልጿል።
news-52830176
https://www.bbc.com/amharic/news-52830176
በኮሮናቫይረስ ምክንያት 1600 በላይ የአእምሮ ህሙማን በስህተት ከሆስፒታል ተለቀዋል ተባለ
በሰሜናዊ ዌልስ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ለ1700 የተጠጉ የአእምሮ ጤና እክል ያለባቸው ታማሚዎች በስህተት ከማዕከላት እንዲወጡ መደረጉ ተገልጿል።
ባሳለፍነው ሳምንት ‘ቤትሲ ካድዋላድር’ የጤና ቦርድ ወረርሽኙ ቀለል ሲል ሰዎች እንደ አዲስ ህክምናቸውን እንዲጀምሩ አሳስቧል። ቦርዱ በግምቴ መሰረት ከ 200 እስከ 300 የሚደርሱ ታማሚዎች ተለቀዋል ቢልም ትክክለኛው ቁጥር ግን 1694 አካባቢ መሆኑ ተገልጿል። በዚህም ምክንያት የጤና ቦርዱ ይቅርታ በመጠየቅ ታማሚዎችን ማፈላለግ ጀምሯል። የቦርዱ ጊዜያዊ ስራ አስፈጻሚ ሲሞን ዲን በበኩላቸው የአእምሮ ታማሚዎቹን ከማዕከላቱ እንዱወጡ ማድረጉ ተገቢ አልነበረም፤ ሊፈጠር የማይገባው ስህተትም ነው ብለዋል። ‘’ይህን ያክል ቁጥር ያላቸው ታማሚዎች የመውጫ ጊዜያቸው ሳይደርስና ህክምናቸውን ሙሉ በሙሉ ሳይጨርሱ እንዲወጡ መደረጋቸው በጣም ያሳዝናል።‘’ አክለውም ‘’ሁሉም ታማሚዎች በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ከያሉበት ተፈልገው ወደ ቀድሞ ህክምናቸው እንዲመለሱ ይደረጋል መባሉ አስደስቶኛል። ነገር ግን እንዲህ አይነት ትልቅ ስህተት ያለበት ውሳኔ በቦርዱ እንዴት ሊፈጸም እንደቻለ አልገባኝም’’ ብለዋል። ጌዜያዊ ስራ አስፈጻሚው ክስተቱን ተቀባይነት የሌለው ነው ካሉ በኋላ የጤና ስርዓቱን ለመደገፍ ፈጣን የሆነ መልሶ የመቋቋም ስራ መሰራት አለበት ብለዋል። የዌልስ መንግስት በበኩሉ ከመጀመሪያ ደረጃ የአእምሮ ጤና ማዕከለት ታማሚዎች ያለጊዜያቸው መለቀቃቸውን ሰምተናል፤ በዚህ ከባድ ወረረርሽኝ ወቅት መከሰቱ ደግሞ አሳሳቢ ያደርገዋል ብሏል። አንድ የመሥግስት ቃል አቀባይ እንዳሉት ሁሉም ታማሚዎች ወዳሉበት አካባቢ ድረስ በመሄድ ተፈልገው ወደ ጤና ማዕከላቱ እንዲመሱ ይደረጋል።
news-47222477
https://www.bbc.com/amharic/news-47222477
ሜክሲኳዊው የአደንዛዥ ዕፅ ነጋዴው ዮአኪን 'ኤል ቻፖ' ጉዝማን በአሜሪካ ጥፋተኛ ተባለ
ሜክሲካዊው የዕፅ ነጋዴ ዮአኪን ''ኤል ቻፖ'' ጉዝማን በኒው ዮርክ ፌደራል ፍርድ ቤት በቀረቡበት 10 ክሶች በሙሉ ጥፋተኛ ተባለ።
የ61 ዓመቱ ''ኤል ቻፖ'' በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው ዮአኪን ጉዝማን ኮኬይን እና ሄሮይን በማስራጨት፣ በህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ባለቤትነት እና በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ክሶች ቀርበውበታል። የፍርድ ቤቱን ውሳኔ የሚጠባበቀው ኤል ቻፖ የተቀረውን እድሜውን በእስር ሊያሳልፍ እንደሚችል ተገምቷል። ኤል ቻፖ ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግላቸው ሁለት የሜክሲኮ እስር ቤቶች ማምለጥ ችሎ ነበር። • ኢትዮጵያዊቷ የዕፅ ነጋዴው ኤል ቻፖን ጉዳይ ለመዳኘት ተመረጠች በድጋሚ ታህሣሥ 2008 በቁጥጥር ሥር የዋለው ኤል ቻፖ 2009 ላይ ለአሜሪካ ተላልፎ ተሰጥቷል። ኤል ቻፖ በብዛት ወደ አሜሪካ ለሚገቡ ዕፆች ተጠያቂ ሆኖዋል። ሲቢኤስ ኒውስ እንደዘገበው ከሆነ ጥቁር ጃኬት እና ክራቫት አስሮ ከፍርድ ቤቱ የተገኘው ኤል ቻፖ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሲተላለፍበት ምንም አይነት የስሜት መለዋወጥ አላሳየም። ከፍርድ ቤቱ በፖሊስ ኃይል ታጅቦ ሲወጣ የፍርድ ሂደቱን ስትከታተል ለነበረችው የ29 ዓመቷ ባለቤቱ ኤማ ኮርኔል የቅንጡ ሰላምታ ሰጥቷታል። የጉዝማን ጠበቆች ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል። ኤል ቻፖ ጉዝማን ማነው? "ኤል ቻፖ'' ማለት ''አጭሩ'' እንደማለት ሲሆን በሰሜናዊ ሜክሲኮ ሲናሎአ የተሰኘ የዕፅ አዘዋዋሪ ቡድን መሪ ነበረ። ኤል ቻፖ የሚመራው ቡድን ወደ አሜሪካ ለሚላከው ዕፅ ትልቁን ድርሻ ይዞ ነበር። እአአ 2009 ፎርብስ ኤል ቻፖ ጉዝማን የተጣራ 1ቢሊዮን ዶላር ያስመዘገበ ከበርቴ ነው በማለት የዓለማችን 701ኛው ሲል የሃብታሞች ዝርዝር ውስጥ አካቶታል። የፍርድ ሂደቱ ተደብቆ የቆየውን የኤል ቻፖ ጉዝማን ህይወትን አደባባይ ያወጣ እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ። በፍርድ ሂደቱ ላይ የቀድሞ የቅርብ አጋሩ የነበሩ ሁሉ መስክረውበታል። ከተሰጡበት ምስክርነቶች አንዳንዶቹ ሰዎችን በድንጋጤ ጭው ያደረጉ ነበሩ። ዕድሜያቸው ለጋ የሆኑና እስከ 13 ዓመት የሚደርሱ ሴቶችን ከመድፈሩ በፊት አደንዛዥ ዕፅ እንዲጠቀሙ ያደርግ ነበር ተብሏል። ጉዝማን ለቀድሞው የሜክሲኮ ርዕሰ ብሔር ኤንሪክ ፔና ኒቶ በ2012 ስልጠን ከያዙ በኋላ እርሱ ላይ የሚደረገው ክትትል እንዲቆም በመጠየቅ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር ጉቦ መክፈሉም የተሰማው በዚያው ችሎት ላይ ነው። ርዕሰ ብሔሩ ግን ይህ ውንጀላ እውነትነት የለውም ሲሉ አስተባብለዋል። ገድሎ ያቃጠላቸው የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴ ተፎካካሪዎች እንዳሉ ከዘመዶቹ መካከልም የገደላቸው እንዳሉ ተገምቷል። ችሎቱ ኤል ቻፖ በ2015 በሜክሲኮ እጅግ ጥብቅ ከሆነው እስር ቤት እንዴት እንዳመለጠም በዝርዝር አድምጧል። ልጁ በእስር ቤቱ አቅራቢያ የሚገኝ ቤት እንደተከራየና ጂፒኤስ ያለው ሰዓት ወደ እስር ቤቱ በድብቅ ማስገባቱ ተመስክሯል። በሚስቱ እና በቅምጦቹ ላይ ለመሰለል በስልኩ ላይ ሶፍትዌር ይጠቀም እንደነበርም ተመስክሮ፤ ኤፍ ቢ አይ የተለዋወጣቸውን የፅሑፍ እንዲያቀርብ ተደርጓል። በአንድ የፅሁፍ መልዕክቱ ላይም ከነበረበት ቤት አሜሪካዊያንና ሜክሲኳዊያን ከከፈቱበት ድንገተኛ ዘመቻ እንዴት እንዳመለጠ የሚገልጽና ልብስ፣ ጫማ እና ጥቁር ሪዝ እንዲመጣለት የጠየቀበት መልዕክቱም ተነቧል። ጉዝማን በአሜሪካ የፍትህ አደባባይ ለፍርድ ከቀረቡ የሜክሲኮ የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴዎች መካከል ትልቁ ነው።
news-53550064
https://www.bbc.com/amharic/news-53550064
ሱዳን ወደ ዳርፉር ተጨማሪ ወታደሮች ልትልክ ነው
ሱዳን ተጨማሪ ወታደሮችን መረጋጋት ወደ ራቀውና በቅርቡ ግጭት ወደተቀሰቀሰበት የዳርፉር ግዛት ልትልክ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ አስታወቁ።
እንደ ተባበሩት መንግሥታት መረጃ ከሆነ በዳርፉር ግጭት 300,000 ያህል ሱዳናውያን ሞተዋል ሁለት ሚሊዮን ደግሞ ተፈናቅለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደሮቹ በዚህ የእርሻ ወቅት ዜጎች ተረጋግተው ግብርናቸው ላይ እንዲያተኩሩ ጥበቃ ያደርጋሉ ብለዋል። ቅዳሜ እለት ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች 60 ሰዎችን የገደሉ ሲሆን፣ ከዚያ በፊት ደግሞ 20 ሰዎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል። እንደ ተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) መረጃ ከሆነ በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ የገበያ ሥፍራዎችና ሱቆች ተዘርፈዋል። "በዳርፉር ግዛት የሚታየው የግጭት መስፋፋት ዜጎች እርሻቸውን ትተው እንዲሰደዱ፣ ለህይወትና ለንብረት መጥፋት እንዲሁም ለሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት መጨመር ሰበብ ሆኗል" ይላል የድርጅቱ መግለጫ። እስካሁን ድረስ የትኛውም ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን አልወሰደም። ዳርፉር ላለፉት ሁለት አስርታት በግጭት ስትታመስ የነበረች ሲሆን፤ ውጊያው ይካሄድ የነበረው ደግሞ ለቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር ታማኝ በሆኑ ኃይሎችና በአማፂያን መካከል ነበር። እንደ ተባበሩት መንግሥታት መረጃ ከሆነ በዳርፉር ግጭት 300,000 ያህል ሱዳናውያን ሞተዋል ሁለት ሚሊዮን ደግሞ ተፈናቅለዋል። አል በሽር በዳርፉር ለፈፀሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ይፈለጋሉ። የ76 ዓመቱ አልበሽር ባለፈው ሳምንት ካርቱም በሚገኝ ፍርድ ቤት ቀርበው ወደ ሥልጣን በመጡበት የመፈንቅለ መንግሥት ጉዳይ ተከስሰዋል። ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ሞት ይጠብቃቸዋል ተብሏል። የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት አል በሽር በሙስናም ተከስሰው ጉዳያቸው እየታየ ይገኛል።
news-45243819
https://www.bbc.com/amharic/news-45243819
ታላቁ ዲፕሎማት ኮፊ አናን ሲታወሱ
በ80 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ኮፊ አናን ለዘጠኝ አመታት ያህል በአለም ትልቁን አለም አቀፍ የዲፕሎማሲ አካል የተባበሩት መንግሥታትን መርተዋል።
በትልልቅ ክስተቶች በታጀበው እነዚህ አመታት በአሜሪካ ላይ 9/11 ተብሎ የሚታወቀው የሽብር ጥቃት እንዲሁም በአሜሪካ የሚመራው ጦር ኢራቅን ሲወር አመራር ላይ ነበሩ። በተለይም በመጨረሻው የስልጣን ዘመናቸው ወቅት በ21ኛው ክፍለ ዘመን አሰቃቂ የሚባሉ እንደ ሶሪያ የርስ በርስ ጦርነት ቀውሶችን ማስማማት የሳቸው ኃላፊነት ነበር። በጄኔቫ የቢቢሲ የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርተር ኢሞጅን ፎክስ ታላቁን ዲፕሎማት እንዲህ ታስታውሳቸዋለች። •በኢትዮጵያ የመንጋ ፍትህ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ነው •ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ባህርዳር ሊያቀኑ ነው ተባለ •ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ሽልማት ታጭተዋል? በመፅሐፍ መደርደሪያየ ላይ "እኛ ህዝቦች፡ የተባበሩት መንግሥት ለ21ኛው ክፍለ ዘመን " (ዊ ዘ ፒፕልስ ኦፍ ዩኤን ፎር ዘ ትዌንቲ ፈርስት ሴንቸሪ) የሚል መፅሐፍ አለ። መፅሐፉ ኮፊ አናን የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ በነበሩበት ወቅት በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች እንደ የአየር ፀባይ ለውጥ፣ ሰላም ማስከበር፣ ኤች አይ ቪ ኤድስና ዘር ጭፍጨፋን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ያደረጓቸውን ንግግሮች ስብስብ ነው። ትልልቅ ችግሮችን ለመፍታት የመንግሥታት መማክርት አካል አስፈላጊነትን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ላይ የሰላ ትችት የሚያቀርቡ አካላት በራሳቸው የተባበሩት መንግሥታት ባይኖር ኖሮ "እኛ መፍጠር እንደሚያስፈልገን" የሚያትቱ ፅሁፎችንም አካቷል። ከዚህ ሁሉ በላይ ይህንን መፅሀፍ የምወደው ራሳቸው ኮፊ አናን ስለሰጡኝ ነው። ከአራት አመት በፊት በጄኔቫ የተባበሩት መንግሥታት መቀመጫ ዋና ፀሐፊነታቸው ሚና ላይ ያጠነጠነ ውይይትን ተሳትፈው ከወጡ በኋላ ነው የሰጡኝ። በተባበሩት መንግሥታት መቀመጫ ጄኔቫ የተለያዩ ውይይቶች ይደረጋሉ፤ የሚመጡ ሰዎችም ቁጥር የሚያስከፋ አይደለም። በዛን ቀን ግን መቶዎችን የሚይዘው አዳራሽ ሞልቶ ብዙዎች ወደ አዳራሹ ለመግባት ውጭ ላይ ተሰልፈው ነበር። ምንም እንኳን አንዳንድ ጨለምተኛ ሐሳብ ያላቸው ስለተባበሩት መንግሥታት መፅሀፍን ለማስተዋወቅ በዛው በተባበሩት መንግሥታት አዳራሽ ውስጥ ከማድረግ በላይ ሌላ ምን አለ የሚሉ አሉ። ልክ ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን የመፅሐፉ ሽያጭ ገቢ ሙሉ በሙሉ የተባበሩት መንግሥታት ኤችአይ ኤድስን ለመዋጋት በሚያደርገው ፕሮግራም እንዲውል ነው። የዛን ቀንም የነበረው ውይይትም በዚሁ ላይ ያተኮረ ነበር። መልካም ስብዕና በአለማችን ላይ ተጋላጭ ለሆኑ ህዘቦች የሚያሳዩት የቸርነትና መንፈስና ፅናትን ብዙዎች ኮፊ አናን የሚያስታውሱበት ሁኔታ ይመስለኛል። ዋና ፀሐፊም በነበሩበት ወቅት ከሳቸው በፊት ከነበሩም ሆነ ከሳቸው በኋላ ከነበሩ ኃላፊዎች በተለየ ወደ ጄኔቫ ይመላለሱ ነበር። የፖለቲካው ተፅእኖም ሆነ ኃይል ተከማችቶ የሚገኘው በኒውዮርክ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጉዳዮች አለም አቀፍ ግጭቶችን ለመፍታት ክፍተት የሚታይበትም ለዚህ ነው። ኮፊ አናን በተለየ መልኩ በጄኔቫ የሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶችን ድጋፍ መለገስና ትኩረት ያላገኙ ስራዎቻቸውንም ትኩረት እንዲያገኙ ማድረግንም ስራ ይሰሩ ነበር። በተቻላቸው መጠን ለሚዲያውም ጊዜ ይሰጡ ነበር። ትህትናን የተሞሉና የጓደኛም ስሜትን የተሞሉ ናቸው። ጥያቄን በተአምር አይሸሹም ለምሳሌም ያህል ለተባበሩት መንግሥታት የሚዲያ አካል እንደተናገሩት የአሜሪካና የእንግሊዝ ጥምር ኃይል የኢራቅን ወረራ ህገ-ወጥ ማለታቸው የሚታወስ ነው። መልካም ስብእና ያላቸው ሰው ነበሩ። በአንዳንድ ወቅቶች መግለጫ በሚሰጥበት ወቅት ተንበርክኬ ሲያዩኝ ፈገግ ብለው በኃዘኔታ ይመለከቱኝ ነበር። በጄኔቫ የነበሩ ሁሉንም ጋዜጠኞችን ያስታውሳሉ፤ ሰው በጭራሽ አይረሱም ነበር። ለማውራት ጊዜ ባይኖራቸው እንኳን ቆም ብለው ሰው ሰላም ይሉ ነበር። የሰላም ሻምፒዮን የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊነት ሚና በአለም ላይ ካሉ ፈታኝ የዲፕሎማሲያዊ ስራዎች አንዱ ነው። ኮፊ አናን በኮሶቮ የነበረው ጦርነትን ለማስወገድ ትልቅ ሚናን የተጫወቱና የአየር ፀባይ ለውጥ ለአለም እንደ ስጋት የተደቀነውም በሳቸው ወቅት ነው። የተባበሩት መንግሥታት በሳቸው አመራርም እያንዳዱን ችግርም አልቀረፈም። በብዙ ተቺዎች ዘንድ በኮፊ አናን አመራር ወቅት የተባበሩት መንግሥታት ስህተቶች ብለው የሚነቅሷቸው በሩዋንዳና በቦስኒያ የነበሩ የዘር ጭፍጨፋዎች፣ በኢራቅ የተከሰተውን ማዕቀብ ተከትሎም አንዳንድ ቢዝነሶችም የተባበሩት መንግሥታት ማዕቀቡን በማለስለሱ ነዳጅንም በመሸጥ የተፈጠረውን ቀውስ የመሳሰሉ ናቸው። ከስህተቶቹ በተቃራኒ በጄኔቫ ኮፊ አናን የሚታወሱት በጦርነት ውስጥ ለሚማስኑና መሔጃ ላጡ፣ ለአካባቢ ቀውሶችና በድህነት ውስጥ ተዘፍቀው ላሉ ምላሽን በመስጠት አይረሴ አሻራን ጥለው አልፈዋል። በተደጋጋሚም ለአለም መሪዎችን ምንም ያህል ኃይል ቢኖራቸውም ከፖለቲካ ጥቅም በፊት ዜጎቻቸውን ሊያስቀድሙ እንደሚገባ በአፅንኦት ይናገሩ ነበር። ማረፋቸው ከተሰማ በኋላም በጄኔቫ የተለያዩ ኃላፊዎችም ታላቁን ዲፕሎማት እንዴት እንደሚያስታውሷቸው እየተናገሩም። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዘይድ ራኢድ ሑሴን "የሰብአዊነት መለኪያ" ብለዋቸዋል። የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ዳይሬክተር ፒተር ማውረር በበኩላቸው ጥልቅ ኃዘናቸውን ገልፀው " ታላቅ ሰብአዊ መሪና የሰላም ሻምፒዮን" ሲሉ ጠርተዋቸዋል። የሳቸው ህልፈተ ህይወት በመላው አለም በተለይም በጄኔቫ ጥልቅ ኃዘንን ጥሎ ያለፈ ቢሆንም በጄኔቫ በተለይ ጓደኛችንን አጥተናል።
43890849
https://www.bbc.com/amharic/43890849
"ፍቅር እስከ መቃብር"ን በአይፎን 7?
ቴክኖሎጂ ትንፋሽ አሳጣን። በመረጃ ወጀብ ተናጥን፤ ተናወጥን።
ማን ይሆን በዚህ ዘመን ከቀልቡ የሆነ? ማን ይሆን ረዥም ልቦለድ ለመጨረስ አደብ የገዛ? ከብጥስጣሽ የበይነ-መረብ የመረጃ ሱናሚ ራሱን ያዳነ!? የዳሰስናቸው፣ የዳበስናቸው፥ የገለጥናቸው፣ አንብበን ሼልፍ ላይ የደረደርናቸው መጻሕፍት ዘመን ሊሽራቸው ነው። በፖስታና በሕዝብ ስልክ ላይ የደረሰው መገፋት ሊደርስባቸው ነው። ለዝመናና ለዘመን የሚሰው ባለተራዎች ለመሆን እየተንደረደሩ ነው። ከትናንት በስቲያ የነርሱ ቀን ነበር። የዓለም የመጻሕፍት ቀን! እኛ ዛሬ ብናስባቸው እምብዛም አልዘገየንም። "ሽፋናቸውን ካልዳሰስኩ፣ ጠረናቸው ካላወደኝ፣ ያነበብኩም አይመስለኝ" ዓለማየሁ ገላጋይ እርግጥ ነው መጻሕፍት ከናካቴው ደብዛቸው አይጠፋ ይሆናል። ሆኖም ብዙ ዘመን አብረውን እንደማይዘልቁ ከወዲሁ ምልክቶች እየታዩ ነው። ለምሳሌ ገና ከአሁኑ ከተፈጥሯዊው መዳፋችን እየተንሸራተቱ በቅንጡ ስልኮቻችን በኩል ራሳቸውን በቴክኖሎጂያዊ "መንፈስ" መግለጥ ጀምረዋል። ካላመናችሁ ብሩክን ጠይቁት። ወጣት ብሩክ ኃይሉ ላለፉት አምስት ወራት መጻሕፍትን ወደ ተንቀሳቃሽ ስልኮች የሚዶል "ሎሚ" የሚባል መተግበሪያ (App) ከወዳጆቹ ጋር አበጅቶ፣ የበይነመረብ መጻሕፍት መደብር ከፍቶ፣ በድረ-ገጽ መጽሐፍ እየቸረቸረ ይገኛል። ሎሚ የተሰኘው ይህ የስልክ መተግበሪያ እስካለፈው ሳምንት ብቻ 16ሺ ሰዎች በእጅ ስልኮቻቸው ጭነውታል። ለመሆኑ ደራሲዎቻችን ይሄን "ጉድ" ሰምተዋል? ከሰሙስ ምን አሉ? የዓለም መጻሕፍት ቀንን አስታከን የተለያዩ ትውልድን የሚወክሉ ደራሲዎች ሃሳብ ጠይቀናል፡፡ የቀንዲል ቤተ ተውኔት መሥራችና እስከ ቅርብ ጊዜም የኢትዯጵያ ደራሲያን ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት የነበሩት ጋሽ አያልነህ ሙላት ድንገት በአንድ ጊዜ ወደ በይነ-መረብ መገስገሳችንን እምብዛምም የወደዱት አይመስልም። "ይሄ መጻሕፍትን ኦንላይን የመሸጡ ጉዳይ እኛ ደራሲያን ማኅበርም መጥተው ጠይቀውናል። እና ብዙዎቻችን ከቴክኖሎጂው ጋር ግንኙነት የለንም። ግራ ተጋብተን ምንድነው ጥቅሙ? ጉዳቱስ? ደራሲውስ ምን ይጠቅማል? እያልንናቸው ነው…" ሲሉ ብዥታ መኖሩን ካተቱ በኋላ ስጋታቸውን ያስከትላሉ። "...ገና በንባብ ዳዴ የምትል አገር ናት። በዚህ ወቅት እንደዚህ ዓይነት የኦንላይን ሽያጭ ሲጀመር ይሄ ዳዴ የሚለው የንባብ ባሕል የሚቆረቁዝ ይመስለኛል።" ይላሉ። ግን እኮ ጋሽ አያልነህ…!ሰው በምንም ያንብብ፥ እንዴትም ያንብብ፣ ዞሮ ዞሮ ዋናው ማንበቡ አይደለም ሊገደን የሚገባው? ስንል ጠየቅናቸው፥ "የቴክኖሎጂ ጠላቶች ሆነን አይደለም እኮ" ብለው ጀመሩ አቶ አያልነህ፤ "...በቴክኖሎጂ የተነሳ ንባብ ጋ እየተፋታ ያለ፣ በፌስቡክ የተወሰኑ ነገሮችን እየወሰደ አነበብኩ ብሎ የሚል ወጣት፣ እንደገና መጽሐፍቱን በዚህ በኩል ይሰራጭ ማለት የንባብ ባሕሉን አይገድለውም ወይ? የሚል ስጋት ነው ያለኝ።" "መጽሐፍ በኢንተርኔት አንብቤ አላውቅም" ደራሲ አስፋው ዳምጤ እረ ለመሆኑ! ከምኑም ከምኑም በፊት፥ በኪንድል ወይም በስልካችሁ ወይም በኮምፒውተሮቻችሁ መጽሐፍ አንብባችሁ ታውቃላችሁ ወይ? አንድ አንዶቹን ብለንም ነበር፤ የ"ጉንጉኑ" ጋሽ ኃይለመለኮት የተወሰነ ሞካክረዋል። ደራሲ አስፋው ዳምጤ ግን የሉበትም። ከጥንት ከጠዋቱ የኩራዝ አሳታሚ ጀምሮ የነበሩት ጋሽ አስፋው ዳምጤ ለዚህ ኤሌክትሮኒክስ ለሚባለው የመጽሐፍ ግብይት ፍጹም ባዕድ ናቸው። ዘመናቸውን ሙሉ ከንባብ ያልተለዩት ጋሽ አስፋው በሕይወታቸው አንድም ቀን ይህን የኤሌክትሮኒክስ መጽሐፍ የሚባልን ነገር አለመጠቀማቸው እምብዛምም ላይገርም ይችላል። "የተሟሉ ሆነው የሚቀርቡ አይመስለኝም" ይላሉ፥ የኦንላይን መጻሕፍትን የማያነቡበትን ምክንያት ሲያስረዱ። ይህንኑ የጋሽ አስፋውን ስሜት ብዙዎቹ ይጋሯቸዋል። ደራሲ ዓለማየሁ በሎሚ የበይነ-መረብ የመጻሕፍት መደብር ውስጥ በምናባዊ ሼልፍ ላይ ተደርድሮ የሚሸጥ አንድ መጽሐፍ ቢኖረውም ይሄ የኦንላይን ነገር አይሆንለትም። ምቾትም የሚሰጠው ነገር አልሆነም። "በሶፍት ኮፒ አንብቤ የጨረስኳቸው መጻሕፍት አሉ። ኦሪጅናል ቅጂያቸውን ሳገኝ ግን በድጋሚ አነባቸዋለሁ። ለምን ካልከኝ ያነበብኳቸው ስለማይመስለኝ" ይላል ዓለማየሁ። በዚያ ላይ "ከነፍስህም ጋር ያለ ቅርርብ አለ። መጽሐፍህ ስንት ውጣ ውረድ አልፎ፥ ታትሞ ለመጀመርያ ጊዜ እጅህ ሲገባ ያለውን ስሜት አስበው። ያን ሁሉ ታጣለህ!" ይልና ሐሳቡን ያጠናክራል። "ለምን እንደሆን አላውቅም ሶፍትኮፒ ሳነብ ነባሩን እርካታዬን አይሰጠኝም።" የሚሉት አቶ ኃይለመለኮት በበኩላቸው ንጽጽሩን ከዚህም በላይም ያሰፉታል፤ "በካሴት ሙዚቃ መስማትና ሙሉ ባንድ ሲጫወት በአካል ተገኝቶ መታደም አንድ ነው?" የሎሚ የስልክ መተግበሪያ ላይ ድርሰቶቻቸውን እየሸጡ ከሚገኙ ወጣት ደራሲዎች መሐል የሸገር ሬዲዮው የወግ ጽሑፎች ተራኪ ግሩም ተበጀ ይገኝበታል። ግሩም ባሕላዊው የኅትመት አሠራር የሚታክት ሂደትን ማለፍ ይጠይቃል ይላል። ደርዝ ያላቸው አሳታሚዎች ገና እንዳልተወለዱ ካብራራ በኋላ የሎሚ መተግበሪያ ወደ ገበያው መምጣት ጊዜውን የጠበቀ እንደሆነ ይናገራል። ግሩም እውነት አለው። በተለምዷዊው አሠራር አንድ መጽሐፍ ተጽፎ አንባቢ እጅ እስኪገባ በአማካይ መንፈቅ ይወስድበታል፡፡ በነ ሎሚ የቀን አቆጣጠር ግን ጠዋት የተጻፈ መጽሐፍ ከሰዓት አንባቢ እጅ ሊደርስ ይችላል፡፡ አላጋነንኩም፡፡ የመተግበሪያውን ፈጣሪ ወጣት ብሩክ ይህንኑ አረጋግጦልኛል። "ፍቅር እስከ መቃብር"ን በአይፎን 7?'' ጋሽ አስፋው ዳምጤ እና ወጣት ብሩክ ኃይሉ ይሄ ነገር በትውልዶች መካከል ያለ ልዩነት ይመስላል። ጋሽ አስፋው ዳምጤ አንድም የኦንላይን መጽሐፍ አንብበው እንደማየውቁ እንደተናገሩት ሁሉ የሎሚ የበይነ መረብ መጽሐፍ መደብሩ መሥራች ወጣት ብሩክ ኃይሉ፥ ነፍስና ሥጋ ያለው፣ ደንበኛውንና መደበኛውን መጽሐፍ ከዳሰስ ረዥም ጊዜ ሆኖታል። ለመጨረሻ ጊዜ መቼ የሚዳሰስ መፃሕፍ እንዳነበበ ሲጠየቅ፤ አጠር ያለ ሳቅ ከሳቀ በኋላ "እኔ እንደነገርኩህ ሚሊኒያ ለሚባለው ለአዲሱ ትውልድ እቀርባለሁ፤ በእኛ ጊዜ ደግሞ ስናድግ ከመጽሐፍ የበለጠ ዲጂታል ከሆኑ ነገሮች ጋር ያለን ቁርኝት ስለሚበልጥ፣ ታላላቆቼ ለሚዳሰሱ መጻሕፍት ትዝታ ሊኖራቸው ይችላል። እኔ ግን የለኝም፤ ሁሉንም ነገር ስልኬ ላይ ማግኘት እመርጣለሁ..." ሲል ይናገራል። "ፍቅር እስከ መቃብር"ን በአይፎን 7 የምናነብበት ዘመን እየቀረበ ይመስላል።
57326606
https://www.bbc.com/amharic/57326606
ቻይና አእዋፋትን የሚያጠቃ በሽታ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ላይ አገኘች
አንድ የ41 ዓመት ቻይናዊ ጎልማሳ ኤች10ኤን3 (H10N3) በተባለ በሽታ የተያዘ የመጀመሪያው ሰው መሆኑ ተገለጸ።
ይህ የበሽታ አይነት (በርድ ፍሉ) ከዚህ ቀደም በአእዋፋት እንጂ ሰዎች ላይ ታይቶ አይታወቅም። ግለሰቡ እንዴት በበሽታው እንደተያዘ ዝርዝር መረጃ አልወጣም። ህመሙ ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ እንደማይተላለፍ ይታመናል። በቻይና ጂአንግሱ ግዛት ነዋሪ የሆነው ግለሰብ ባለፈው ሳምንት ነበር በሽታው የተገኘበት። አሁን ከበሽታው አገግሞ ከሆስፒታል ሊወጣ እንደሆነ ተገልጿል። የተለያዩ አይነት የአእዋፋት ህመሞች ያሉ ሲሆን፤ ከዶሮ ወይም ከሌሎች አእዋፋት ጋር በቅርበት የሚሠሩ ሰዎች በበሽታ መያዛቸው ተዘግቦ ያውቃል። በበሽታው ከተያዘው ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች ህመሙ እንዳልተገኘባቸው ተገልጿል። የቤጂንግ ብሔራዊ የጤና ተቋም እንዳለው፤ ግለሰቡ ሆስፒታል የገባው ሚያዝያ 28 ሲሆን፤ ኤች10ኤን3 እንዳለበት የተገለጸው ከአንድ ወር በኋላ ነው። ግሎባል ታይምስ እንደዘገበው ተቋሙ "በዓለም ላይ ኤች10ኤን3 የያዘው ሰው ሪፖርት ተደርጎ አያውቅም። ከጫጩት ወደ ሰው በመተላለፍ የአሁኑ የተለየ አጋጣሚ ነው። በስፋት የመሰራጨቱ እድልም አነስተኛ ነው" ብሏል። በሽታው በስፋት የመተላለፍ እድሉ ውስን እንደሆነም ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት ለሮይተርስ የዜና ወኪል "አሁን ላይ ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ የሚጠቁም ነገር የለም" ብሏል። "አቪን ኢንፍሉዌንዛ በጫጩቶች መካከል እንደሚሰራጨው ሁሉ የሰው ልጆችም ሊያዙ ይችላሉ። ይህ የሚያሳየን የኢንፍሊዌንዛ ወረርሽኝ ስጋት መኖሩን ነው" ሲልም ድርጅቱ ማብራሪያ ሰጥቷል። አሁን ላይ ኤች5ኤን8 (H5N8) የሚባል ዝርያ አዕዋፍትን እያጠቃ ይገኛል። በተለያዩ የአውሮፓ አገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ጫጩቶችን ገድሏል። የካቲት ላይ ሩስያ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን ዝርያ በሰው ላይ እንዳገኘች አስታውቃ ነበር። ከአእዋፋተ ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ የተሰራጨው እአአ ከ2016 እስከ 2017 ሲሆን፤ 300 ሰዎች ሞተዋል።
news-48810180
https://www.bbc.com/amharic/news-48810180
አሜሪካ፡ ብዙ ሰዎች በፌሰታል የተጣለችውን ልጅ በጉዲፈቻ ለመውሰድ እየጎረፉ ነው
በአሜሪካ ጆርጂያ ግዛት በፌስታል ተጥላ የተገኘችውን ህፃን ወስዶ ለማሳደግ በዓለም ዙሪያ ያሉ ቤተሰቦች ወረፋ መያዛቸውን የመንግሥት ኃላፊዎች ተናገሩ።
በአሜሪካ በጆርጅያ ግዛት በፌስታል የተጣለችው ሕፃን ልጅ 'ኢንድያ' የሚለው ቅፅል ስም የወጣላት ሕፃን ከ20 ቀናት ገደማ በፊት በፌስታል ተጠቅልላ የተገኘች ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቅሶዋን ሰምተው ነበር ለፖሊስ ደውለው ያሳወቁት። ፖሊሶች በደረት ካሜራቸው በቀረፁት ተንቀሳቃሽ ምስል ፌስታሉን ቀደው ሲያወጧት ይታያል። ሕጻኗ ወዲያው ወደ ሆስፒታል የተወሰደችው ሲሆን ዶክተሮች ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባት ተናግረው በአሁን ሰዓትም ኪሎዋ እየጨመረ መሆኑን አሳውቀዋል። ከተገኘች ሦስት ሳምንታት የሞላት ሕፃኗ በሕፃናት ማቆያ የምትገኝ ሲሆን 'ደስተኛ' እና 'በጥሩ ሁኔታ ላይ' ትገኛለች ተብሏል።። ቋሚ መኖሪያ ቤት እስኪገኝላት ድረስ በሕፃናቱ ማቆያ እንደምትቆይ የተነገረ ሲሆን የፎርሲት ክልል የፖሊስ ኃላፊ ቢሮ የልጅቷን እናትና ዘመዶች ለማግኘት እየጣሩ ነው። "እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል?' ተብሎ ነበር" መሠረት ማኒ ኤርትራ፡ ''እናቶች ከህጻናት ልጆቻቸው ጋር ታስረዋል'' ጄኔራል አደም የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው ተሾሙ ፖሊስ በፌስቡክ 'ስለ ህፃኗ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸው' አሳውቀዋል። ቶም ሬሊንግ የጆርጅያ የቤተሰብ እና ሕፃናት አገልግሎት ዳይሬክተር ሲሆን ሕፃኗን ለማሳደግ ደግሞ ፍላጎት ያሳዩ ብዙ ቤተሰቦች አሉ ይላል። ቶም "ልጅቷን ለማሳደግ እየተረባረቡ ያሉ ቤተሰቦች ወረፋ ይዘዋል" በማለት ለኤቢሲ የቴሌቪዥን ጣቢያ 'ጉድ ሞርኒንግ አሜሪካ' ፕሮግራም ተናግሯል። ጫካ አካባቢ ለቅሶ የሰሙ ነዋሪዎች ለፖሊስ አሳወቁ በአስገራሚ ሁኔታ የተገኘችው ይህች ሕፃን ሁኔታው በዓለም ዙሪያ ያሉ የብዙኃን መገናኛዎችን ትኩረት እንድትስብ አድርጎ በመቶ የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ልጅቷን በጉዲፈቻ ለማሳደግ ፈቃደኝነታቸውን አሳውቀዋል። ቶም ሕፃኗ በሕይወት መኖሯ ሲያስብ "እንደዚህ ዓይነት ተዓምራዊ ክስተት በሕይወቴ አይቼ አላውቅም" ብሏል። እትብቷ እምብርቷ ላይ እንዳለ የተገኘችው ሕፃን በፌስታል ውስጥ ተጥላ በአካባቢው ነዋሪዎች ስትገኝ ከተወለደች ሰዓታትን ብቻ ነበር ያስቆጠረችው። የክልሉ ፖሊስ ኃላፊ ሮን ፍሪማን የሕፃኗን መትረፍ "የፈጣሪ ጣልቃ ገብነት" እንደሆነ ገለፀዋል።
news-55068748
https://www.bbc.com/amharic/news-55068748
ስኮትላንድ ለዜጎቿ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን በነጻ ልታቀርብ ነው
ስኮትላንድ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ለዜጎች በነጻ በማቅረብ የመጀመሪያዋ አገር ልትሆን ነው።
የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች የአገሪቱ የሕዝብ እንደራሴዎች ትናንት ማክሰኞ ዕለት ዜጎች የወር አበባ ንጽህና በነጻ እንዲያገኙ የቀረበውን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ ማጽደቃቸው ተገልጿል። በአዲሱ ሕግ መሠረትም የየአካባቢው ባለስልጣናት ማንኛውም ምርቶችን የሚፈልግ ሰው መነጻ እንዲያገኛቸው የማመቻቸት ግዴታ አለባቸው ተብሏል። ይህንን ሀሳብ ያቀረቡት የሌበር ፓርቲ ተወካዩዋ ሞኒካ ሌነን ናቸው። የሕዝብ እንደራሴ ሞኒካ ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች እጥረት ላይ ሲሰሩ ቆይተዋል። ''ይህን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ ምንም የሚያግደን ነገር የለም። በተለይ ደግሞ በዚህ የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን እንዲህ በሚያስጨንቅበት ወቅት'' ብለዋል የሕዝብ እንደራሴዋ። አክለውም '' የወር አበባ በወረርሽኝ ጊዜ የሚቆም ነገር አይደለም። ለወር አበባ የሚሆኑ ምርቶች በቀላሉ ለሰዎች ማቅረብና በድጋሚ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ጥሬ እቃዎችን መጠቀም በጣም ወሳኝ ነው'' ብለዋል። በስኮትላንድ በተሰራ አንድ ኢመደበኛ ጥናት መሰረት ከ2000 በላይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና የኮሌጅ ተማሪዎች በቀረበላቸው ጥያቄ ከአራት ሴቶች መካከል አንዷ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂ ምርቶችን በበቂ ሁኔታ መግዛት አትችልም። ይህ በንዲህ እንዳለ በዩናይትድ ኪንግደም ከሚገኙ ሴቶች መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት የወር አበባ መገልገያዎችን መግዛት የማይችሉ ሲሆን 15 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በበቂ ሁኔታ መግዛት አይችሉም። በተጨማሪም 19 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በዋጋው ውድነት ምክንያት ጥራት የሌላቸውን እና ለመጠቀም የማይመቹ መገልገያዎችን ለመግዛት ተገድዋል። በጥናቱ መሰረት እድሜያቸው ከ14 እስከ 21 ከሆኑ ሴቶች መካከል 71 በመቶ የሚሆኑት የወር አበባ መገልገያዎችን ከመድሀኒት ቤቶችና ሌሎች ቦታዎች ሄደው ለመግዛት ያፍራሉ። የስኮትላንድ መንግሥት ይህንን ሀሳብ ለመደገፍ 5.2 ሚሊየን ዩሮ የመደበ ሲሆን ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 'ፌርሼር' የተባለው በጎ አድራጎት ድርጅት ደግሞ ለዝቅተኛ ገቢ ቤተሰቦች የወር አበባ መገልገያዎችን በነጻ እንዲያቀርብ ግማሽ ሚሊየን ዩሮ ያገኛል ተብሏል።
news-55876977
https://www.bbc.com/amharic/news-55876977
ኮሮናቫይረስ፡ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ የኮቪድ ክትባትን የሚቃወሙ ሰልፈኞች ከፖሊስ ተጋጩ
በአሜሪካ፣ ካሊፎርኒያ ግዛት፣ ሎስ አንጀለስ ከተማ የኮቪድ ክትባት ውሸት ነው የሚሉ ቀኝ አክራሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፡፡
ከፖሊስ ጋር የተጋጩት ክትባት እየተሰጠበት የሚገኘውን የዶገር ስታዲየም በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ሰልፈኞቹ ይህን የክትባት መስጠቱ ሂደት ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል እንዲስተጓጎል አድርገዋል፡፡ ቁጥራቸው 50 የሚሆኑ የጸረ ክትባት አቀንቃኞች ስታዲየሙን ለማዘጋት የቻሉት መግቢያውን በመዝጋት ጭምር ነው፡፡ ክትባት ለማግኘት ሰልፍ ላይ የነበሩ በርካታ መኪኖች በነዚህ የክትባት ተቃዋሚዎች ምክንያት አገልግሎት ሳያገኙ ተመልሰዋል፡፡ ሰልፈኞቹ የኮቪድ ክትባት የተጭበረበረ ስለመሆኑ የሚያወሱ መፈክሮችን የያዙ ሲሆን ኅብረተሰቡን ‹አትከተቡ፤ እናንተ የቤተ ሙከራ አይጥ አይደላችሁም› እያሉ ሲቀሰቅሱ ታይተዋል፡፡ የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ ቀኝ አክራሪ ሰልፈኞቹ ለክትባት የተሰለፉ ሰዎችን ‹ ነፍሳችሁን አድኑ፣ የውሸት ሳይንስ መጫወቻ አትሁኑ እያሉ እየጮኹ ሲቀሰቅሱ ነበር፡፡ የክትባት መስጫውን ሰልፈኞቹ የተቆጣጠሩትም በአገሬው አቆጣጠር ከቀኑ 8 ሰዓመት ጀምሮ ነው፡፡ የሎስ አንጀለስ ፖሊስ በትዊተር እንዳስታወቀው ስታዲየሙ አልተዘጋም፤ ክትባቱ ቀጥሏል ብሏል፡፡ የካሊፎርኒያ ገዥ ጋቪን ኒውሰን በስታዲየሙ እየተሰጠ የነበረው የክትባት ዘመቻ በሰልፈኞች ለጊዜው ቢስተጓጎልም ወደ ሥራ ተመልሷል ብለዋል፡፡ ጀርማን ጃኩዝ የተባለና ክትባት ለማግኘት ሰልፍ ሲጠባበቅ የነበረ ዜጋ ለሎስ አንጀለስ ታይምስ ቁጣውን የገለጸ ሲሆን ‹‹ይህ የቀኝ አክራሪዎች ድርጊት ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው› ብሏል፡፡ ‹‹ለሳምንታት ክትባት ለማግኘት ስጠባበቅ ነበር፡፡ እኔ የጥርስ ሐኪም ነኝ፡፡ በሽተኞቼን ሳክም በጣም ተጠግቻቸው ነው፡፡ ከኮቪድ መጠበቅ እሻለሁ፡፡ ክትባቱ ያስፈልገኛል፡፡ ተህዋሲውን ለመከላከል ብቸኛው መንገድ ክትባት ነው›› ሲል ሐሳቡን አጋርቷል፡፡ በአመዛኙ የትራምፕ ደጋፊ የነበሩ እንደሆኑ የሚገመቱና ቀኝ አክራሪ የሆኑት ሰልፈኞች ከያዟቸው መፈክሮች አንዱ ‹‹ሲኤንኤን እያታለላችሁ ነው›› ይላል፡፡ ሌሎች መፈክሮች፣ ‹‹ጭምብላችሁን ቀዳዳችሁ ጣሉት››፣ ‹‹የሰው አይጥ አትሁኑ›› የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ከአሜሪካ ግዛቶች ካሊፎርኒያ በተህዋሲው ክፉኛ ከተጠቁት ተርታ ትመደባለች፡፡ 40ሺ የግዛቲቱ ነዋሪዎች በኮቪድ ሞተዋል፡፡ 3 ሚሊዮኑ ተህዋሲው አለባቸው፡፡ በመላው አሜሪካ በኮቪድ ተህዋሲ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች በሚቀጥለው ወር ግማሽ ሚሊዮን እንደሚያልፍ ይጠበቃል፡፡
42800321
https://www.bbc.com/amharic/42800321
ሊቢያ ውስጥ 27 ሰዎች በቦምብ ጥቃት ተገደሉ
በሊቢያዋ ሁለተኛ ከተማ ቤንጋዚ ውስጥ በሚገኝ አንድ መስኪድ አቅራቢያ ትናንት ምሽት በሁለት መኪኖች ላይ የተጠመዱ ቦንቦች ፈንድተው ቢያንስ 27 ሰዎች ተገደሉ።
በደቂቃዎች ልዩነት ውስጥ በፈነዱት ቦምቦች ምክንያት ከ20 እስከ 30 ተጨማሪ ሰዎች የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው የተለያዩ ዘገባዎች አመልክተዋል። የመጀመሪያው ቦምብ የፈነዳው አል-ስሌይማኒ በተባለው ሰፈር ውስጥ ከሚገኝ መስኪድ ፊት ለፊት ሲሆን በወቅቱም ሰዎች የምሽት የፀሎት ፈጽመው ከመስኪዱ በመውጣት ላይ ሳሉ ነበር። ሁለተኛው ቦምብ ደግሞ ከመንገድ በተቃራኒ ስፍራ ላይ የመጀመያውን ተከትሎ ነበር የፈነዳው። ከቦምብ ጥቃቱ ሰለባዎች መካከል ሰላማዊ ሰዎችና ወታደሮች ይገኙበታል። በከተማው የሚገኘው የአል-ጃላል ሆስፒታል ቃል-አቀባይ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል እንደተናገሩት የጥቃቱ ሰለባዎች ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚል ተናግረዋል። እስካሁን ጥቃቱ በማን እንደተፈፀመ ግልፅ አይደለም። የቢቢሲ የሰሜን አፍሪካ ዘጋቢ ራና ጃዋድ ማን እንደፈፀማቸው የማይታወቁ በርካታ ተመሳሳይ የቦምብ ጥቃቶች ሊቢያ ውስጥ ከዚህ በፊት ማጋጠማቸውን ተናግራለች። ከሰባት ዓመት በፊት ሙአማር ጋዳፊ ከስልጣን ከተባረሩ በኋላ ሊቢያ ከባድ ጦርነት ውስጥ ወድቃለች። ሃገሪቱ ውስጥ ባሉት ሁለት ተቀናቃኝ ፓርላማዎችና ጠንካራ ታጣቂ ቡድኖች መካከል የበላይነትን ለመያዝ በሚደረገው ፍልሚያ ምክንያት እስላማዊ መንግሥት የተባለው አክራሪ ቡድን ለመጠናከር እድልን አግኝቷል። የቤንጋዚ ከተማ በወታደራዊው መስክ ሃያል በሆነው ሃሊፋ ሃፍታር በሚመራው፤ እራሱን የሊቢያ ብሄራዊ ሠራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድንና እስላማዊ ታጣቂዎች መካከል ግጭቶች ሲካሄዱባት ቆይታለች። ለሦስት ዓመታት ከተደረገ ፍልሚያ በኋላ ሃፍታር ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ የቤንጋዚ ከተማን ሙሉ ለሙሉ ከእስላማዊ ታጣቂዎች ነፃ ማውጣቱን አሳውቆ ነበር። ቢሆንም ግን በቤንጋዚ ከተማ ውስጥ የሚያጋጥሙት ግጭቶችና ጥቃቶች ቀጥለዋል።
43665468
https://www.bbc.com/amharic/43665468
"እንግሊዝ በእሳት እየተጫወተች ነው"ስትል ሩሲያ አስጠነቀቀች
በተባበሩት መንግስታት የሩሲያ አምባሳደር የሆኑት ቫሲሊ ኔብኒዚያ ከቀድሞ ሰላዩ መመረዝ ጋር በተያያዘ እንግሊዝ የተያያዘቸው ማስረጃ በሌላቸው ውንጀላዎች ሩሲያን ማጠልሸት እንደሆነ ተናግረዋል።
በተመድ የሩሲያው አምባሳደር እንግሊዝ በእሳት እየተጫወተች እንደሆነና በዚህም እንደምትፀፀት ተናግረዋል አምባሳደሩ ይህን ያሉት በተመድ የፀጥታው ፍርድ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው። እንግሊዝ ከምረዛ ጀርባ ያለችው ሩሲያ ናት ብትልም ሩሲያ ነገሩን አስተባብላለች። ሩሲያ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በሚደረገው ምርመራ ልሳተፍ ብትልም ራሷ የድርጊቱ ፈፃሚ ራሷ መርማሪ የሚል አንድምታ ያለው ምላሽ በእንግሊዝ ተሰጥቷል። የሩሲያው የቀድሞ ሰላይ ሰርጌ ስክራይፓልና ሴት ልጃቸው ዩሊያ ከአንድ ወር በፊት ራሳቸውን ስተው የተገኙት እንግሊዝ ሳልስበሪ ውስጥ ነበር። የ66 አመቱ ስክራፓልና የ33 ዓመቷ ልጃቸው ዩሊያ አሁንም ሆስፒታል ናቸው። የ66 ዓመቱ አባቷ አሁንም በፅኑ እንደታመሙ ሲሆን ዩሊያ ግን አገግማለች። ሞስኮ በኒዮርክ የተካሄደውን የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ የጠራችው እንግሊዝ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ መመለስ የሚገባት ነገሮች አሉ በማለት ነው። በተመድ የሩሲያው አምባሳደር ኒቤነዚያም እንግሊዝ ምንም ተጨባጭ ነገር በሌለበት ሩሲያ ላይ የፕሮፓጋንዳ ጦርነት መክፈቷን ተናግረዋል። የቀድሞ ሰላዩንና ልጃቸውን ለመመረዝ ጥቅም ላይ የዋለው ኖቫይቾክ ሩሲያ የባለቤትነት መብት ያስመዘገበችበት እንዳልሆነም ይልቁንም በየትኛውም አገር እየተሰራ እንዳለ ገልፀዋል። "የሆነ ግራ የገባው ቴአትር ነው።የተሻለ ድራማ ሰርታችሁ መምጣት አልቻላችሁም?"በማለት እንግሊዝ እያደረገች ያለውን ነገር ኮንነዋል። 15 አባላት ላለው የፀጥታው ምክር ቤትም ሩሲያ ለምን በጣም አደገኛና ግልፅ በሆነ መንገድ አንድ ግለሰብን መግደል ትፈልጋለች? ሲሉ ጠይቀዋል። ሰዎችን በመርዛማ ኬሚካል ከመግደል ይልቅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ረቂቅ የግድያ ስልቶች ለመኖራቸውን የእንግሊዙ የቴሌቭዥን ተከታታይ ፊልም 'ሚድሳመር መርደርስ' ምስክር እንደሚሆን እስከመጥቀስም ደርሰዋል አምባሳደሩ።
news-53245472
https://www.bbc.com/amharic/news-53245472
ቼክ ሪፐብሊክ ኮሮናቫይረስን 'ደህና ሁን' ስትል ደግሳ ተሰናበተች
የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከምድራችን የመጥፊያ ቀን እጅጉን የራቀ መሆኑን ያሳወቀው በዚህ ሳምንት ነበር። ነገር ግን ቼክ ሪፐብሊክ ደግሳ ኮሮናቫይረስን "ደህና ሁን" ስትል ተሰናብታዋለች።
ማክሰኞ እለት በፕራግ ከተማ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማብቃቱን በማስመልከት ነዋሪዎች ተሰባስበው አክብረውታል ማክሰኞ እለት በፕራግ በሚገኘው ቻርልስ ድልድይ ላይ 500 ሜትር በሚረዝም ጠረጴዛ ዙሪያ የተሰባሰቡ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከቤታቸው ይዘውት የመጡትን መጠጥና ምግብ በጋራ ተቋድሰዋል። እንግዶች አጠገባቸው ከጎረቤቶቻቸው ጋር ምግብ የተጋሩ ሲሆን ማህበራዊም ሆነ አካላዊ ርቀት አይስተዋልም ነበር ተብሏል። ይህ ደግሞ በእንቅስቃሴ ገደብ ውስጥ በቆዩ ከተሞች ሁሉ ያልተስተዋለ ነው ተብሏል። 10 ሚሊዮን ሕዝብ ባላት ቼክ ሪፐብሊክ የኮቪድ-19 እንዳለባቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 12 ሺህ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 350 ሰዎች ሞተዋል። ይህንን ፈንጠዝያ ያዘጋጁት አካላት እንደተናገሩት በዚህች ዝነኛ የቱሪስት መስህብ ከተማ ጎብኚ በመጥፋቱ ሊካሄድ ችሏል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። በፈንጠዝያው ላይ የተነሱ ምስሎች እንደሚያሳዩት ሰዎች ተጠጋግተው በመቀመጥ ሲመገቡ፣ ሲጠጡና ትርዒቶችን ሲመለከቱ ይታያል። በዚህ ድግስ ላይ ለመገኘት አስቀድሞ ቦታ ማስያዝ ያስፈልግ የነበረ ሲሆን ያሉት ስፍራዎች ሁሉ የሞሉት ፈንጠዝያው ከመጀመሩ አስቀድሞ ነው በትልቅ ዙሪያ የተሰባሰቡ ሰዎች ምግባቸውን እየተመገቡ የሙዚቃ ትርዒት ታድመዋል ኦንድሬጅ ኮብዛ ይህንን ፈንጠዝያ ካዘጋጁት መካከል አንዱ ሲሆን በከተማዋ ውስጥም ካፍቴሪያ አለው። ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ስለበዓሉ ሲናገር " የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ማብቃትን ሰዎች አደባባይ ወጥተው በመገናኘት እንዲሁም ከጎረቤታቸው ጋር ምግብ መቋደስ እንደማይፈሩ በማሳየት እንዲያከብሩት እንፈልጋለን" ብሏል። በዚህ ድግስ ላይ ለመገኘት አስቀድሞ ቦታ ማስያዝ ያስፈልግ የነበረ ሲሆን ያሉት ስፍራዎች ሁሉ የሞሉት ፈንጠዝያው ከመጀመሩ አስቀድሞ ነው። ይህ ክብረ በዓል የተዘጋጀው ቼክ ሪፐብሊክ ጥላ ነበረውን የእንቅስቃሴ ገደብ ማላላቷን ተከትሎ ነው በዝግጅቱ ላይ ከታደሙት መካከል አንዷ የሆነችው ጋሊና ኮህምቼንኮ ስለ ድግሱ የሰማችው በፌስ ቡክ መሆኑን ገልፃ ደስተኛ መሆኗን ተናግራለች። "ከስራ አምሽቼ ነው የወጣሁት፤ እናም ምግብ አዘጋጅቶ ለመምጣት አልቻልኩም፤ ነገር ግን በቤቴ ያገኘሁትን ወይንና ጣፋጮች ይዤያለሁ" ስትል ተናግራለች። ቼክ ሪፐብሊክ የእንቅስቃሴ ገደብ የጣለችው ወረርሽኙ እንደተከሰተ ሲሆን በዚህም የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ማድረግ ችላ እንደነበር ይነገራል። ባለፈው ሳምንት መንግሥት እስከ አንድ ሺህ ሰዎች ድረስ በአደባባይ መሰብሰብ ይችላሉ ሲል ፈቅዷል። ዋና፣ ሙዚየሞች፣ መካነ አራዊቶች እንዲሁም ቤተ መንግሥቶች ክፍት ሲሆኑ የጎብኚዎች ቁጥርም አልተገደበባቸውም። ምግብ ቤቶችና መጠጥ ቤቶችም እንግዶቻቸውን በቤት ውስጥ ማስተናገድ እንደሚችሉ ከተፈቀደ አንድ ወር ሆኖታል።
news-53160665
https://www.bbc.com/amharic/news-53160665
በቻይና የቢሊየነሮች ዝርዝር ጃክ ማ 3ኛ ሆነ
ቻይናዊው ኮሊን ሁዋን ከጥቂት ዓመታት በፊት አንድ ተራ የጉግል መሥሪያ ቤት ሰራተኛ ነበር፡፡ ፒንዶዶ የሚባል የድረገጽ የገበያ ጉሊት ፈጠረና ከተራ ሰራተኝነት ወደ ሚሊየነርነት፣ ከሚሊየነርነት ወደ ቢሊየነርንት ተመነደገ፡፡
አሁን ኮሊን ሁዋን ሐብቱ 45.4 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ብሏል የባለጸጎችን ምስጢር የሚያወጣው ፎርብስ መጽሔት፡፡ ይህ ማለት ኮሊን ሁዋን ከአሊባባው ጌታ ጃክ ማን በአንድ ደረጃ በልጧል ማለት ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ከቻይናዊው ቁጥር አንድ ቢሊየነር የቴንሳ ፈጣሪ ፖኒ ማ ሲሆን ቀጥሎ የፒንዶዶው ኮሊን ሁዋን ይከተልና ጃክ ማ ሦስተኛ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ሚስተር ሁዋን መጀመርያ በማይክሮሶፍት ተለማማጅ ሰራተኛ ሆኖ ነበር የገባው፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ጉጉል መስሪያ ቤት ገብቶ በመሐንዲስነት ሦስት ዓመት ቆየ፡፡ • የህዳሴው ግድብ ድርድር ወደ ማይታረቅ ቅራኔ ደረጃ ደርሶ ይሆን? • ኮሮናቫይረስንና ኢምፔሪያሊዝምን 'እንደመስሳለን' የሚሉት ጆን ማጉፉሊ • በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ሊደረግ ነው በ2016 የጦመረው አንድ ጽሑፍ ‹‹ እነዚያ በጉግል መስሪያ ቤት የቆየሁባቸው 3 ዓመታት እጅግ ወሳኝ ነበሩ›› ብሎ ነበር፡፡ ፎርብስ እንደሚለው የፒንዶዶ የድረ ገጽ ገበያ ተፈላጊነት ጣሪያ በመንካቱ ነው ሚስተር ሁዋን የአሊባባውን ጃክ ማንን ሊበልጠው የቻለው፡፡ ሚስተር ሁዋን ፒንዶዶን የፈጠረው በፈረንጆቹ በ2015 ነበር፡፡ ይህ የኮሮና ወረርሽኝ የዚህን የድረገጽ ኦንላይ ገበያ ድርሻ በከፍተኛ ሆኔታ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል፡፡ ምክንያቱም ቀድሞ በዚህ ገጽ በአንድ ቀን የነበረው ገበያ 50 ሚሊዮን አካባቢ ሲሆን አሁን ግን 65 ሚሊዮን አልፏል፡፡ ፒንዶዶ ከሌሎች የኦንላይን ጉሊቶች የሚለይበት አንዱ መንገድ ሰዎች እየተደራጁ ሰብሰብ ብለው አንድ እቃ መግዛት መቻላቸው ነው፡፡ ይህን ካደረጉ የዕቃው ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንስላቸዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ደንበኞች በድረገጹ ጌም መጫወት ይችላሉ፤ የገበያ ኩፖንም ይሸለማሉ፤ በኩፖኑ ደግሞ የሚፈልጉትን እቃ እንዲገዙበት ያስችላቸዋል፡፡ አሁን ዓለምን እየመሩ ያሉ ቢሊየነሮች በብዛት ገቢያቸው ከኦንላይን ግብይት ጋር እየተሳሰረ መጥቷል፡፡ ፎርብስ ባወጣቸው የቅርብ ጊዜ መረጃዎች የዓለም ቁጥር አንዱ ባለጸጋ የአማዞኑ ጄፍ ቤዞስ ሲሆን ሐብቱ $162.2 ቢሊዮን ደርሶለታል።
51886417
https://www.bbc.com/amharic/51886417
አውሮፓ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ 'ማዕከል' ሆናለች ተባለ
በቀደሙት ሳምንታት የኮሮናቫይረስ ማዕከል የነበረችው ቫይረሱ የተቀሰቀሰባት ቻይና የነበረች ሲሆን ባለፉት ጥቂት ቀናት በታየው ሁኔታ ግን አውሮፓ የቫይረሱ ማዕከል ወደ መሆን መምጣቷን የዓለም ጤና ድርጀት አስታወቀ።
የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የአውሮፓ አገራት ቫይረሱን ተቆጣጥረው ነፍስ ለማዳን መጠነ ሰፊ ስራዎችን መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። "ይሄ እሳት እንዲነድ አትተዉት" በማለት በአውሮፓ እየታየ ያለው የኮሮናቫይረስ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢነትን ለመግለፅ ሞክረዋል። ዶ/ር ቴድሮስ ይህን ያሉት በርካታ የአውሮፓ አገራት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን እንዲሁም ሞትን እያስመዘገቡ ባለበት በዚህ ወቅት። • የዩናይትድ ኪንግደም ጤና ጥበቃ ሚኒስትር በኮሮናቫይረስ ተያዙ • ጣልያን ኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው አካባቢዎችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ዘጋች • ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መሆኑ ታወጀ ጣልያን ከአውሮፓ አገራት ከፍተኛውን የኮሮናቫይረስ ስርጭትና ሞት እያስመዘገበች ያለች የአውሮፓ አገር ነች። ባለፈው አንድ ቀን በተወሰኑ ሰዓታት ውስጥ በጣልያን 250 ሞቶች ሲመዘገቡ እስካሁን በአጠቃላይ 1266 ሞቶች፤ 17660 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ተመዝግቧል። ከጣልያን ቀጥሎ በቫይረሱ ክፉኛ የተመታችው የአውሮፓ አገር ስፔን ስትሆን በትናንትናው እለት ብቻ የሟቾች ቁጥር በእጥፍ ሲጨምር በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 4231 ደርሷል። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ለሁለት ሳምንት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚያውጁ አስታውቀዋል። በበርካታ የአውሮፓ አገራት ድንበር ላይ ከፍተኛ የኮሮናቫይረስ ምርመራና ቁጥጥር እየተደረገ ነው።
news-42550177
https://www.bbc.com/amharic/news-42550177
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለፍልስጤማውያን የሚሰጠው እርዳታ ሊቋረጥ ይችላል ሲሉ አስጠነቀቁ
አሜሪካ ለፍልስጤማውያን የእርዳታ እጇን መዘርጋት ልታቆም ትችላለች። "ስለ ሰላም ለመነጋገር ፈቃደኛ አይደሉም" ብለዋል ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቲውተር መልዕክታቸው አሜሪካ ለምትሰጠው እርዳታ "ምስጋናም ወይንም አክብሮት" ተቀብላ አታውቅም ሲሉም አክለዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለፍልስጤማውያን የሚሰጠው እርዳታ ሊቋረጥ ይችላል ሲሉ አስጠነቀቁ በተጨማሪም አጨቃጫቂውእየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማነት ውሳኔ ለሰላም ድርድሩ "ከጠረጴዛው ላይ መነሳት" ሰበብ ሆኗል። ፍልስጤማውያን ውሳኔው የሚያሳየው አሜሪካ ገለልተኛ ሆና ልትሸመግል እንደማትችል ነው ብለዋል። ባለፈው ወር ውሳኔው በተባበሩት መንግሥታት የተኮነነ ሲሆን 128 ሃገራትም ከትራምፕ ውሳኔ በተቃራኒው ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ምን አሉ? ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለፓኪስታን የእርዳታ ገንዘብ የላኩትን "ውሸት እና አለመታመን" የሚል የቲውተር መልዕክታቸውን ተከትለው "እንዲሁ በባዶ ቢሊየን ዶላር የምንሰጠው ለፓኪስታን ብቻ አይደለም።" "በየዓመቱ ለፍልስጤማውያንም በርካታ ሚሊየን ዶላሮች እንሰጣለን ነገር ግን ክብርም ሆነ ምስጋና አላገኘንም። ከእስራኤል ጋር እንኳ በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ ስለሰላም ለመነጋገር አይፈልጉም" ብለዋል። ኒኪ ሃሌይ በተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት "የድርድሩ አካል የነበረችውን እየሩሳሌም ከጠረጴዛ ላይ አንስተናታል፤ ነገር ግን እስራኤል ለዚያ የበለጠ ትከፍላለች። ፍልስጤማውያን ግን ለሰላም ንግግሩ በራቸውን ዘግተዋል። ታዲያ ለምን ወደፊት ያንን ያህል ገንዘብ እንሰጣቸዋለን?" ፍልስጤማውያን ምን አሉ? እየሩሳሌም በዓለማችን በጣም አጨቃጫቂ ከሆኑ ቦታዎች አንዷናት። እስራኤል ሙሉ እየሩሳሌምን ለዋና ከተማነት ትጠይቃለች። ፍልስጤማውያን ግን በ1967ቱ የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት በእስራኤል የተያዘውን ምሥራቅ እየሩሳሌምን የወደፊቷ የፍልስጤም ዋና ከተማ እንድትሆን ይፈልጋሉ። ትራምፕ ግን ይህ ውሳኔ በቀጠናው አለመረጋጋት ሊፈጥር ይችላል እየተባለ ባለበት እየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ መሆኗን በይፋ ተቀብለዋል። በተጨማሪም የአሜሪካ ኤምባሲም የሁሉም ሃገራት ቆንሲላዎች ካሉበት ቴላቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም ይዞራል ብለዋል። ከዚህ መግለጫ በኋላም የፍልስጤም ፕሬዝዳንት መሃሙድ አባስ ከትራምፕ መንግሥት የሚመጣ ምንም አይነት ምክረ ሃሳብ አንቀበልም ሲሉ አስታውቀዋል። እየሩሳሌምንም "የፍልስጤማውያን ዘላለማዊ ከተማ" ብለዋታል። የትራምፕ ቲውተር መልዕክት የመጣው በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ከሆኑት ኒኪ ሀሌ አሜሪካ የተባበሩት መንግሥታት ለፍልስጤማውያን ስደተኞች የሚያደርገውን ድጋፍ ታቋርጣለች የሚለውን ንግግር ተከትሎ ነው። ድርጅቱ ትምህርትን፣ ጤናን እና ሌሎች ማህበራዊ ፕሮግራሞችን ያካሄዳል። አሜሪካ በ2016 ወደ 370 ሚሊየን ዶላር በመስጠት ትልቋ ለጋሽ ሃገር ናት።
50313544
https://www.bbc.com/amharic/50313544
በቃፍታ-ሸራሮ ብሔራዊ ፓርክ በተከሰተው ሰደድ እሳት 1,500 ሄክታር ደን ወደመ
በሰሜን ኢትዮጵያ በቃፍታ-ሸራሮ ብሔራዊ ፓርክ በተከሰተው ሰደድ እሳት ሳቢያ 1,500 ሄክታር ደን መቃጠሉ ተገለጸ።
የቃፍታ-ሸራሮ ብሔራዊ ፓርክ አስተባባሪ አቶ ዘነበ አረፋይኔ ለቢቢሲ እንደገለፁት፤ ሰደድ እሳቱ የተነሳው ፓርኩ ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ገብተው ወርቅ ለማውጣት የሚሞክሩ እረኞች ባቀጣጠሉት እሳት እንደሆነ ታውቋል። አስተባባሪው "እሳቱ በተለይም በፓርኩ ውስጥ የሚገኙ ዝሆኖችን እንዳያባርር ተሰግቷል" ብለዋል። • የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከቃጠሎው በኋላ • የሰሜን ተራሮች ፓርክ እሳት ሙሉ በሙሉ አልጠፋም ሰደድ እሳቱ ሰኞ አመሻሽ ላይ እንደተከሰተና ዛሬ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ አቶ ዘነበ ገልጸዋል። ሰደድ እሳቱ እንደተነሳ ለዱር እንስሳትና ደን ጥበቃ ባለስልጣን እንዳሳወቁ የተናገሩት አስተባባሪው፤ እሳቱን ለማጥፋት የትግራይ ምዕራባዊ ዞንና የቃፍታ ሑመራ ወረዳ መስተዳድር የአደባይ ሕዝብ መተባበሩን አስረድተዋል። ማኅበረሰቡ ሰደድ እሳቱን በባህላዊ መንገድ ለማጥፋት ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ዛሬ ጠዋት እሳቱን መቆጣጠር መቻሉንም ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአከባቢው የሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊሶች እሳቱን በማጥፋት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውም ታውቋል። አስተባባሪው ዳግመኛ ሰደድ እሳት እንዳይከሰት ከፍትኛ ክትትልና ጥንቃቄ መወሰድ አለበት ብለዋል።
news-41325315
https://www.bbc.com/amharic/news-41325315
ከምድረ-ገጽ የመጥፋት ሥጋት በሰውነት መጠን ይወሰናል
በዓለማችን ላይ ካሉ እንስሳት ሁሉ በመጠን ግዙፎቹና ትናንሾቹ እንስሳት ከምደረ ገጽ የመጥፋት ስጋት ይበልጥ ተጋርጦባቸዋል ይላል- አዲስ የወጣ ጥናት
እንደጥናቱ የጀርባ እጥንት ያላቸው እንስሳት የመጥፋት ተጋላጭነታቸው በሰውነታቸው መጠን ይወሰናል፤ በጣም ትልቅ ወይም ትናንሽ ካልሆኑት ይልቅ በሁለቱም ጫፍ ያሉት ለሞት የተጋለጡ ናቸው። ከፍተኛ ክብደት ያላቸው በአደን ስጋት ውስጥ ሲወድቁ ትንንሾቹ ደግሞ በአየር መበከልና በማረፊያ ዛፎች መመናመን ምክንያት ህልውናቸው እየተፈተነ ነው። "ከሁሉም የሚተልቁት የጀርባ አጥንት ያላቸው እንስሳት ከምንም በላይ በቀጥታ በሰዎች ይገደላሉ'' ይላሉ በኦሬጎን ዩኒቨርሲቲ የአጥኚ ቡድኑ መሪ የሆኑት ፐሮፌሰር ቢል ሪፕል። "ትንንሾቹ ደግሞ ለእነርሱ ምቹ የሆኑ መኖሪያዎች በጣም ውሱን እየሆኑ ነው፤ ይሄ ደግሞ የመጥፋት አደጋን የመተንበይ ያክል አደገኛ ነው'' 'ሃመርሄድ' የሚባለው ሻርክ በህገወጥ አጥማጆች ምክንያት አደጋ ላይ ወድቋል ጥናቱ እንደሚለው የእንስሳቱ የሞት መጠን በሰውሰራሽ ምክንያቶች በርካታ እንስሳት ከምድረገጽ የሚጠፉበት ዘመን እየተቃረበ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ታዲያ ለዚህ ምክንያቶቹ ምንድናቸው ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ መፈለጉ አልቀረም። የተገኘው አንድ ፍንጭ ደግሞ የስውነት መጠናቸው ነው፤ በአጥቢ እንስሳትና በወፎች ላይ የተደረገው ጥናት የሚያሳየው ግዙፍ ሰውነት ያላቸው ለመጥፋት እየተቃረቡ መሆኑን ነው። አጥኚዎቹ በሺዎች በሚቆጠሩ ወፎች ፣ በአጥቢና ተሳቢ እንስሳት እንዲሁም በየብስና በውሃ በሚኖሩ እንስሳት ዙሪያ መረጃ ሲያጠናቅሩ በግዙፎቹና ትናንሾቹ እንስሳት ከሌሎቹ ጋር ሊነጻጸር የማይችል የሞት መጠን አስተውለዋል። "በሚያስገርም ሁኔታ የጅርባ እጥንት ካላቸው እንስሳት ግዙፎቹ ብቻ ሳይሆኑ ትንንሾቹም በትልቅ አደጋ ላይ መሆናቸውን ተረዳን '' ብለዋል ፕሮፌሰሩ። ይህ እንቁራሪትም ብዛቱ እየተመናመነ መጥቷል እንደ ዝሆን ፣ አውራሪስና እንበሳ ያሉ ሞገስ ያላቸው እንስሳት ለዘመናት የመከላከያ ጥረቶች ማዕከል ሆነው ቆይተዋል። ሆኖም እንደ አሳነባሪ፣ የሶማሊያ ሰጎንና የቻይና ግዙፍ እንሽላሊት መሰል ተሳቢዎች እንዲሁም ሌሎች የአሳ፣የወፍና የተሳቢ እንስሳት ዝርያዎች ትኩረት ተነፍጓቸዋል። በተመሳሳይ የእንቁራሪትና የአይጥ ዝርያዎችም ቸል እየተባሉ ነው። "እንደሚመስለኝ ስለትንንሾቹ ዝርያዎች ከሁሉ አስቀድመን ግንዛቤ መስጠት አለብን፤ ምክንያቱም ትልልቆቹ ናቸው ሁልጊዜም የሰዎችን ትኩረት የሚስቡት'' ይላሉ ፕሮፌሰር ሪፕል። ከአሜሪካ፣ ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ከስዊዘርላንድና ከአውስትራሊያ የተውጣጡት የጥናቱ አዘጋጆች ከ25,000 በላይ የሚሆኑ ዝርያዎችን የክብደትና የሞት መጠናቸውን ግንኙነት አነጻጽረዋል። ከነዚህ ውስጥ 4000 የሚሆኑት የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠባቸው አረጋግጠዋል። የጅርባ አጥንት ያላቸው ግዙፎቹና ትንንሾች እንስሳት ደግሞ በመሬትም ኖሩ በውሃ ውስጥ ከምደረ ገጽ የመጥፋት ስጋት ላይ ናቸው። ለግዙፎቹ እንስሳት ስጋት የሆኑት ትንንሾቹ እንስሳት ላይ የተደቀኑ ስጋቶች የባራቪያ አይጠ-መጎጦች ከፍተኛ የመጥፋት ስጋት ውስጥ ናቸው አጥኚዎቹ እንደሚሉት እንስሳቱን ከስጋት ለመጠበቅ የተለያዩ አማራጮች ቢኖሩም በአስቸኳይ መደረግ ያለባቸው ጉዳዮችም አሉ። "ከምንም በላይ የዓለምን የዱር እንስሳት ስጋ ፍጆታ መቀነስ አደኑን፣ አሳ ማጥመዱንና፣ የደን መመናመኑን ለመቀነስ ወሳኝ እርምጃ ይሆናል ፤ ያም ሆነ ይህ ግን ሰዎች ለእንስሳቱ ሞት ዋነኞቹ ተጠያቂዎች ናቸው''
news-42490533
https://www.bbc.com/amharic/news-42490533
ብራዚል የቬንዝዌላን ዲፕሎማት አባረረች
ብራዚል የቬንዝዌላውን አንጋፋ ዲፕሎማት ጌራርዶ ዴልጋዶን በብራዚል ተቀባይነት የሌለው ግለሰብ ስትል አውጃለች።
የቬንዝዌላው ፕሬዝደንት ኒኮላስ ማዱሮ ብራዚል የሕግ የበላይነትን ጥሳለች ሲሉ ኮንነዋል። ካናዳም የቬንዝዌላውን አምባሳደር እና ምክትላቸውን 'ከሃገር ላስወጣ' ነው ማለቷ ይታወሳል። ካናዳ የቬንዝዌላን አምባሳደር አባረረች ብራዚል ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ቬንዝዌላ የብራዚልን አምሳደር ከካራካስ ካባረረች በኋላ ነው። ቬንዝዌላ አምባሳደሩን ያባረረችበትን ምክንያት ስታስረዳ፤ ብራዚል ግራ ዘመም የነበሩትን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዴልማ ሩሴፍ ያለ አግባብ ነው ክስ ቀርቦባቸው ከስልጣን እንዲወርዱ የተደረገው ትላለች። ቬንዝዌላ በተደጋጋሚ ካናዳን በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ትገባለች በማለት ባሳለፈነው ሳምንት መጨረሻ የካናዳ አምባሳደርንም ከሀገር አስወጥታለች። የካናዳዋ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክርስችያ ፍሬላንድ በሰጡት መግለጫ ''እኛ ካናዳዊያን የዜጎቹን ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት ነጥቆ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ከሚያሳጣ መንግሥት ጋር ወዳጅነት ሊኖረን አይችልም'' ሲሉ ተደምጠዋል። የቬንዝዌላው አምባሳደር ከሃገር ውጪ መሆናቸውን እና ወደ ካናዳ እንዲገቡ አንደማይፈቀድላቸው እንዲሁም ምክትል አምባሳደሯ ካናዳን ለቀው አንዲወጡ እንደተነገራቸው የውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ጨምረው ተናግረዋል። የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደርም በፕሬዝዳንት ማዱሮ ላይ ማዕቀቦችን ከመጣሉም በላይ ፕሬዘደንቱን ''አምባገነን'' ሲል መፈረጁ ይታወሳል። የቬንዙዌላ ተቃዋሚዎች ፕሬዝደንት ማዱሮ እና የቀድሞ ፕሬዝደንት ሁጎ ቻቬዝ በሶሻሊስት ሥርዓተ-መንግሥታቸው የቬንዝዌላን ኢኮኖሚ ክፉኛ ጎድተዋል ሲሉ ድምጻቸውን ያሰማሉ። የቬንዙዌላ መንግሥት በበኩሉ አሜሪካ በሃገራችን ላይ የጣለችው ማዕቀብ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መቀነስ ለኢኮኖሚ ድቀቱ ምክንያት ነው ይላሉ። ቬንዝዌላ በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ካለባቸው ሀገራት አንዷ ስትሆን መድሃኒትን ጨምሮ መሰረታዊ የሚባሉ ሸቀጦች እጥረት በተደጋጋሚ ያጋጥማታል። የፕሬዝደንት ማዱሮ የስድስት ዓመት የስልጣን ዘመን እአአ 2019 ይጠናቀቃል። ቢሆንም ተቃውሞ የበረታባቸው ማዱሮ በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ለተጨማሪ የስልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ አስታወቀዋል። ማዱሮ ከጥቂት ቀናት በፊት የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ከሃገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ማገዳቸው ተዘግቧል።
51202804
https://www.bbc.com/amharic/51202804
ቻይና ውስጥ የተከሰተው ተላላፊና ገዳይ ቫይረስ አሜሪካ ደረሰ
ቻይና በግዛቷ የተገኘው ቫይረስ የበለጠ ሊስፋፋ እንደሚችል ባለስልጣናቷ እያስጠነቀቁ ነው።
በቅርቡ በቻይና ተከስቶ 9 ሰዎችን ለህልፈት የዳረገው ቫይረስ አሁን ካለበት በላይ ሊስፋፋ እንደሚችል የአገሪቱ ባለስልጣናት ማረጋገጣቸውን ይፋ አድርገዋል። በውሃን ግዛት እስካሁን በተደረገው ምርመራ 440 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ታውቋል። አሁን በሚወጡ መረጃዎች መሰረት ቫይረሱ በበርካታ የቻይና ግዛቶች ተስፋፍቷል። ይህም በአጭር ጊዜ ውስጥ የተደረገ መስፋፋት ስለሆነ ቀጣይ ብዙ ግዛቶችን በአጭር ጊዜ ያዳርሳል ተብሎ በትልቁ ስጋትን በመፍጠሩ ነው የባለስልጣናቱ ማስጠንቀቂያ ያስፈለገው። ከቻይና ውጭም በተለያዩ የዓለም አገራት ቫይረሱ ተሻግሮ መገኘቱ ደግሞ አሳሳቢነቱን ጨምሮታል። ከነዚህ አገራት መካከል ደቡብ ኮሪያና ታይላንድ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው። የተደረገው ምርመራ ቻይና ውሃን ግዛት የተነሳው ቫይረስ ከእሲያ አህጉር ወጥቶ ሌላ አህጉር ገብቷል። ቫይረሱ አሜሪካ መግባቱ ተረጋግጧል። ባለስልጣናትም አሁን ቫይረሱ በከፍተኛ ደረጃ እየተዛመተ ያለበት ወቅት መሆኑን አምነው ቻይና ከፍተኛ ክትትል ማድረግ እንዳለበት አስጠንቅቀዋል። ትናንት በተደረገው ምርመር መሰረት በቫይረሱ ዙሪያ አንድ ተጨማሪ ግኝት ተገኝቷል። ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ ተረጋግጧል። ይህ ደግሞ ሁኔታውን እጅግ ውስብስብና አደገኛ ያደርገዋል ተብሎ ተሰግቷል። 'የአደጋው ፍጠነት' ቫይረሱ ከተከሰተ በኋላ በመንግሥት ደረጃ ትናንት በተሰጠው ይፋዊ መግለጫ፤ የቻይና ምክትል የጤና ሚንስትር እንዳረጋገጡት የቫይረሱ ዋነኛ መተላለፊያ በመተንፈሻ አካላት አማካኝነት ነው ብለዋል። ቫይረሱ ከየት እንደመጣ ለማወቅ የሚደረገው ጥረት እስካሁን ምንም ውጤት አላስገኘም። በተለይ ሰሞኑን የቻይና አዲስ ዓመት የሚከበርበት ወቅት መሆኑና በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ውጭ አገራት የሚጓዙ በመሆናቸው የቫይረሱን ስርጭት ያፈጥነዋል በማለት ባለስልጣናት ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። የአዲስ ዓመት በዓሉ በሽታውን ማስፋፋት ብቻ ሳይሆን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ሂደት አስቸጋሪ እንደሚያደርግም ምክትል ሚንስትሩ ስጋታቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም በሽታውን ለመቆጣጠር ሲባል ጠንከር ያሉ ርምጃዎች ሊወሰዱ ይችላሉ ተብሏል። በውሃን ግዛት ሰዎች እንዳይሰሰባሰቡ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሲሆን የዶሮና ሌሎች የዱር እንስሳት ግብይትም ለጊዜው ታግዷል።
news-41157846
https://www.bbc.com/amharic/news-41157846
የከተሜን ህይወት ቀላል ለማድረግ ጤፍን ፈጭቶ መሸጥ!
ቃልኪዳን በለጠ ከጥቂት ወራት በፊት ሥራ የጀመረው አነስተኛ የንግድ ድርጅቷ ጤፍን እየፈጨ በ5፣ በ10 እና በ25 ኪሎዎች ለተጠቃሚዎች እያደርሰ ይገኛል።
ባለፉት ዓመታት ከከተማ የአኗኗር ዘይቤ መለወጥ ጋር በተያያዘ ልዩ ልዩ የባልትና ውጤቶችን በተለያዩ መጠኖች አዘጋጅቶና አሽጎ መሸጥ እየተለመደ መጥቷል። ይሁንና ይህ ልማድ ለአያሌ ዘመናት ዐብይ ዕለታዊ ምግብ ሆኖ እስከዛሬ በዘለቀው ጤፍ ላይ እምብዛም ሲተገበር አይታይም ነበር። በተለምዶ ጤፍ በጥሬውና በብዛት የሚሸመት በመሆኑ የመግዛት አቅም ለሌላቸው ሰዎች አስቸጋሪ ነው የምትለው ቃልኪዳን፤ ይዛ የቀረበችው ምርት በገንዘብ እንዲሁም በጊዜ ላይ የሚፈጠርን ጫና የሚቀርፍ አማራጭ እንደሆነ ታምናለች። ከሁለት ዓመታት በፊት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመረቀችበት የሙያ ዘርፍ ጋዜጠኛነት ቢሆንም አሁን ስምንት ሰራተኞች ያሉትን ሮያል ባልትና ብላ የሰየመችውን አነስተኛ የንግድ ድርጅት ትመራለች። በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ተፈላጊ የሆነውን ጤፍ አዘጋጅቶና መጥኖ ማቅረብ ዘመናዊ ሕይወትን የማቀላጠፍ ሚና ይኖረዋል ትላለች ቃልኪዳን። ''ገብያ ድረስ ሄጄ ጤፍ መግዛት ወይም ወፍጮ ቤት በመሄድ ጊዜዬን ማባከን አልፈልግም፤ ለዛም ነው የከተማው ሰው ከመደብሮች ውስጥ ሳሙና ወይም ዘይት ገዝተው እንደሚሄዱት ሁሉ ጤፍንም በሚፈልጉት መጠን እንዲያገኙ እድሉን የፈጠርኩት'' ብላለች። የከተሜን ህይወት ቀላል ለማድረግ ጤፍን ፈጭቶ መሸጥ! ቃልኪዳን የመሰረተችው ዓይነት ምርትን የሚያቀርቡ ድርጅቶች መስፋፋት ዋነኛው ትሩፋት ተጠያቂነት ነው ትላለች። ''ይህም ተጠቃሚዎች በሚገዟቸው የምግብ ምርቶች ላይ መተማመን እንዲኖራቸው ያደርጋል። እኔም ለማቀርበው ምርት ጥራት ሃላፊነቱን እወስዳለሁ'' ስትል ጨምራ ተናግራለች። ከአንድ ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ጤፍን በሚፈጩበት ወቅት ባዕድ ነገሮችን ቀላቅለዋል የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው መዘገቡ ይታወሳል። ያጋጥሟት ችግሮች ''ሥራውን በጀመርኩበት ጊዜ የጤፍን አይነቶችን ለይቼ ለማወቅ እቸገር ነበር። ከዚህ በላይ ግን ከብዶኝ የነበርው ከጤፍ ደላሎች ጋር አብሮ መስራት ነበር። ለዚህ ችግር መፍትሄ ያደረኩት ደግሞ ጥሩ የጤፍ አቅርቦት በሚገኝባቸውን ቦታዎች፤ አነስተኛ መጋዘኖችን ተከራይቼ በቀጥታ ከገበሬዎች ጤፉን በመግዛት አስፈላጊ በሚሆን ጊዜ ወደ አዲስ አበባ አጓጉዛለሁ'' ትላለች። ቃልኪዳን ለጀማሪ ድርጅቷ ትልቅ እቅድ አላት፤ ''ጤፍ ከኢትዮጵያ ውጪም ተፈላጊነቱ እየጨመረ በመምጣቱ፤ ይህ ለእኔ የንግድ ሥራ መልካም አጋጣሚ ነው። እድሉ ከተመቻቸም በአጭር ጊዜ ውስጥ የጤፍ ዱቄትን ወደ ውጪ የመላክ እቅድ አለኝ'' ስትል ትናገራለች። ልዕለ-፥ምግብ ጤፍ በውስጡ በያዛቸው ጤናማ ንጥረ ነገሮች ምክንያት በብዙ ቦታዎች ተመራጭ እየሆነ ነው። ተወዳጅነቱ በአንድ በኩል ግሉተን ከሚባለው ንጥረ ነገር ነፃ በመሆኑ እንዲሁም በፕሮቲን እና በካልሲዬም ከመበልጸጉ የሚመነጭ ነው። አንዳንዶች እንዲያውም "አዲሱ ልዕል-ምግብ" እያሉ ያወድሱት ይዘዋል። በዚህም ምክንያት እንጀራ በልዩ ልዩ የዓለም ክፍሎች እየታወቀ ነው። ይሁንና ከባህልና በዘመናት ከዳበረ ልምድ በመነሳት በበርካታ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ እንጀራን ከመግዛት ይልቅ በቤት ውስጥ ጋግሮ መጠቀምን ይመርጣሉ። ስለዚህ ጤፍን ገዝቶ፣ አዘጋጅቶ፣ አስስፈጭቶና ጋግሮ አስከ ማቅረቡ ድረስ ያለው ከባድ ሃላፊነት በሴቶች ትከሻ ላይ ይወድቃል። ቃልኪዳን በጀመረችው ሥራ በርካታ ሴቶች ጤፍን ለምግብ በማዘጋጀት በኩል ያለባቸውን የሥራ ጫና በግማሽ ሊቀንስ ይችላል ብላ ታምናለች።
news-55086097
https://www.bbc.com/amharic/news-55086097
ትራምፕ መሸነፋቸው አምነው ሊቀበሉ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጡ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጆ ባይደን መሸነፋቸውነ ሊቀበሉ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጡ።
ትራምፕ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ "ጆ ባይደን በ 'ኤሌክቶራል ኮሌጅ' የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆኑ ከተረጋገጠ መሸነፌን ልቀበል እችላለሁ" ብለዋል። "ኤሌክቶራል ኮሌጅ" የሚባለው ከየግዛቱ የተወከሉ የዲሞክራት ፓርቲ ተወካዮች በአንድ ተሰብስበው በመደበኛ ሁኔታ ለተመራጩ ፕሬዝዳንት ድምጽ የሚሰጡበት ኩነት ነው። እንደሚታወቀው አሜሪካዊያን ድምጽ የሚሰጡት በቀጥታ ለፕሬዝዳንት እጩዎች ሳይሆን ለግዛት ወኪሎች ነው። የግዛት ወኪሎች ቁጥር የሚወሰነው ደግሞ በግዛቱ የሕዝብ ብዛት ነው። እነዚህ የግዛት ወኪሎች በየግዛቱ ሕዝብ የሰጣቸውን ድምጽ በአንድ ተሰብስበው ለተመረጠው ፕሬዝዳንት ሲሰጡ የተመራጭ ፕሬዝዳንቱ ፕሬዝዳንት መሆን ፍጻሜ ይሆናል። የግዛት ምርጫ ተወካዮች ግን የግድ ሕዝብ ምረጥልኝ ብሎ የሰጣቸውን ድምጽ መከተል አይገደዱም። ትራምፕ ትናንት ሐሙስ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ በኖቬምበር 3 የተደረገውን ምርጫ ውጤት መቀበል ቀላል እንዳልሆነ ደጋግመው ተናግረዋል። ምርጫው ድብን ያለ መጭበርበር የነበረበት ነው ሲሉም በመረጃ ያልተደገፈ ክሳቸውን በድጋሚ አስተጋብተዋል። በኖቬምበሩ ምርጫ ጆ ባይደን 306 የግዛት ወኪሎችን (ኤሌክቶራል ኮልጅ) ድምጽ በማግኘት ዶናልድ ትራምፕን በማያሻማ ልዩነት አሸንፈዋል። ዶናልድ ትራምፕ ያገኙት ኤልክቶራል ኮሌጅ ድምጽ 232 ብቻ ነው። ሆኖም ይህ የአሐዝ ልዩነት ሁለቱ ተፎካካሪዎች በየግዛቶቹ የነበራቸውን ተቀራራቢ ድምጽ አያሳይም። ይህም የሆነው በአሜሪካ ምርጫ አካሄድ በአንድ ግዛት በርካታ ቁጥር ያገኘው እጩ ሁሉንም ለግዛቱ የተመደቡ የወኪሎችን ድምጽ ቁጥሮች ጠቅልሎ ስለሚወስድ ነው። ይህን አሰራር የማይከተሉት የአሜሪካ ግዛቶች ሁለት ብቻ ናቸው። አንድ እጩ አሸናፊ ለመሆን የሚያስፈልገው ኤሌክቶራል ድምጽ 270 ነው። የግዛት ወኪሎች (ኢሌክተርስ) በሚቀጥለው ወር ተገናኝተው የምርጫ ሂደቱን መርሐግብር የሚያሟላውን ኩነት ይፈጽማሉ፤ ይህም በአንድ ቦታ ተገናኝቶ የግዛታቸው ሕዝብ የሰጣቸውን ድምጽ ለተመራጩ ፕሬዝዳንት መስጠት ነው። ትራምፕና ጠበቆቻቸው እንደ ፔንሲልቬኒያ ባሉ ወሳኝ ግዛቶች ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል የክስ ፋይል ሲከፍቱ ነበር የሰነበቱት። ሆኖም በአብዛኛዎቹ ግዛቶች የትራምፕና ጠበቆቻቸው ክሶች "ውሀ የሚቋጥሩ አይደሉም" በሚል ውድቅ ተደርገውባቸዋል። በዚህ ሳምንት መጀመርያ ነበር ትራምፕ ለመጀመርያ ጊዜ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ወደ ዋይት ሐውስ የሚገቡበት ሂደት እንዲጀመር ይህንኑ ሥራ ለሚያቀላጥፈው መሥሪያ ቤት ይሁንታን የሰጡት። በሚሊዮን የሚቆጠር በጀትም ለዚሁ መሥሪያ ቤት ለቀዋል። ይህ ዘግይቶ የመጣው የትራምፕ መለሳለስ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአገር ምስጢር የሚባሉ መረጃዎችን በየሰዓቱ እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ሆኗል። ሐሙስ ዕለት ትራምፕ ከጋዜጠኞች የተነሳላቸው አንዱ ጥያቄ የግዛት ወኪሎች (ኤሌክቶሬትስ) ለባይደን ድምጽ ከሰጡ ዋይት ሐውስን ይለቃሉ ወይ የሚል ነበር። ትራምፕ ሲመልሱም፥ "እንዴት አለቅም፣ እለቃለሁ እንጂ፣ እናንተም ይህን ታውቃላችሁ" ብለዋል። ሆኖም ትራምፕ ይህን ካሉ በኃላ አስከትለው፣ "የግዛት ወኪሎቹ ግን ለባይደን ድምጽ ከሰጡት ስህተት ነው የሚሆነው" ሲሉ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነገር ተናግረዋል። "ሽንፈቴን መቀበል የከበደኝ ምርጫው በስፋት መጭበርበሩን ስለዋውቅ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። በጆ ባይደን የፕሬዝደንታዊ ክብረ በዓል ይገኙ እንደሆነ ተጠይቀው ትራምፕ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። በአሜሪካ ታሪክ አንድ ተሸናፊ ፕሬዝዳንት ሽንፈትን ውጦ ለመቀበል ሲያንገራግር ትራምፕ ምናልባትም የመጀመርያው ሳይሆኑ አይቀርም።
news-52896405
https://www.bbc.com/amharic/news-52896405
"ተቃውሞዎቹ እውነተኛ የለውጥ መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ" ባራክ ኦባማ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የጆርድ ፍሎይድን ሞት ተከትሎ እየተካሄዱ ያሉ ተቃውሞዎች ፖሊስ ማሻሻያ እንዲያደርግ እውነተኛ የለውጥ መነሻዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናገሩ፡፡
የቀድሞ ፕሬዚደንቱ፤ የተቃውሞ ሰልፎች ለአስርት ዓመታት የዘለቀውን የፖሊስ አሰራሮች እና በአገሪቷ ሰፊ የወንጀል ፍትህ ሥርዓትን የማሻሻል ችግሮች እውነተኛና ሕጋዊ ስጋቶችን ይወክላሉ ብለዋል፡፡ ኦባማ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ያመሰገኑ ሲሆን "እነርሱ የእኛን ክብርና ድጋፍ ይገባቸዋል" ብለዋል፡፡ ሆኖም ግጭት የቀሰቀሱ የተወሰኑ ሰዎችን ድርጊት አውግዘዋል፡፡ ሰዎች ከፖለቲካና ከተቃውሞ መምረጥ የለባቸውም ያሉት ኦባማ ሁለቱንም ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡ አክለውም "ግንዛቤ ለመፍጠር ማነሳሳት አለብን፤ ለለውጥ እርምጃ የሚወስዱ ዕጩዎች መምረጣችንን ለማረጋገጥ መደራጀት እና ድምጻችንን መስጠት ይገባናል፡፡" ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ኦባማ በመጨረሻም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ዘርና አካባቢ ሳይለይ የተካሄዱ ከፍተኛ የወጣቶች እንቅስቃሴ ተስፋ እንደሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ "ወደፊት በዚሁ ከቀጠልን ምክንያታዊ የሆነ ቁጣችንን ወደ ሰላማዊ፣ ዘላቂነት ያለው እና ውጤታማ ድርጊት መለወጥ እንችላለን፡፡ ይህ ጊዜ ከፍ ያሉ ሃሳቦቻችን ዳር ለማድረስ በአገራችን ረዥም ጉዞ የእውነተኛ ለውጥ ጅማሮ ሊሆን ይችላል" ብለዋል ኦባማ ባለፈው ሳምንት በሜኔሶታ በነጭ ፖሊስ ቁጥጥር ሥር በግፍ በሞተው የ46 ዓመቱ ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ምክንያት በርካታ የአሜሪካ ግዛቶች በተቃውሞዎች እየተናጡ ነው። በሌሎች የዓለም አገራት ከፍተኛ ቁጣ ተቀስቅሷል፡፡ የተቃውሞ ሰልፎችም እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ የግለሰቡን ሞት ተከትሎ አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የጥቁሩ አሜሪካዊ ሞት ፖሊስ ኃይልን ከመጠቀሙ ጋር በፍጹም የሚያያዝ አይደለም ሲሉ መዘገብ ጀምረው ነበር። አንዳንዶች እንዲያውም የሞተው በራሱ የጤና ችግር ነው እስከማለት ደርሰው ነበር። ይሁን እንጅ በሟች አስከሬን ላይ ምርመራ ሲያደርግ የቆየው የሕክምና ተቋም ጆርጅ ፍሎይድ የተገደለው በሰው ምክንያት ትንፋሽ አጥሮት እንደሆነ ይፋ አድርጓል።
news-54776440
https://www.bbc.com/amharic/news-54776440
የአሜሪካ ምርጫ፡ ትራምፕ እና ባይደን የመጨረሻ ሰዓት ቅስቀሳ እያደረጉ ነው
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን እሁድ ዕለት የመጨረሻ ቅስቀሳዎቻቸውን ለማካሄድ ወደተለያዩ የአሜሪካ ክፍሎች ተጉዘዋል።
ፕሬዝደንት ትራምፕ በአገሪቱ የሚገኙ አምስት ጦርነት የተካሄደባቸውን ቦታዎች የጎበኙ ሲሆን፤ ጆ ባይደን ደግሞ ፔንሲልቬኒያ ውስጥ የምረጡኝ ቅስቀሳቸው በማካሄድ ንግግር አድርገዋል። የዴሞክራቲክ ፓርቲው እጩ ከማክሰኞ በፊት እየወጡ ባሉ መረጃዎች መሰረት በአጠቃላይ ከትራምፕ በተሻለ ድምጽ እያገኙ እንደሆነ እየተገለጸ ነው። ነገር ግን ወሳኝ በሚባሉ ግዛቶች ያላቸው ብልጫ እምብዛም ስላልሆነ የምርጫውን ውጤት ሊቀየር ይችላል ተብሏል። . ከነገ በስትያ አሸናፊው በሚለየው የአሜሪካ ምርጫ በሕዝብ አስተያየት ማን እየመራ ነው? . ዋይት ሀውስ በዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ንግግር ተቆጣ . ኢትዮጵያ በትራምፕ የህዳሴ ግድብ አስተያየት ላይ ያለመ የተቃውሞ ፊርማ ልታሰባስብ ነው ከ90 ሚሊየን በላይ ሰዎች በፖስታ ከወዲሁ ድምጻቸውን የሰጡ ሲሆን፤ በአገሪቱ ታሪክ በፖስታ ይህን ያክል ቁጥር ያለው ዜጋ ሲመርጥ ይህ ከፍተኛው ነው። ምናልባት መላው ዓለምን እያስጨነቀ የሚገኘው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ለዚህ ምክንያት እንደሆነም ተገምቷል። አሜሪካ እስካሁን ከየትኛውም የዓለም አገር የሚበልጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን አስመዝግባለች። ባሳለፍነው ቅዳሜ ብቻ 99 አዲስ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተዘግቧል። የአሜሪካ ከፍተኛ የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የኮሮናቫረስ ስርጭትን በመቆጣጠር ረገድ የወሰደውን እርምጃ የተቹ ሲሆን፤ ዋይት ሀውስ ደግሞ ንግግራቸው ፖለቲካዊ አላማ ያለው ነው ሲል ከሷል። ዶናልድ ትራምፕ በምረጡኝ ዘመቻቸው የመጨረሻዎቹን አምስት ግዛቶች አዳርሰዋል። ሪፐብሊካኑ ፕሬዝደንት እሁድ በእጅጉ የተጨናነቀ ጉዟቸውን አድርገዋል። በመጀመሪያ በሎዋ ሰልፈኞችን ያገኙ ሲሆን፤ ሚቺጋን እና ሰሜን ካሮላይናም ሄደዋል። በመቀጠል ጆርጂያ እና ፍሎሪዳ ግዛቶችን አዳርሰዋል። እነዚህ ሁሉም ግዛቶች በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ከፍተኛ ፉክክር የሚካሄድባቸው ናቸው። ፕሬዝዳንቱ በሚቺገን ለሚገኙ ደጋፊዎቻቸው ንግግር ሲያደርጉ ''በእኔ አመራር የአሜሪካ ምጣኔ ሀብት እስከዛሬ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እያደገ ነው'' ሲሉ ተደምጠዋል። ከኮሮናቫይረስ ጋር በተያያዘ ደግሞ አሜሪካውያን ''ከአደገኛ የባይደን የእንቅስቃሴ ገደብና ደህንነቱ ከተጠበቀ ክትባት'' መካከል መምረጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጉዳይ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ጆ ባይደን መካከል ዋነኛ ከሚባሉት የመከራከሪያ ነጥቦች አንዱ ከሆነ ቆይቷል። ጆ ባይደን ምርጫውን ካሸነፉ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ሊጥሉ እንደሚችሉ በተደጋጋሚ ጠቁመዋል። ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ መጣል የአሜሪካን የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ ይከተዋል ሲሉ ተደምጠዋል። ዴሞክራቱ ባይደን በፊላደልፊያ በነበራቸው ቅስቀሳ ወቅት ለጥቁር አሜሪካውያን ንግግር አድርገዋል። በአሜሪካ ያለውን ''መዋቅራዊ ዘረኝነት'' እንደሚዋጉ የገለጹ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕን ደግሞ ከቫይረሱ ስርጭት ጋር በተያያዘ ወረፍ አድርገዋቸዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሰጡት ምላሽ በብዙዎች ዘንድ እንዲተቹ አድርጓቸዋል። ትራምፕ መጋቢት ላይ በወረርሽኙ ምክንያት ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲደነግጉ ተቀባይነታቸው ጨምሮ ነበር። 55 በመቶ አሜሪካውያን በወቅቱ ድምፃቸውን ለእሳቸው ሊሰጡ እንደሚችሉ አንድ ድምፅ ሰብሳቢ ድርጅት አሳውቆ ነበር። ነገር ግን በቅርቡ የተሰበሰበ አንድ ድምፅ እንደሚጠቁመው የሪፐብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች ጭምር ትራምፕን ፊት ነስተዋቸዋል። ለዚህም ነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጭምብል መልበስን ጨምሮ በወረርሽኙ ላይ ያላቸውን አቋም እያለሳለሱ ያሉት ይላሉ ባለሙያዎች።
53852370
https://www.bbc.com/amharic/53852370
ጃዋር መሐመድ፡ እነ አቶ ጃዋር መሐመድ ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸው ተገለፀ
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በትናንት ውሎው በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ እና 14 ተጠርጣሪዎች የቅድመ ምርመራ መዝገብ ባለፈው ቀጠሮ የተሰጡ ትዕዛዞችን አፈፃፀምና የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ነበር ትናንት፣ ሐሙስ (ነሐሴ 14 2012) ቀጠሮ የያዘው።
በትናንትናው ዕለትም ባለፈው ቀጠሮ ተሰጥተው ከነበሩ ትዕዛዞች አንደኛው ተጠርጣሪዎች የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግላቸው የሚል ነበር። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም ከኢትዮጵያ ጤና ኢንስቲትዩት የተላከ የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤት ማስረጃን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል። በማስረጃው መሠረት አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ ሃምዛ አዳነ (ቦረና) እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃ ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸው በችሎቱ ላይ ተነግሯል። በሌላ በኩል፣ በሌላ ቀጠሮ ትዕዛዝ ተሰጥቶበት የነበረው የአቶ ጃዋር መሐመድ የሕክምና ጉዳይ ነበር። ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሐመድ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። አቶ ጃዋር መሐመድ በትናንቱ ችሎት ሕክምና እንዳላገኙ እና አሁንም እየታመሙ እንደሆነ "ምግብ ስበላ ያስመልሰኛል፤ ያስቀምጠኛል" በማለት የጤንነታቸውን ሁናቴ አስረድተዋል። አቶ ጃዋር ለህይወታቸው ካላቸው ስጋት የተነሳ በማያውቁት ሃኪም መታከም እንደማይፈልጉ ጨምረው ተናግረዋል። በተለይ "ሃጫሉ ሞቷል፤ ጃዋር ነው የቀረው እየተባለ ነበር። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም ህይወቴ ላይ ስጋት ስላለ ነው ጥብቅ ጥበቃ እያደረገልኝ ያለው፤ እኔም የመንግሥት የሕክምና ተቋማትን ንቄ ሳይሆን ለሕይወቴ ካለኝ ስጋት አንጻር ነው በግል ሀኪሜ መታከም የፈለግሁት" ሲሉ አስረድተዋል። ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጀዋር መሐመድ ሰኞ ዕለት መርማሪ ፖሊስ እና አቃቤ ሕግ እርሳቸው ጋር በመገኘት የግል ሐኪማቸውን ጠርተው መታከም እንደሚችሉ ነግረዋቸው የነበረ ቢሆንም በወቅቱ ግን የሐኪማቸው ስልክ ስላልነበራቸው በነጋታው መጥተው እንዲያክሟቸው ቢጠሯቸውም እንዲያክሟቸው እንዳልተፈቀደ እና እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ አቃቤ ሕግ "በወቅቱ አስቸኳይ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ከነበር ሐኪማቸውን ጠርተው እንዲታከሙ ነግረናቸው ነበር። ይሁን እንጂ ስልካቸው የለኝም በማለት ሊታከሙ አልቻሉም። ከዚያ ውጪ ግን ባለው ደንብ መሰረት ነው መታከም ያለባቸው" በማለት ለችሎቱ አስረድቷል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም አቶ ጃዋር መሐመድ በፌደራል ፖሊስ ሪፈራል ሆስፒታል ሁኔታዎችን ማመቻቸቱንና እዚያ የሚታከሙ ከሆነም "ለሕይወታቸው ዋስትና" እንደሚሰጥ ተናግሯል። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ የሕገ-መንግሥቱን አንቀጽ 21 በመጥቀስ፣ አቶ ጃዋር መሐመድ በግል ሐኪማቸው የመታከም መብት እንዳላቸው ይህም እንዲፈፀም ትዕዛዝ ሰጥቷል። በሌላ በኩል በተጠርጣሪዎች በጠበቆቻቸው በኩል እንደ ቅሬታ ሲነሳ የነበረው የካሜራ ጉዳይ ነው። ይህም ጠበቆች ደንበኞቻቸውን የሚያናግሩበት ስፍራ ላይ ምስልና ድምጽ የሚቀርጽ ካሜራ በመገጠሙ ምስጢራቸው በተጠበቀ መልኩ ደንበኞቻቸውን ማናገር እንዳልቻሉ ነሐሴ 11 2012 በነበራው የችሎት ውሎ ላይ ተናግረው ነበር። ፍርድ ቤቱም ጠበቆች ደንበኞቻቸውን ምስጢራቸው በተጠበቀ መልኩ ማግኘት እንዲችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ ጠበቆች ትናንት ለችሎቱ እንዳስረዱት፣ ደንበኞቻቸውን ለማነጋገር ሰኞ፣ ረብዑ እና አርብ ቀጠሮ እንደተያዘላቸው ገልፀው ረብዑ እለትም ወደ ስፍራው ባመሩበት ወቅት ካሜራው እንደተገጠመ መሆኑን መመልከታቸውን ገልፀው ስልክ ቁጥራቸውን ትተው ሲስተካከል እንዲጠሯቸው በመንገር መመለሳቸውን ገልፀዋል። በእለቱም (ረብዑ 13/2012) ወደ አስር ሰዓት አካባቢ ተደውሎላቸው መጠራታቸውን፣ ይሁን እንጂ በመምሸቱ የተነሳ ደንበኞቻቸውን ሳያነጋግሩ መመለሳቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለችሎቱ ተናግረዋል። "ዛሬ እንዳነጋግራቸው ነው ተነጋግረን የተመለስነው፤ ዛሬ ጠዋት ስንሄድ ደግሞ ያለ ቀናችሁ ነው የመጣችሁት ገብታችሁ ማናገር አትችሉም ተብለን ተመልሰናል እና ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እያከበረ አይደለም" በማለት እንዲስተካከልላቸው በመጠየቅ ለችሎቱ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። ፖሊስ በበኩሉ የተገጠመው ካሜራ ቤተ መጻህፍትን ለመጠበቅ እንደሆነ በመናገር፣ ጠበቆች ከደንበኞቻቸው ጋር እንዲገናኙ ሌላ ስፍራ ማመቻቸታቸውንና መገናኘታቸውን ለዚህም ደግሞ ጠበቆች ወደ ቅጽር ግቢው ገብተው ደንበኞቻቸውን ሲያናግሩ የፈረሙበትን መዝገብ ማቅረብ እንደሚችሉ ለችሎቱ ተናግሯል። ይሁን እንጂ ጠበቆች "ከዚህ በፊት በነበረው አሰራር ገብተን ደንበኞቻችንን አናግረን ስንወጣ ነው የምንፈርመው አሁን ገና ደንበኞቻችንን ሳናገኝ እንድንፈርም ይደረጋል፤ ገና ወደ ውስጥ ስንገባ፥ ሳናገኛቸው እየተመለስን ነው" ብለዋል። ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አድምጦ፣ ጠበቆች ደንበኞቻቸውን ምስጢሩ በተጠበቀበት ስፍራ ማግኘት አለባቸው። ይህም መፈፀም አለበት፤ ይህ ካልተፈፀመ ግን ሕጋዊ ርምጃ እንደሚወስድ በመግለጽ ውሳኔ ሰጥቷል። የጋዜጠኛ መለሰ አቤቱታ እና የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ፍርድ ቤቱ ከዚህ ቀደም በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የቅድመ ምርመራ መዝገብ ሥራ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች በሙሉ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ የኦኤምኤን ጋዜጠኛው አቶ መለሰ ዲሪብሳን ጨምሮ በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ስር ለሚገኙ ለአራት ሰዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራው አለመካሄዱን ጠበቃው አቶ ዋቤ ሐጂ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ መለሰ፤ "ከእኛ ጋር ታስረው የነበሩ ሰዎች በኮሮና ተይዘዋል። ፍርድ ቤቱም ከዚህ ቀደም ምርመራ እንዲደረግልን አዞ ነበር። ይሁን እንጂ እስካሁን ምርመራ አልተደረገልንም። ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እያከበረ አይደለም" ሲሉ ለችሎቱ አቤቱታቸውን አቅርበዋል። ከዚህ በተጨማሪም አቶ መለሰ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ቤተሰቦቻቸውን በስልክ እያገኙ መሆኑን እና እርሳቸው ግን ይህን መከልከላቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። በስተመጨረሻም ችሎቱ የተጠርጣሪዎች እንዲሁም የአቃቤ ሕግ አቤቱታ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት እንዲሁም ደግሞ የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለነሐሴ 18 2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
news-56726062
https://www.bbc.com/amharic/news-56726062
ኪም ካርዳሺያን እና ካንያ ዌስት ከፍቺ በኋላ ልጆቻቸውን በጋራ ለማሳደግ ተስማሙ
ካንዬ ዌስት ከኪም ካርዳሺያን ያፈራቸውን አራት ልጆቹን በስምምነት ለማሳደግ ተስማማ።
ይህ የተሰማው ካርዳሺያን ሰባት ዓመት ከቆየችበት ትዳር እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር የካቲት 19/2021 ፍቺ ለመፈፀም የሚያስችላትን ፋይል መክፈቷን ተከትሎ ነው። አሜሪካዊው ራፐር ካንዬ እና የቴሌቪዥን እውናዊ ትርዒት ኮከቧ ኪም ካርዳሺያን ትዳራቸውን ለማፍረስ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል። ካንዬ ዌስት እና ካርዳሺያን ሁለት ኖርዝ እና ቺካጎ የተሰኙ የሰባት እና ሦስት ዓመት ሴት ልጆች፣ ሴይንት እና ሳላም የሚባሉ የአምስት ዓመት እና የሁለት ወር ወንድ ልጆችን አፍርተዋል። ካርዳሺያን ለችሎቱ እንዳስገባችው አቤቱታ ከሆነ ሁለቱም ጥንዶች ትዳራቸውን ከመመስረታቸው በፊት በገቡት ስምምነት መሰረት ሀብታቸውን ለይተው ሲኖሩ ነበር። ጥንዶቹ በየተሰማሩበት ዘርፍ ዝናን ያተረፉ ሲሆን ትዳራቸውም አድናቂዎቻቸው በቅርበት የሚከታተሉት ነበር። የአርባ ዓመቷ ካርዳሺያን ዝናን ያተረፈችው እኤአ በ2007 እርሷና ቤተሰቧ ላይ የሚያተኩር 'ኪፒንግ አፕ ዊዝ ካርዳሺያን' የተሰኘ የቴሌቪዥን እውናዊ ትርዒት ላይ መቅረብ ከጀመረች በኋላ ነው። ትርዒቱ በተከታታዮች ዘንድ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈ ሲሆን፣ የመጨረሻው ምዕራፍ የሚቀጥለው ዓመት እንደሚቀርብ ታውቋል። ትዕይንቱ በ14 ዓመታት ቆይታው ኪምና ቤተሰቧን በከፍተኛ ሁኔታ አበልጽጓል። ዓለም እንዲያውቃቸውም አድርጓል። ኪም ካርዳሺያን ባለፈው ሳምንት በርካታ ሚሊዮን ዶላሮች የሚያንቀሳቅሱ ሁለት ድርጅቶቿ ከቢሊየነሮች ተርታ አሰልፈዋታል። የ43 ዓመቱ ዌስት፣ በራፕ ሙዚቃ ስምና ዝናን ያተረፈ ሲሆን፣ በፋሽን ዲዛይነርነትም ይታወቃል። ዌስት ባለፈው ዓመት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ለመሆን በግሉ የተወዳደረ ቢሆንም ሳይሳካለት ቀርቷል።
45862788
https://www.bbc.com/amharic/45862788
የሰኔ 16ቱ ጥቃት ተጠርጣሪ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሰጠ
በሰኔ አስራ ስድስቱ ጥቃት ከተጠረጠሩት መካከል አንዱ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ፖሊስ የሚያካሂደውን የምርመራ አጠናቆ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ ሰጠ።
ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተፈጸመውን ቦምብ ጥቃት በማሰተባበር፣ በመምራትና ለቦምብ ፍንዳታ የሚሳተፉ አካላትን በመመልመል የተጠረጠሩት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ባልደረባ በነበሩት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ጉዳይ ላይ ፍርድ ቤት የአንድ ሳምንት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሰጥቷል። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ለመግደል በመሞከር የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ቀጠሮ ተጠየቀ • የዓለምፀሐይ፣ የፍስሃ እና የካሳሁን አዲስ ተስፋ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አንደኛው የወንጀል ችሎት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የፈቀደው ፖሊስ አስር ተጨማሪ ቀናት ምርመራውን ለማጠናቀቅ ፍርድ ቤቱን ከጠየቀ በኋላ ነው። ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ በሦስት ቀናት አሳጥሮ ነው ሰባት ቀናት የፈቀደው። ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል በአቶ ተስፋዬ ኡርጌ ቤት የተገኘው ቦምብ ሰኔ 16/2010 ዓ.ም ጥቃት ከተፈፀመበት ቦንብ አንፃር የቴክኒክ ምርመራ ውጤቱ እንዲቀርብ ያዘዘ ቢሆንም ፖሊስ የምርመራ ውጤቱ ባለመጠናቀቁ ውጤቱን ለማቅረብ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል። ፍርድ ቤቱም የምርመራው ሂደት ስላለበት ደረጃ ማብራሪያ የጠየቀ ሲሆን ፖሊስ የመጨረሻ የቴክኒክ ምርመራ ውጤቱን አጠናቆ በቀጣይ ቀጠሮ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ተጠርጣሪውም በጉዳዩ ላይ ፍርድ ቤቱ ተደጋጋሚ የምርመራ ጊዜ በመስጠቱ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መጠየቁን ተቃውመዋል። ፍርድ ቤቱ ምርመራውን እያካሄደ ያለው ፖሊስ የምርመራውን ውጤት ለጥቅምት 12/2011 ዓ.ም እንዲቀርብ በማሳሰብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
news-50167137
https://www.bbc.com/amharic/news-50167137
በሩዋንዳ ለነፍሰጡር እናቶች የሚሆን የስፖርት እንቅስቃሴ ተጀመረ
ሩዋንዳ ለነፍሰጡር እናቶች የሚጠቅምና በጋራ የሚደረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደጀመረች ተገለጸ።
ለመጀመሪያ ጊዜ በአገሪቱ በተካሄደው በዚህ የነፍሰጡር እናቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ ለቢቢሲ እንደተናገሩት መደሰታቸውንና ባለስልጣናትም ስፖርታዊ እንቅስቃሴው እንዲቀጥል እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። በዋና ከተማዋ ኪጋሊ ውስጥ በተካሄደው የመጀመሪያው የስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ ከ100 በላይ ነፍሰጡር እናቶች የተሳተፉ ሲሆን አላማውም የነፍሰጡር ሴቶችን አካላዊ ሁኔታን በተመለተ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ለመለወጥ መሆኑን አዘጋጆቹ ተናግረዋል። • ፊደል ያልቆጠሩት ኢትዮጵያዊት የቀዶ ህክምና ባለሙያ • በጀርባቸው የሚተኙ ነፍሰጡሮች ህይወት የሌለው ልጅ እየወለዱ ነው አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅትና ስፖርታዊ እንቅስቃሴውን ያስተባበረው መሪ ኔልሰን ሙካሳ እንደገለጹት፤ በርካታ ሩዋንዳውያን አንዲት ሴት ስታረግዝ ከሁሉም አይነት አካላዊ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ አለባት ብለው ያምናሉ። "ነፍሰጡር እናት እንቅስቃሴ የማታደርግ ከሆነ ለራሷና ለተሸከመችው ልጇ ደህንነት በጣም አደገኛ ነው" ብለዋል ሙካሳ። በስፖርታዊ እንቅስቃሴው ላይ ተሳታፊ ከነበሩት ነፍሰጡር እናቶች መካከል አንዷ ሊብሬ ኡዊዜይማና ለቢቢሲ እንደገለጸችው በእርግዝናዋ ጊዜ ፈጽሞ አካላዊ እንቅስቃሴ አድርጋ አታውቅም። "ስላልለመድኩት በጣም ደክሞኝ ነበር፤ ነገር ግን ከሌሎች ነፍሰጡር ሴቶች ጋር አካላዊ እንቅስቃሴን በማድረጌ በጣም ደስተኛ ነኝ" ብላለች። የሰባት ወር እርጉዝ የሆነችው ሩትም ሌሎች ተመሳሳይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍ እንደምትፈልግ ተናግራለች። • የሴቶች የቆዳ ክሬሞች የደቀኑት አደጋ "በጣም ጥሩ ነገር ነው፤ ልምምድ አድርጌያለሁ። ዘና የማለት ስሜት ፈጥሮብኛል፤ በተጨማሪም የጽንሱ እንቅስቃሴም ደስ የሚል ስሜትን ፈጥሮብኛል" ስትል የተሰማትን ገልጻለች። በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ውስጥ የማህጸንና ጽንስ ሃኪም የሆኑት ዶክተር ጂያን ኒይሪንክዋያ ወደ ግል ክሊኒካቸው የሚመጡትን ሁሉም ነፍሰጡር እናቶች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። "የእግር ጉዞ፣ ዋናና ሰዎነትን ማፍታታት ምንም አይነት አሉታዊ ተጽዕኖ በእርጉዝ ሴቶች ላይ የለውም" ይላሉ ዶክተር ጂያን። የስፖርታዊ እንቅስቃሴው አስተባባሪዎች በዝግጅታቸው ላይ ለታደሙ እርጉዝ ሴቶች የሚሆኑና ምንም አይነት የጎንዮሽ ውጤት የሌላቸውን የእንቅስቃሴ አይነቶችን መምረጣቸውን ገልጸዋል። ጨምረውም ወንዶች በዚሁ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
news-56398436
https://www.bbc.com/amharic/news-56398436
በምሥራቅ ጎጃም በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ30 ሰዎች ህይወት አለፈ
በአማራ ክልል ውስጥ በምሥራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ውስጥ ዛሬ፣ ሰኞ ጠዋት በደረሰ ከባድ የመኪና አደጋ የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታወቁ።
አደጋው የደረሰው በዞኑ ውስጥ በሚገኘው በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በቤዛ ብዙሃን ቀበሌ ልዩ ስሙ ቡሃች ተብሎ በሚጠራ አካባቢ እንደሆነ የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር አይችሉህም ዳምጤ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የሞጣ ከተማ ኮምዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት የሐኪም ቤት ምንጮችን ጠቅሶ እንዳስታወቀው ቀደም ሲል 27 የነበረው የሟቾች ቁጥር ወደ 30 ከፍ ብሏል። አደጋ የደረሰው ተጓዦችን አሳፍሮ ከደብረ ታቦር ከተማ በመነሳት ወደ አዲስ አበባ ሲያቀና በነበረ ዋሊያ አውቶብስና ከግንደ ወይን ወደ ሞጣ ይጓዝ በነበረ ቅጥቅጥ አይሱዙ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ መካከል በተፈጠረ ግጭት ነው። አደጋው ዛሬ ሰኞ መጋቢት 6/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡30 ሰዓት አካባቢ ምሥራቅ ጎጃም ውስጥ ቡሃች ከተባለው ቦታ ላይ መድረሱን ኃላፊው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። አደጋው የተከሰተው ሁለቱ ተሽከርካሪዎች መጓዝ ከነበረባቸው የመንገድ መስመር በተቃራኒ በሚሄዱበት ጊዜ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ከግጭቱ በኋላ አይሱዙው ከ150 ሜትር በላይ ከመንገድ ውጪ ወደ ገደል ተንከባሎ መግባቱ ተነግሯል። በአደጋው ከሞቱት ሰዎች መካከል 23ቱ በአይሱዙ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ሲሆኑ፣ ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ የአደጋውን መድረስ ተከትሎ ለዕርዳታ በባጃጅ ተሽከርካሪ ተሳፍረው በቶሎ ለመድረስ ሲጓዙ ተሽከርካሪው ተገልብጦ ለህልፈት የተዳረጉ ናቸው። አንደኛው ሟች ደግሞ በአገር አቋራጭ የዋሊያ አውቶብስ ውስጥ ተሳፋሪ የነበረ ግለሰብ ነው ተብሏል። ኋላ ላይ ሦስት ተጨማሪ ሰዎች በአደጋው መሞታቸው ተገልጿል። ከሟቾች በተጨማሪም በአደጋው ስድስት ሰዎች ከባድ አደጋ ደርሶባቸው ለህክምና ወደ ባሕር ዳር የተላኩ መሆኑን የገለፁት ምክትል ኮማንደር አይችሉህም፣ ሌሎች 17 ሰዎች ደግሞ በሞጣ ሆስፒታል ህክምና እያገኙ ነው ብለዋል። ይህ ከባድ አደጋ የደረሰው ሁለቱም ተሽከርካሪዎች በኩርባ ላይ በከፍተኛ ፍጥነት ሲያሽከረክሩ መሆኑንም ኃላፊው ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተመሳሳይ ዜና ባለፈው ቅዳሜ በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ 51 ኩንታል እህልና 25 ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ መኪና ከሌሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ ተገልብጦ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ ኮምዩኒኬሽን ገልጾ ነበር። በዚህም በሦሰት ቀናት ውስጥ ብቻ በሁለቱ የተሽከርካሪ አደጋዎች ምክንያት የ42 ሰዎች ህይወት ለህልፈት ተዳርጓል። በኢትዮጵያ በሚደርስ የተሽከርካሪ አደጋ ሳቢያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰው ህይወት እንደሚያልፍና የአካል ጉዳት እንደሚደርስ በየዓመቱ የሚወጡ ሪፖርቶች ያመለክታሉ። በቅርቡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋዎችን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት ላይ እንደጠቀሰው ያለፉት ስድስት ወራት በአገሪቱ ውስጥ 20 ሺህ 672 የመንገድ ትራፊክ አደጋዎች አጋጥመዋል። በዚህም መሠረት ካለፈው ዓመት ከሐምሌ 1 ቀን 2012 እስከ ታኅሣስ 30/2013 ዓ.ም ድረስ በደረሱ አደጋዎች የ1 ሺህ 849 ሰዎች ህይወት አልፏል። በስድስት ወራት ውስጥ በትራፊክ አደጋ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ 2 ሺህ 646 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት እንዲሁም 2 ሺህ 565 ዜጎች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል እንደደረሰባቸው የፌደራል ፖሊስ ገልጿል።
news-53190950
https://www.bbc.com/amharic/news-53190950
የጄነራል ሰዓረ እና ሜጀር ጀነራል ገዛኢ የችሎት ክርክር ለቤተሰብ ክፍት እንዲሆን ተፈቀደ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ እንዳስታወቀው በጀነራል ሰዓረ መኮንን እና በሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ የግድያ ወንጀል ችሎት ለቤተሰቦቻቸው ክፍት እንዲሆን መፈቀዱን አስታውቋል።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጀነራል ሰዓረ መኮንን እና በሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ የግድያ ወንጀል ሲካሄድ የነበረው የክርክር ሂደት እንዲቀጥል መወሰኑም ተገልጿል። • "ልባችንም ቤታችንም ጨልሟል" የጀነራል ሰዓረ እና ሜ/ጀነራል ገዛኢ ቤተሰቦች የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ፍርድ ቤቶች በከፊል በመዘጋታቸው ክርክሩ ለጊዜው ተቋርጦ የነበረው ክርክር የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ እንዲቀጥል አቤቱታ በማቅረቡ የምስክር መስማቱን ሂደት ተከሳሽ በማረሚያ ቤት ሆኖ በፕላዝማ እየታገዘ እንዲቀጥል ትዕዛዝ ሰጥቷል። የጀነራል ሰዓረ እና ሜ/ጀነራል ገዛኢ ቤተሰቦች በማኅበራዊ ሚድያ ከሚሰሙት ውጪ ስለጉዳዩ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ግድያው ከተፈጸመ አንድ ዓመት የሞላው ቢሆንም ጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዳልተሰጠው የሚናገሩት የጀነራል ሰዓረ ባለቤት ኮሎኔል ጽጌ አለማየሁ፣ "ሰዓረ፤ ጠበቃ እና ጠያቂ ያጣ ሰው ነው። የሚቆምለት ሰው የለውም፤ እኛ አቅም የለንም። ከእኔ አቅም በላይ ነው። ማን ጋር ተሂዶ አቤት እንደሚባልም አላውቅም፤ ጨንቆኛል" ብለው ነበር። የሜ/ጀነራል ገዛኢ አበራ ባለቤትም፣ ". . .ሰዓረ እና ገዛኢ ትልልቅ መሪዎች ናቸው። የአገሪቱ ጀነራሎች ናቸው። በሥራ ላይ እያሉ ነው የተገደሉት። የፌደራል መንግሥት፣ የመከላከያ እና ደኅንነት ባለበት አገር ትልልቅ መሪዎች ማን ገደላቸው? ለምን? መልስ ማግኘት ይገባን ነበር። ለቤተሰቡ ዝምታው ከግድያው በላይ ነው የሆነብን . . ." ብለው ነበር። • ሰኔ 15 ያጎደለው የአምባቸው ቤተሰብ አክለውም "የማውቀውና ያነጋገረኝ ባለስልጣን የለም፤ እንደተጎዳን፣ ጥቃት እንደደረሰብን፣ ያን የመሰለ ሰው አጥተን በጭንቀትና በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ተረድቶ አይዟችሁ ያለን የለም፡፡ . . . የሚጠይቀኝ ባገኝ የሚሰማኝን እናገር ነበር. . . የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደን" በማለት ታጋይ አበባ ዘሚካኤል ለቢቢሲ ተናግረዋል። የችሎት ክርክሩ ሂደት ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ባሉት ቀናት የተጎጂ ቤተሰቦች እና ጉዳዩን መከታተል የሚፈልጉ ውስን ሚዲያዎች ወይም ግለሰቦች ባሉበት እንደሚቀጥልም ተገልጿል።
45819967
https://www.bbc.com/amharic/45819967
የትናንቱ የ4 ኪሎ ውሎ እና አንድምታው
የትናንቱ የ4ኪሎ ውሎ ለአንዳንዶች መገረምን፣ ለበርካቶች መደናገጥን ፈጥሮ ነበር። በቤተ መንግሥቱን አካባቢው የነበረው ውሎ ምን ይመስል ነበር? መቼ ምን ተከሰተ? አንድምታውስ?
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ ከወታደሮቹ ጋር ሲነጋገሩ ትናንት ከሰዓት ቤተ መንግሥት አካባቢ ያለው ውጥረት ከተሰማ በኋላ የቢቢሲ ዘጋቢ ወደ ቦታው አቅንቶ ነበር። ከዚህ በታች ያሉት ሁኔታዎች የተወሰዱት ከዓይን እማኖች፣ ሪፖርተራችን ከተመለከታቸው እና ለቤተ መንግሥት ቅርብ ከሆኑ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ናቸው። ማለዳ 3:00 ሰዓት አካባቢ ከ4 ኪሎ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደዉ መንገድ ሙሉ በሙሉ ባይባልም ዝግ ነበር። መንገዱ ትምህርት ሚኒስቴር ፊት ለፊት በቆመ የፖሊስ ታርጋ ባለዉ መኪና ነበር የተዘጋዉ። የመንገዱ መዘጋት የትራፊክ መጨናነቅን ፈጥሮ ነበር። አልፎ አልፎ ኮድ 4 ታርጋ ያላቸዉ መኪኖች (ንብረትነታቸው የመንግሥት የሆኑ) እንዲያልፉ ሲደረግ ነበር። • የሰራዊት አባላቱ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይት • ኦነግ ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ማወጁን ገለፀ • የጠቅላይ ሚኒስትሩ 100 ቀናት ማለዳ 4፡30 ገደማ ቤተ መንግሥት አካባቢ በመቶዎች የሚቆጠሩ፤ ቀይ መለዮ የለበሱ ወታደሮች ተሰባስበው ታዩ። ማለዳ 5፡00 አካባቢ ቀይ መለዮ የለበሱት ወታደሮች ቁጥር እየጨመረ መጣ። ከፊሎቹ ወታደሮች ከነትጥቃቸው ነበሩ። ክላሽንኮቭ እና ስናይፐር ከታጠቋቸው የጦር መሣሪያዎች መካከል ይገኙበታል። ዕኩለ ቀን ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ከቦሌ ወደ ቤተ መንግሥት እየተጓዙ ነበር። ቤተ መንግሥት አካባቢ ሲደርሱ የምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠባቂዎች ከመኪና በመውረድ ቀይ መለዮ ከለበሱት ወታደሮች ጋር ሲነጋገሩ ታይቷል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል አመሻሽ ላይ በቴሌቪዥን ብቅ በለው ሁኔታውን እንዳስረዱት ከሆነ ወታደሮቹ ከነ ትጠቃቸው ወደ ቤተ መንግሥት በመዝለቅ ጠቅላይ ሚንስትሩን ማነጋገር እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር። ከነትጥቃቸው ወደ ቤተ መንግሥት መግባት እንደማይችሉ ሲነገራቸውም 'እኛ አንታመንም ወይ? ጠቅላይ ሚንስትሩ የምንወደው መሪ ነው። ችግራችንን ይስማልን'' በማለት ትጥቅ ላለመፍታት አንገራግረው እንደነበር ኮሚሽነሩ አብራርተዋል። ጊዜ ከወሰደ ንግግር በኋላ ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ ጋር ከዚያም በመቀጠል ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ጋር ውይይት አድርገዋል። 10 ሰዓት አካባቢ በአዲስ አበባ ለሰዓታት የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ ነበር። ወታደሮቹ ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ ጋር ፎቶ ሲነሱ ከሰዓት 10 በኋላ ወታደሮቹ መሣሪያቸውን አስቀምጠው ወደ ስብሰባው ገብተዋል። ታጥቀውት የነበረዉ መሣሪያም ተሰብስቦ በወታደር ሲጠበቅ ነበር። ተዘግቶ የነበረው ከ 4 ኪሎ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደዉ መንገድም ሙሉ በሙሉ የተከፈተውም በዚሁ ጊዜ ነበር። "አደገኛ እና የደኅንነቱን ድከምት ያሳየ" ቢቢሲ በስልክ ያነጋገራቸው አንድ የቀድሞ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን ክስተቱን 'የወታደራዊ ደኅንነቱን ድክመት ያሳየና አደገኛ' ሲሉ ገልጸውታል። እኚህ መኮንን እነዚህ ወጣቶች ያነሱት ጥያቄ ከሞላ ጎደል የጠቅላላ ወታደሩን ጥያቄ ሊወክል ይችላል ካሉ በኋላ የሄዱበት መንገድ ግን ከወታደራዊ ጥብቅ ዲሲፕሊ እና ሕግ ያፈነገጠ እንደሆነ አብራርተዋል። ዩኒፎርም በለበሱ ወታደሮች እንዲህ ዓይነት አስገዳጅ ስብሰባ የመጥራት ጉዳይ የማይታመንና አስደንጋጭ ነው ይላሉ መኮንኑ። "የትናንቱ ክስተት የሚነግረን ነገር ወታደራዊ የመረጃ ክፍል ሥራውን በአግባቡ እንዳልሠራ ነው።" እኚህ መኮንን ችግሩ በጥቅሉ የወታደራዊ ደኅንነት የመረጃ ክፍል መሆኑን ሲጠቅሱ ክስተቱ ያደገበትን ሂደት በመዘርዘር ነው። በአሠራር ደረጃ ወታደሮች ለግዳጅ ሲንቀሳቀሱም ኾነ ወደ ካምፓቸው ሲመለሱ የሚሄዱበት መስመር በዘፈቀደ የሚመረጥ እንዳልሆነ ከጠቆሙ በኋላ የወታደር ኮንቮዮች መነሻና መድረሻ፣ ሰዓታቸውም ኾነ እንቅስቃሴያቸው በአዛዦች በኩል ተከታታይ የመረጃ ልውውጥ የሚደረግብት እንደሆነ ያወሳሉ። ወታደሮቹ ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባ ነበር ወይ ተብለው የተጠየቁት መኮንኑ ከዚያ በፊት ማቆም ይገባ ነገር እንጂ "ከገቡ በኋላ ነገሮችን በነሱ ደረጃና ስሜት ወርዶ ማስተናገድ ምንም አማራጭ አልነበረውም" ብለዋል። ያን ስሜታቸውን በመረዳትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገሩን ለጊዜውም ቢሆን በብልሀት ፈተውታል። "የግል ብቃታቸውና ጥበባቸው ረድቷቸዋል" ይላሉ። እኚሁ ከፍተኛ መኮንን እንደሚገምቱት በወጣት ወታደሮቹ የዋህነት ውስጥ ተጠቅሞ ሴራ የጎነጎነ አካል አለ። እንዲህ እንዲያምኑ ያስገደዳቸው ደግሞ በወታደሩ ውስጥ ያለ ጥብቅ የዕዝ ሰንሰለት ነው። ወታደሮቹ ዝም ብለው ድንገት በስሜት ተነሳስተው ወደ ቤተ መንግሥት ሊመጡ የሚችሉበት ዕድል ሊኖር አይችልም ብለው ያምናሉ። የማንቂያ ደወል ወታደራዊ ደኅንነቱ ከዚህ በኋላ ይህ ነገር እንዴት ሊሆን ቻለ? ከጀርባው እነማን ነበሩ? ወደፊት ተመሳሳይ ስሜቶች ቢያቆጠቁጡ እንዴት ማቆም ይቻላል? የትኞቹ የወታደር ክፍሎች ለዚህ የተመቹና "ስሱ" ናቸው የሚለው ላይ ትልቅ ሥራ እንደሚጠብቀው አስገንዝበዋል። "ይህ ነገር ለነገ የሚባል አይደለም። ፋታ የሚሰጥም አይደለም።" ይላሉ ከፍተኛ መኮንኑ። "ከለውጡ በፊት እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ቢፈጠር ምን ዓይነት ወታደራዊ የዲሲፕሊን እርምጃ ሊወሰድ ይችል ነበር?" ሲል ቢቢሲ ጥያቄ ያነሳላቸው እኚህ መኮንን "መጀመርያውኑም የሚሞከርም የሚታሰብም አይሆንም ነበር" ብለዋል። "ወታደሩ አካባቢ ያለው ችግር እነርሱ ከገለጹትም በላይ ነው። ከግዳጅ አፈጻጸም፣ ከትምህርትና ሥልጠና፣ ከውጭ ተልዕኮ እንዲሁም ከማንነት ጋር ተያይዞ የተጎዳ ሠራዊት ነው" ካሉ በኋላ "ቀደም ባለው አሠራር በግምገማ ወቅት ጥያቄዎች ይነሳሉ፤ የሚመለሱበት መንገድ ግን አዝጋሚ ነበር" ብለዋል። መኮንኑ እንደሚያምኑት አሁን የለውጡ መንፈስ ተከትሎ ወጣት ወታደሮቹ ዲሞክራሲውን የሚረዱበት መጠንና መንገድ ስለሚለያይ ለዚህ ተግባር አብቅቷቸዋል። "ወታደርን ወታደር የሚያደርገው ሥነ ሥርዓቱ ነው። አንዴ ሠራዊት ውስጥ ከገባህ ወደድክም ጠላህም የሚያስጠይቅ ነገር ሁሉ ያስጠይቅሀል። ይህ ተግባር እንደዋዛ የተወሰደው አሁን የሽግግር ስሜት ላይ በመሆናችንና ሆደ ሰፊ ለመሆን እየተሞከረ ስለሆነ ነው። አሁን ያለውን መልካም ስሜት እንዳያደበዝዘው ሲባል ጥብቅ እርምጃዎች ላይወሰዱ ቢችሉም ነገሮች በዚህ መንገድ ይቀጥላሉ ማለት ግን አይቻልም።" ብለዋል። ስማቸውን መግለጽ የማይሹት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኑ እንደሚያምኑት ይህ የትናንቱ ክስተት ለወታደራዊ ደኅንነቱ የማንቂያ ደወል ነው።
news-53967063
https://www.bbc.com/amharic/news-53967063
ኢትዮጵያ ፡ ኮቪድ-19 ያሰናከለው ምርጫና ያልተረጋጋው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር
ዓለም አቀፉን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተከትሎ ባይራዘም ኖሮ ባለፈው ቅዳሜ ኢትዮጵያ ውስጥ የምርጫ ቀን ይሆን ነበር።
አንዳንዶች ምርጫው በተራዘመበት ሒደት ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ሲሆን፣ ከናካቴው ምርጫው በመራዘሙ ውሳኔ ላይ አልስማማም ያለ የሚመስለው የትግራይ ክልል የራሱን ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ደፋ ቀና ላይ ነው። ምርጫው መራዘሙ ይፋ ከሆነበት ከወርሃ መጋቢት አንስቶ ምን ዓይነት የፖለቲካ እና የደኅንነት ለውጦች ተከሰቱ ሲል ቢቢሲ የተለያዩ አካላትን አነጋግሯል። ሒሩት ክፍሌ ለእስር ባይታወር አይደለችም። የሃምሳ ዓመቷ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሥራ አስፈፃሚ አባል በህይወት ዘመኗ ለአራት ጊዜያት ያህል እስርን ቀምሳለች። በቅርቡ እንኳ ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት ከተቀሰቀሰው እና ቢያንስ የ170 ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈው ግርግርና ጥቃት ጋር በተያያዘ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በነበረው ሁከት እጇ አለበት ተብላ በቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ ሃያ አንድ ያህል ቀናትን በእስር ቤት አሳልፋለች። "ከቀኑ ስድስት ሰዓት ገደማ ይሆናል" ትላለች ሒሩት የተያዘችበትን ሁኔታ ለቢቢሲ ስታስረዳ፤ "አካባቢው ላይ ያልተለመዱ ሰዎች ይተዩ ነበር፤ እና ሰው ተጠራጥሮ ምንድን ናቸው እነዚህ ሰዎች? ሲለኝ ለማየት ነው የወጣሁት። [. . . ] ወደቤቴ ስመለስ ተከታትለውኝ ተመለሱ፤ [. . . ] ፖሊሶች ነን፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ለጥያቄ ይፈልግሻል አሉኝ" ከዚያም ከሦስቱ ፖሊሶች ጋር ጉዞ መጀመሯን ትናገራለች ሒሩት። እስር ቤት ከገባች በኋላ አንድ ጊዜ ምርመራ እንደተደረገላት፣ በመጀመሪያዎቹ ቀናት ምግብ ከቤተሰብ ይገባላት እንዳይነበር፣ ጠበቃዋን እንዳላገኘችና የምትቀይረው ልብስ እንዳልነበራት ታስታውሳለች። ሒሩት የወርሃ ሰኔውን ነውጥ ተከትሎ ከታሰሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች መካከል መፈታት ከቻሉት ጥቂቶች ውስጥ አንዷ ናት። በብዙዎች በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አጠቃላይ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መራዘሙን ተከትሎ፤ መዘግየቱ የተሻለ ዝግጅት ለማድረግ ዕድል ሊፈጥር ይችላል ብለው ተስፋ ከሰነቁት መካከል መቀመጫውን ኔዘርላንድስ ያደረገው የፖለቲካ እና የደኅንነት ተንታኙ አደም ካሴ አበበ (ዶ/ር) ይገኝበታል። ይሁንና በነባራዊነት የታየው ተደጋጋሚ የፖለቲካ እና የደኅንነት ችግሮች ፈጠው መታየታቸው መሆኑ ተንታኙን ቅር አሰኝቷል። "ቀድሞውኑም ኢትዮጵያ ስሱ የሆነ ሽግግር ላይ ነበረች" የሚለው አደም (ዶ/ር)፤ "የምርጫው መራዘም ለአንዳንድ ተቃዋሚ ቡድኖች አዲስ የሙግት ነጥብ ፈጥሮ ውጥር ብሎ የነበረውን የፖለቲካ እና የደኅንነት ሁኔታ የበለጠ አክርሮታል" ሲል ለቢቢሲ ያስረዳል። "ውሳኔውን ተከትሎም ምርጫ መቼ ይካሄዳል የሚለውን በመወሰን ረገድ ለፌዴራል መንግሥት ብቸኛ የወሳኝነት ዕድል መስጠቱ እንዲሁም ለተቃዋሚዎች በዚህ ሽግግር ወቅት ምንም ዓይነት ይፋዊ የሆነ ሚናን በመንፈጉ ሙቀቱን የበለጠ ጨምሮታል።" የአናሳዎች መብት ተቆርቋሪው ማይኖሪቲ ራይትስ እንዳተተው እንዲሁም በሌሎች ዘገባዎች እንደተገለፀው በነውጡ ወቅት በሕዝብ ብዛት በአገሪቱ ቀዳሚ በሆነው የኦሮሚያ ክልል ብሔር እና ሐይማኖትን ያማከለ ጥቃት ደርሷል፣ ሰዎች ተገድለዋል፣ ንብረታቸውም ወድሟል። ይሄንን ተከትሎም መንግሥት የወሰዳቸው የእስር እርምጃዎች በአንዳንድ በጥቃቶቹ በተደናገጡ ሰዎች ዘንድ ድጋፍን አግኝቶ የነበረ ይመስላል። ይሁንና እርምጃው የተቃውሞን እንቅስቃሴ ያዳክማል ሲሉ የሚያብጠለጥሉትም አሉ። ስመ ጥር አባሎቹ የታሰሩበት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀ መንበር መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር) "ዋናው ነገር መረጋጋትን ወደ አገሪቷ እና ወደ ፖለቲካ ከባቢው መመለስ መሆን አለበት" ይላሉ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ። "ነገር ግን እየተሄደበት ያለው መንገድ ለማናችንም የሚጠቅም አይደለም። ሰዎቹ የታሰሩበት መንገድ በኦሮሞ ወጣት ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ አይመስለኝም። ተቃዋሚን የመጨፍለቅ ሙከራ ተደርጎ የተቆጠረ ነው የሚመስለኝ።" መረራ (ፕሮፌሰር) ይቀጥሉናም "ችግራችን ፖለቲካዊ ነው፤ መንግሥት እየተከለተለ ያለው መንገድ ግን 'የሕግ የበላይነት' የሚለውን ነው፤ ችግራችን የሕግ የበላይነት አልነበረም፤ ችግራችን የፖለቲካችን ቆሞ ቀር መሆኑ ነው። በተለይ ደግሞ ዲሞክራሲያዊ ሽግግርን ለማሳካት የነበረው ተስፋ መክሸፍ ዋጋ እያስከፈለን ነው።" የታሰሩ ሰዎች ረዘም ላለ ጊዜ ክስ ሳይመሰረትባቸው መቆየቱ እና ፖሊስ ወይንም ዐቃቤ ሕግ በሚያቀርቧቸው ተደጋጋሚ የተጨማሪ ቀን ይሰጠን ጥያቄዎች የፍርድ ሒደቱ መጓተቱ ሌላኛው መንግሥት ላይ የሚቀርብበት ትችት ነው። ይህንን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበለት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሰክሬታሪ ቢሮ ለቢቢሲ በላከው የጽሁፍ ምላሽ የደረሰው ውደምት ስፋት እና ጥልቀት ጊዜን የሚወስድ እና አንጡራ ሀብትን የሚጠይቅ ምርመራ መጠየቁን ገልጿል። ይህ የሚከናወነውም አገሪቷ ከዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ግብግብ በተያያዘችበት ወቅት መሆኑን ጨምሮ አስረድቷል። "በታላቅ ጥረት እና ትጋት ሕግ አስከባሪ ተቋማታችን የምርመራ ሒደቱን በመቋጨት ላይ ይገኛሉ" የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት እንደ አብነትም በታዋቂ የፖለቲካ ሰዎች ላይ የምርመራ ሥራ ተጠናቅቆ የቅድመ-ክስ የችሎት ሒደት መጀመሩንም ያነሳል። ይህ የሆነበት ምክንያትም ፖለቲከኞቹ ያላቸውን ገዘፍ ያለ ተፅዕኖ በመጠቀም ምስክሮች ላይ ጫና ሊያሳድሩ ይችላሉ የሚል ስጋት በመፈጠሩ መሆንን ይናገራል። "መንግሥት በቅርቡ በአንዳንድ የፖለቲካ ሰዎች የተለኮሱ የነውጥ ክስተቶች በእርግጥም በዲሞክራሲያዊ ሽግግራችን ላይ አደጋን የደቀኑ ናቸው ብሎ ያመናል" የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ "ኃላፊነት በጎደለው አኳኋን ለሚንቀሳቀሱ፤ አገሪቱን የሚያስተዳድረውን ሕግ ከቁብም ለማይቆጥሩ የተቃውሞ ፖለቲከኞች መንግሥት ምላሽ ሲሰጥ ከፍ ያለ ቁጥብነትን ቢያሳይም፤ እንዲህ ያለው ቁጥበነት ግን ከዚህ ወዲያ የሚኖር አይሆንም" ብሏል። ኢትዮጵያ አሁንም ከፖለቲካዊ ውጥረት የተገላገለች አትመስልም። ከሁለት ሳምንታት በፊት እንኳ በኦሮሚያ ክልል የተቃውሞ ሰልፎች ተስተውለዋል፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ ሰዎች ተገድለዋል፤ ሌሎችም ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የተጠረጠርችበትን ወንጀል የምታስተባብለውና የሦስት ልጆች እናት የሆነችው ሒሩት ክፍሌ ተደጋጋሚ እስርን የምትቀምሰው ከፖለቲካ ተሳትፎዋ ጋር በተያያዘ መሆኑን ታምናለች። ረጅሙ በእስር ቤት ያሳለፈችው ጊዜ ሰባት ዓመታትን ያህል ነው። በወቅቱ የአስራ ዘጠኝ ዓመት እስር ተፈርዶባት የነበረ ቢሆንም ለበርካታ ወራት የዘለቀ ሕዝባዊ ተቃውሞን ተከትሎ በ2010 ዓ.ም የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ከመወሰናቸውም በተጨማሪ በርካታ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና የሐይማኖት መሪዎች ከእስር እንዲፈቱ ሲወሰን እርሷም ለቤቷ በቃች። ወዲያውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ይፋ የተደረጉ የማሻሻያ እርምጃዎችን ስታይ የእስር ዘመን አበቃ ብላ አስባ እንደነበር ትናገራለች፤ አሁን ግን "ብዙም እርግጠኛ አይደለሁም" ትላለች።
43283518
https://www.bbc.com/amharic/43283518
አይ ኤስ በኒጀር የአሜሪካ ወታደሮችን ሞት የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል ለቀቀ
አይ ኤስ እስላማዊ ቡድን ባለፈው ጥቅምት ወር በኒጀር በተሰማሩ የአሜሪካ ፀረ ሽብር ግብረ ሃይል ወታደሮች ላይ በፈጸመው ጥቃት የተገደሉ ወታደሮችን የሚያሳይ ተንቀሳቃሸ ምስል ይፋ አደረገ።
የትዳር አጋሯን በጥቃቱ ያጣች አሜሪካዊት ባሏን ስትሰናበት ተንቀሳቃሽ ምስሉ በእስላማዊ ቡድኑ የመልእክት መቀባበያ ላይ እስካሁን ሳይለቀቅ ለምን እንደዘገየ ግልፅ አይደለም። ተንቀሳቃሽ ምስሉ ከወታደሮቹ በአንዱ የጭንቅላት ቆብ ላይ በተገጠመ ካሜራ የተቀረፀ ነው። ጥቃቱ በኒጀር በሚገኙ የአሜሪካ ፀረ ሽብር ግብረ ሃይል ወታደሮች ላይ በእስላማዊ ቡድኑ መፈፀሙን ለመግለፅ የታለመ ይመስላል። ተንቀሳቃሽ ምስሉ ሲጀምር ለእስላማዊ ቡድኑ መሪ አቡ ባክር አል ባግዳዲ ያላቸውን ታማኝነት በሚያሳዩ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖችን ያሳያል። ባለፈው ወር በተለያዩ ተንታኞች ይህ ግንኙነት የተገመተ ቢሆንም በእስላማዊ ቡድኑ በሚጠቀምባቸው የመገናኛ ብዙሃን ግን በይፋ እስካሁን ድረስ አልቀረበም ነበር። ከሞቱት ወታደሮች የአንዱ ወታደር ባለቤት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለማጽናናት በስልክ ባነገሯት ወቅት በተናገሩት ነገር በማዘኗ ውዝግብ መፈጠሩ ይታወሳል። ተንቀሳቃሸ ምስሉ በርካታ ወታደሮች በበረሃ ውስጥ ምሽግ ለመያዝ ሲሮጡ ያሳያል ሲል ቢቢሲ ሞኒተሪንግ ዘግቧል ። በተንቀሻቃሽ ምስሉ ላይ ወታደሮች ሲታኮሱ እንዲሁም የሞተ ወታደር ምስል ይታይበታል። ተንቀሳቃሽ ምስሉን የቀረፀው ወታደር እስኪገደል ድረስ ውጊያው ቀጥሎ እንደነበር ከቪዲዮው መረዳት ይቻላል።
news-41759669
https://www.bbc.com/amharic/news-41759669
የሌሉት 350 ሚሊዮን ሠዎች
"በዓለም አቀፍ ደረጃ" የሚል ሪፖርት ይፋ በሆነ ቁጥር፤ በሚሊዮን ወይንም በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሠዎች የሚል መረጃ አብሮ ይፋ መደረጉ የተለመደ ነው።
መገናኛ ብዙሃን በዓለም ላይ ላይ የተከሰተን ትልቅ ችግር እና አደጋ በሚዘግቡበት ወቅት ቁጥሩን አግዝፈው ስለሚያስቀምጡ ዜናው መልዕክቱን ያጣል። ትክክለኛውን መረጃም ሳያስቀምጡ ቀርተው ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም እንደዓመታዊው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባሕል ተቋም (ዩኔስኮ) ሪፖርት በዓለም አቀፍ ደረጃ የትምህርት ተደራሽነት ቁጥር በ 350 ሚሊዮን ልዩነት ያለው ሆኗል። ይህ ልዩነት ትንሽ አይደለም። የእንግሊዝ፣ የጀርመን፣ የፈረንሳይ፣ የጣሊያንና የስፔን አጠቃላይ የህዝብ ቁጥርን የሚያክል ነው። ያልተመዘገቡ እና የማይታዩ "የማይታዩት" ሠዎች "የደሃ ደሃዎች" በሚል የሚገለጹ ናቸው። እነዚህ ቤተሰቦች በማይመች አካባቢ በመኖራቸው ምክንያት የህዝብ ቆጠራና እና የመንግሥት አስተዳደር ያልደረሳቸው ናቸው። እነዚህ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እና ያልተመዘገቡ ሰዎች በታዳጊ ሃገራት፣በህገወጥነት እና ሳይመዘገቡ ደግሞ በስደተኝነት ይኖራሉ። የዩኔስኮ ሪፖርት እንደሚገልጸው ቤት ለቤት ጥናት፣ ቆጠራ እና የልደትና የሞት ምዝገባ መደበኛ ለሆነው የመረጃ አሰባበሰብ ቢጠቅምም ትክክለኛ ውጤት የሚሰጠው በተደራጀ፣ በሚታይና አገልግሎት በተዳረሰባቸው አካባቢዎች ነው። ዓለም አቀፍ አሃዞች ምን ያህል ትክክለኛ ናቸው? በዚህ ምክንያትም በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በመረጃ ሰብሳቢዎች የማይመዘገቡ ይሆናል። የጎዳና ተዳዳሪ ልጆችም ትምህርት ቤት ካልገቡ ልጆች ጋር አብረው አልተቆጠሩም። መረጃው ካላካተታቸው ጋርም አብረው አልተደመሩም። ቤት የሌላቸውና ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚኖሩ ሰዎች መረጃዎችን ከቤት ወደ ቤት በመሄድ በሚሰበበስቡ ሰዎችም አልተመዘገቡም። የፖለቲካ ግጭትን ተከትሎ ድንበር እንዲሻገሩ የተደረጉ ስደተኞች መረጃም ስለማይታወቅ አልተቆጠሩም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲ በታዳጊ ሃገራት ከቤት ወደ ቤት በተደረገ መረጃ መሰብሰብ ሥራ 250 ሚሊዮን ሰዎች እንዳልተቆጠሩ ግምቱን አስቀምጧል። በበለጸጉት ሃገራት በህገወጥ መንገድ የሚኖሩትን ጨምሮ 100 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ መረጃ ከሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ውጭ ናቸው ይላል። ተጠያቂነት የዘንድሮው የትምህርት ዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ትኩረቱን በተጠያቂነት ላይ አድርጓል። ሆኖም የዩኔስኮ ጥናት እንደሚያሳው መንግሥታት የትምህርት ተደራሽነት ባለማሳደጋቸው ሊጠየቁ የሚገባው ድጋፍ በሚፈልጉት ሰዎች ብዛት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ መሃይምነትን ለመቀነስ እና የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋፋት የተቀመጠው ግብ አንዳንዶችን ያላካተተ ነው። ይህ በብሄራዊ መዝገብ ውስጥ ያልተካተቱ ሰዎችን ጉዳይ ማን ይከታተለዋል የሚል ጥያቄን ይጭራል ይላል ዩኔስኮ። ይህን መሰሉ የመረጃ ልዩነት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሃዝ ላይም ይስተዋላል። የትምህርት ዕድል ያላገኙ ህጻናትን የሚገልጸው ዓመታዊው ሪፖርቱ፤ መረጃ ለመሰብሰብ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎች ያሉትንም ያካትታል በማለት የዩኔስኮ ሪፖርት ያስረዳል። ተማሪዎች ትምህርት ቤት ቢገቡም አሁንም 264 ሚሊዮን የሚሆኑት ዕድሉን አላገኙም ከትምህርት ስርጭት አለመመጣጠን እና ትምህርት ላይ ከሚደረገው የገንዘብ ፍሰት አንጻር ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩት እና "የማይታዩት" አለመካተታቸውን ዩኔስኮ ይገልጸል። ትምህርት ቤት አለመግባት በዚህ ዓመት ይፋ የሆነ አዲስ ሪፖርት እንደሚገልጸው 264 ሚሊዮን ወጣቶች የመጀመሪያ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አላገኙም። የትምህርት ዘርፉ ለስድስተኛ ተከታታይ ዓመት የሚደረግለት ፋይናንስ ድጋፍ መቀነሱን ሪፖርቱ ገልጾ ስጋቱን አስቀምጧል። ቤት አልባ እና ስደተኛ ሰዎች ከይፋዊ ቆተራ ውጭ ናቸው የቀድሞ ትምህርት ሚንስቴሮች ቡድን የሆነው አትላንቲስ ግሩፕ ለትምህርት የሚደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ሊሆን ይገባል ብሏል። ባለፈው ወር ሌላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት እንደገለጸው የትምህርት ተደራሽነትን ከማስፋፋት አንጻር ባለፉት አስር ዓመታት የነበረው ለውጥ ወደ ዜሮ የተጠጋ ነበር። ሌላ የድርጅቱ ሪፖርት ደግሞ 600 ሚሊዮን ወጣቶች ትምህርት ቤት ቢገቡም መሠረታዊ ዕውቀት አልገበዩም ብሏል።
news-45480816
https://www.bbc.com/amharic/news-45480816
«የወሊድ መቆጣጠሪያን ወዲያ በሉት»፡- የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ
የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ሃገሪቱ በርካታ ሕዝብ ስለሚያስፈልጋት ሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒቶች መውሰድ ቢያቆሙ እንደሚሻል አሳውቀዋል።
«ሴቶች አሁን ስለ ወሊድ መቆጣጠሪያ ተስፋ ቢቆርጡ ይሻላል» ሲሉ ነው ማጉፉሊ የተደመጡት። ተቃዋሚው የሕዝብ እንደራሴ ሴሲል ምዋምቤ የፕሬዚዳንቱ ሃሳብ ከሃገሪቱ የጤና ፖሊሲ ጋር የሚጣረስ ነው ሲሉ ማጉፉሊን ወርፈዋል። የታንዛኒያ ሕዝብ 53 ሚሊዮን ገደማ የሚገመት ሲሆን፤ 49 በመቶ ያህሉ ዕለታዊ ገቢ ከ2 ዶላር (54 ብር ገደማ) በታች ነው። አልፎም ሃገሪቱ ከዓለማችን ሃገራት ከፍተኛ የውልደት መጠን ያለባት ሃገር ናት፤ አንዲት ሴት በአማካይ አምስት ልጆች አላት። • ታንዛኒያ ቦይንግ "787-8 ድሪምላይነር" ገዛች ማጉፉሊ ይህን በተናገሩ ማግስት የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፈ ቀላጤ የሆኑት ጆብ ዱጋይ ሴቶች ሰው ሰራሽ ጥፍር እና የዓይን ሽፋሽፍት እንዳይጠቀሙ ከልክለዋል። ለቢቢሲ ድምፃቸውን የሰጡት አፈ ቀላጤው እገዳው ከጤና ጋር የተያያዘ ነው የሚል አጠር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል። አዲሱ ህግ ሴት የምክር ቤት አባላት ጉርድ ቀሚስና ጂንስ ሱሪ እንዳያደርጉ ያግዳል፤ ምክር ቤቱን የጎበኙ ሴቶችም ለህጉ ተገዢ እንዲሆኑ ይገደዳሉ። ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ያደረጉት ማጉፉሊ «ሴቶች ብዙ ልጅ ወልደው እነሱን ለመመገብ ጠንክሮ ላለመሥራት ነው አንድ ወይም ሀሉት ልጅ ብቻ የሚወልዱት» ብለዋል። • በታንዛንያ አርግዘው የተገኙ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ታሰሩ «ወደ አውሮጳ ተጉዤ ትንሽ ልጅ መውለድ ያለውን ጉዳት ተመልክቻለሁ» ሲሉም 'ልምዳቸውን' አካፍለዋል። ተቃዋሚው ምዋምቤ «ማጉፉሊ ይህን ካሰቡ አራት የቤተሰብ አባል ብቻ የሚሸፍነውን የጤና ኢንሹራንስ ወደ አስር የቤተሰብ አባል ባሳደጉት ነበር» ብለዋል። ማጉፉሊ፤ በፈረንጆቹ 2015 ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ ስለ ወሊድ መቆጣጠሪያ ጉዳት ከመዘከር ቦዝነው አያውቁም። ባለፈው ዓመት ነብሰ ጡር ተማሪዎች ከወለዱ በኋላ ትምህርት መቀጠል ባይችሉ የሚል ሃሳብ መስጠታቸው አይዘነጋም። • የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የሃሰት መረጃን ሊቆጣጠሩ ነው
news-54157562
https://www.bbc.com/amharic/news-54157562
አውስትራሊያ፡ የተጠርጣሪውን ጭንቅላት ረግጦ መሬት ላይ ያጣበቀው ፖሊስ ታገደ
በአውስትራሊያ ፖሊስ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር በሚያውልበት ወቅት በመኪና ገጭቶ ጭንቅላቱን መርገጡን ተከትሎ ከስራ ታግዷል።
ክስተቱ የደረሰው በሜልቦርን ከተማ ዕሁድ እለት ነበር። የ32 አመቱ ተጠርጣሪ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ሲያውሉት ባደረሱበትም አደጋ በፅኑ ህሙማን ክፍል በሞትና በህይወት መካከል ውስጥ ነው ያለው ተብሏል። ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር በሚውልበት ወቅት ተቀረፀ የተባለ ቪዲዮ መውጣቱንም ተከትሎ ቤተሰቡ ነፃ ምርመራ እንዲከፈት ጥሪ አድርጓል። የቪክቶሪያ ፖሊስም ውስጣዊ ምርመራ ጀምሬያለሁ ብሏል። በባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የሜልቦርን ከተማ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት በወጣው መመሪያ ምክንያት ጥብቅ የእንቅስቃሴ እግድ ላይ ናት። ከጤና ጋር በተያያዘ ለዚህ ስጋት የሚሆኑና መመሪያዎችን ጥሰው የሚገኙ አውስትራሊያውያኖችንም በቁጥጥር ስር እንዲያውሉና እንዲቀጡ ፖሊሶች ከፍተኛ ኃይል ተሰጥቷቸዋል። የእሁዱ ሁኔታ ግን ከኮሮናቫይረስ መመሪያ ጋር የተያያዘ አይደለም ተብሏል። ግለሰቡ ከፖሊስ ጋር ያለው ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት ወደ አዕምሮ ጤና ሆስፒታል ለህክምና ሄዶ ነበር። የሆስፒታሉ ሰራተኞችም ናቸው ለፖሊስ የደወሉት። ሁኔታውን ሲከታተል የነበረ ግለሰብ የቀረፀው ቪዲዮ እንደሚያሳየው አንደኛው ፖሊስ ጭንቅላቱን በእርግጫ ሲመታውና መሬት ላይ ሲያጣብቁት ይታያል። የቪክቶሪያ ፖሊስ ግለሰቡ ነውጠኛ ባህርይ እያሳየና አንደኛው ፖሊስም ላይ ጥቃት አድርሷል ብሏል። በሰቨን ኒውስ የቴሌቪዥን ጣቢያ የታየው ይህ ቪዲዮ ላይ ግለሰቡ መሃል ጎዳና ላይ ሲራመድና እጁን ወደ ፖሊስ መኪናው አቅጣጫ ሲያውለበልብ ይታያል። ከዚያም ዘወር ብሎ ቀስ ብሎ ሲራመድ የሚታይ ሲሆን የፖሊስ መኪናውም ይገጨዋል። ከደቂቃዎች በኋላ የተቀረፀ ሌላ ቪዲዮም እንደሚያሳየው አንደኛው ፖሊስ ጭንቅላቱን ሲረግጠውና ከመሬት ጋር ሲያጣብቀው ይታያል። ከዚያም ይህንን ፖሊስ ጨምሮ አምስት ሌሎች ፖሊሶች ከመሬት ጋር አጣብቀውት ይታያል። ጥቃት የደረሰበት ግለሰብ አባት ፖሊስ ያልተገባ ኃይል ተጠቅሟል ብሏል። "አሜሪካ ወይም ቤይሩት የተቀረፀ ቪዲዮ የማይ ነው የመሰለኝ" በማለትም ለሄራልድ ሰን ጋዜጣ ተናግረዋል። "ፖሊስ ከህግ በላይ አይደለም። ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባል። እየረገጡትና እየደበደቡት ነበር፤ እሱም በምላሹ እንኳን እየታገለ አልነበረም። ያልተገባ ተግባር ነው" ብለዋል። ጠበቃው ጄረሚ ኪንግ ለኤቢሲ ኒውስ እንደተናገሩት ደንበኛቸው ምንም አይነት ወንጀል እንዳልፈፀመና በቁጥጥር ስር በዋለበትም ወቅት አእምሮው ባልተረጋጋበት ወቅት ነው ብለዋል። "ግለሰቡ ካለበት ሁኔታ አንፃር ፖሊስ ሊንከባከበው በሚያስፈልግበት ወቅት፣ በተለየ መንገድ ሊያየው ይገባ ነበር" ብለዋል። ፖሊስ በበኩል ግለሰቡ ሲረብሽ እንደነበርና በቁጥጥር ስር አልውልም ብሎ በማስቸገርም የፖሊስ መኪና አበላሽቷል ብሏል። ሆኖም ክስተቱ አሳሳቢ ነገሮች ስላሉበት ምርመራ እንደሚከፈትም ተገልጿል።
news-53998602
https://www.bbc.com/amharic/news-53998602
በምሥራቅ ባሌ የተመረዘ ውሃ የጠጡ 100 ፍየሎች ሞቱ
በምሥራቅ ባሌ ዞን የተመረዘ ውሃ የጠጡ ከ100 በላይ ፍየሎች ሲሞቱ ስምንት ሰዎች ደግሞ ታመው ህክምና እርዳታ ማግኘታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ገለፁ።
በዞኑ ራይቱ ወረዳ በሃረዱቤ ገበሬ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ከ500 በላይ የሚሆኑ ፍየሎች የተመረዘ ውሃ ጠጥተው ከመካከላቸው 102 ሲሞቱ አራት መቶዎቹ መትረፋቸውን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል። የቀበሌው ነዋሪ የሆኑት አቶ ኡመር አብዱላሂ አካባቢው በረሃማ በመሆኑ ለሰዉም ሆነ ለእንስሳት ለመጠጥ የሚውለው ውሃ ከጉድጓድ የሚቀዳ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ውሃውን ከጥልቅ ጉድጓድ በገመድ እየጎተቱ በማውጣት እንደሚጠቀሙ የሚናገሩት አቶ ኡመር "ከድሮ ጀምሮ በእንደዚህ መንገድ ነው የምንጠቀመው፤ ቅርብ ጊዜ ግን አይተን በማናውቀው መልኩ 97 ፍየሎች ውሃውን እንደጠጡ ወዲያውኑ ሞቱ" ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። አምስቱ ፍየሎች ደግሞ የእንስሳት ህክምና ማዕከል ደርሰው መሞታቸውን ነዋሪው አክለው ተናግረዋል። ከፍየሎቹ ውጪ ከጉድጓዱ ውሃውን የጠጡ ስምንት ሰዎች ታምመው እንደነበር ነዋሪዎቹ ገልፀዋል። ስምንቱ ሰዎች በአካባቢው በሚገኝ ጤና ተቋም ህክምና እርዳታ አግኝተው በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ለቢቢሲ የተናገሩት አቶ ኡመር፣ ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ችግር ገጥሟቸው እንደማያውቅ አስረድተዋል። አቶ ኡመር ለችግሩ ምክንያት ይሆናል የሚሉት ሁለት ነገር መሆኑን በማስረዳት፣ "አንደኛ መርዛማ አውሬዎች፤ እንደ እባብ ያለ ውሃ ውስጥ ገብቶ ሊሆን ይቸላል፤ ሌላኛው ደግሞ ድንበር ላይ ነው የምንኖረው፤ በዚህ ውሃ ላይ ደግሞ በተደጋጋሚ ግጭቶች አሉ፤ ምናልባት ሰዎች መርዘውት ሊሆን ይችላል" የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረዋል። የራይቱ ወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሽብሩ አደሬ ስለሁኔታው ተጠይቀው፣ የጉድጓድ ውሃው እንዴት እንደተመረዘ ለማጣራት ናሙና ለአሰላ የእንስሳት ቤተ ሙከራ መላኩን ገልፀዋል።
news-42700121
https://www.bbc.com/amharic/news-42700121
አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ግብፅ በአባይ ላይ ያላትን ጥቅም ለማስጠበቅ ቃል ገቡ
የግብፁ ፕሬዝዳንት አብድል ፈታህ አል ሲሲ የሀገራቸውን የውሃ አቅርቦት እያስጠበቁ ከኢትዮጵያ እና ከሱዳን ጋር ያላቸው ሰላማዊ ግንኝነት ዙሪያ አትኩረው እንደሚሰሩ መናገራቸውን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ዘግቧል።
የግብፁ ፕሬዝዳንት አብድል ፈታህ አል ሲሲ ግብፅ ከሱዳን እና ከኢትዮጵያ ጋር በድንበር እና በአባይ ውሃ አጠቃቀም ዙሪያ አለመግባባት ውስጥ መሆኗ ይታወቃል። ግብፅ የውሃ አቅርቦቷ የተመሰረተው ሙሉ በሙሉ አባይ ላይ ሲሆን የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሀገሪቱ የውሃ ድርሻ ይጎዳዋል ሲሉ ይናገራሉ። ግብፅ ለረዥም ዓመት አባይን መጠቀም ተፈጥሮአዊ መብቷ እንደሆነ በመጥቀስ በዓለም ትልቁ ወንዝ ላይ የሚካሄዱ ፕሮጀክቶችን ትቃወም ነበር። ግብፅ ለረዥም ጊዜ የቆየ በማእድን ሃብቱ የታወቀው እና ቀይ ባህር አቅራቢያ በሚገኘው ሀላየብ ትራያንግል ጋር በተያያዘ ከሱዳን ጋር ግጭት ውስጥ ናት። ሁለቱም ሀገራት የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱ ሲሆን ቦታው በግብፅ ቁጥጥር ስር ይገኛል። ባለፈው ግንቦት ወር ሱዳን ከግብፅ የሚገቡ የግብርና እና የእንስሳት ተዋፅኦችን ማገዷ ይታወሳል። በቅርቡም "ለመመካከር" በሚል ሰበብ አምባሳደሯን ከካይሮ ጠርታለች። አል ሲሲ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር ሀገራቸው ወታደራዊ አቅሟን ታጠናክራለች። በተጨማሪም "ይህ ደህንነታችን ነው፤ ሀገራችንን መከላከል የሚችል በቂ ወታደራዊ ሃይል አለን። አሁን የምናገረው ይህንን ሰላም ለማስጠበቅ ነው። በድንበር አካባቢ ያለውን ሁሌም እናጠናክራለን፤ ከማንም ጋር አናብርም በሌላ ሃገር ጉዳይ ጣልቃ አንገባም" ብለዋል። አል ሲሲ መልእክታቸው ለግብፃውያን ቢመስልም "ለኢትዮጵያ እና ሱዳን ወንድሞቻችን ጉዳዩ ግልፅ ይሆንላቸዋል" ብለዋል። የግብፅ ፕሬዝዳንት ባለፈው ሳምንት ያለውን የውሃ እጥረት ያስወግዳል ተብሎ የታለመ ከየቤቱ የሚወገዱ ውሃዎችን ለማከም የሚያገለግል ትልቅ የውሃ ማጣሪያ እየገነባች እንደሆነ ይፋ አድርገው ነበር። ባለፈው ወር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሳሜህ ሹክሪ በአዲስ አበባ በመገኘት ስለ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ መነጋገራቸው ይታወቃል። የሃይል ማመንጫ ግድቡ 6000 ሜጋ ዋት ያመነጫል ተብሎ የታሰበ ሲሆን ይህም ከስድስት የኒውክሌር ማብላያ ጣበያ ጋር የሚስተካከል ያደርገዋል። ግንባታው በ2012 የተጀመረ ሲሆን ግድቡ እስካሁን ድረስ 60% ብቻ መጠናቀቁን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
news-46068719
https://www.bbc.com/amharic/news-46068719
የሳዑዲው ልዑል «ኻሾግጂ አደገኛ ሰው ነበር» ማለታቸው እያነጋገረ ነው
የሳዑዲው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን «ኻሾግጂ እንደ አደገኛና አክራሪ ኢስላሚስት ነው የማየው» ብለው ለአሜሪካ መናገራቸው እየተዘገበ ነው።
አልጋ ወራሹ ከዋይት ሃውስ ጋር በቀጭኑ ሽቦ ይህን ውይይት ያደረጉት ኻሾግጂ መሞቱ ሳይታወቅ ጠፍቶ ሳለ ነበር ተብሏል። የአሜሪካዎቹ ጋዜጦች ዋሽንግተን ፖስት እና ኒው ዮርክ ታይምስ ያወጡትን ይህን ዘገባ የሳዑዲ አራቢያ መንግሥት ክዶታል። ሳዑዲ አረቢያዊው ጃማል ኻሾግጂ ከሃገሩ ተሰዶ አሜሪካ ውስጥ ይኖር የነበረ ሲሆን ልዑሉ ለውጥ እንዲያመጡ በስራው ይወተውት የነበረ ግለሰብ ነበር። • 'ጉደኛው ጋንግስተር' በልገር እሥር ቤት ውስጥ ተገደለ ሬሳው የት ይግባ የት ውሉ ያልታወቀው ኻሾግጂ ኢስታንቡል በሚገኘው የቱርክ ኤምባሲ ውስጥ በመገደሉ ዙሪያ ቱርክ፣ አሜሪካና እና ሳዑዲ አራቢያ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ሳዑዲ አረቢያ ንጉሱ እና ቤተሰባቸው በጋዜጠኛው ግድያ እጃቸው የለበትም ስትል ሙጥጥ አድርጋ ክዳለች፤ «እውነቱን ለማውጣት የማልቆፍረው የለም» በማለት። ባለፈው ሳምንት ልዑል ሞሐመድ «ወንጀሉ የሳዑዲዎች ልብ የሰበረ ነው» ብለው ማለታቸው አይዘነጋም። ከትራምፕ ልጅ ባል ጃሬድ ኩሽነር እና ከደህንነት አማካሪው ጆን ቦልተን ጋር በስልክ ያወሩት ልዑሉ «ኻሾግጂ የሙስሊም ወንድማማቾች አባል ነው» ማለታቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል። • ታንዛኒያ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎችን አድና ልታስር ነው ልዑሉ ወደ አሜሪካ የደወሉት በፈረንጆቹ ጥቅምት 9 እንደሆነም ተነግሯል፤ ኻሾግጂ ከጠፋ አንድ ሳምንት በኋላ። ልዑሉ አጋጣሚውን ተጠቅመው አሜሪካ ከሳዑዲ ጋር ያላትን ወዳጅነት በጥብቅ እንድትይዝ አደራ ብለዋል ተብሏል። በጉዳዩ ዙሪያ ኦፊሴላዊ መግለጫ የሰጡት የኻሾግጂ ቤተሰቦች ጃማል የማንኛውም አክራሪ ቡድን አባል እንዳልነበር ገልፀዋል። «ጃማል ኻሾግጂ ምንም ዓይነት አደጋ ሊያመጣ የሚችል ሰው አልነበረም፤ እሱን አደገኛ ማለት እንደመሳለቅ ነው» ይላል የቤተሰቡ መግለጫ። • «ካሾግጂ ወዲያው ነበር የታነቀው» ቱርክ
46093859
https://www.bbc.com/amharic/46093859
የዕውቁ ፈረንሲያዊ ገጣሚ ሻርል ቦድሌር የኑዛዜ ወረቀት በጨረታ ተሸጠ
የፈረንሳይ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ገጠሚ የነበረው ሻርል ቦድሌር ራሱን እንደሚያጠፋ የፃፈበት ብጣሽ ወረቀት 7.3 ሚሊየን ብር በጨረታ ተሽጧል።
ሻርል ቦድሌር ፈረንሳይ አሉኝ ከምትላቸው የምን ጊዜም ምርጥ ገጣሚያን ተርታ ስሙ የሰፈረ ነው ማስታወሻው የተፃፈው እኤአ ሰኔ 30 1845 ሲሆን የተፃፈውም ለፍቅረኛው ዣን ዱቫል ነው። ገጣሚው ያኔ 24 ዓመቱ የነበረ ሲሆን ደብዳቤውን በፃፈ ዕለት ራሱን ለማጥፋት ሞክሮ ተርፏል። • ተፈጥሮን በብሩሽ የሚመዘግበው መዝገቡ • አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው ማዕቀብ ተግባራዊ ሊደረግ ነው እንዲህ አይነት ጨረታዎችን የሚያስተዋውቀው ኦዝና ድረ ገፅ ደብዳቤው ለአንድ ግለሰብ የተሸጠው ከተገመተለት ዋጋ ሶስት እጥፍ በላይ መሆኑን ገልጿል። በዚህ ደብዳቤው ላይ ለፍቅረኛው "ይህ ደብዳቤ ሲደርስሽ ሞቻለሁ" ሲል ራሱን ማጥፋቱን ገልጾበታል። "ራሴን የማጠፋው ዳግም የመኖር ፍላጎቴ ከወስጤ ስለተሟጠጠ ወይም ተኝቶ መነሳት ስለታከተኝ ነው" በማለት በደብዳቤው ላይ አስፍሯል። ይህን ደብዳቤ የጻፈው የገንዘብ ችግር በነበረበት ወቅት ነበር ቡድሌ በውርስ ያገኘውን ገንዘብ አባክኖ ችግር ውስጥ ከተዘፈቀ በኋላ ደረቱን በመውጋት ራሱን ለማጥፋት የሞከረ ሲሆን ሙከራው ግን ለከፋ ጉዳት ሳይዳርገው ቀርቷል። እራሱን ለማጥፋት ከሞከረበት ዕለት በኋላ ለ22 ዓመታት ኖሯል። 'ሌ ፍለር ዱ ማል' በተሰኘው ተከታታይ ጽሁፎቹ ዝናው እጅግ ናኝቶ ነበር። • ግብፅ የኮፕቲክ ክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ያደረሱትን በሞት ቀጣች • የ29 ዓመቷ የህክምና ዶክተርና ኢንጅነር ዕልልታ ጉዞ የግጥም ስራዎቹ በፈረንሳይ ሥነ-ጽሁፍ ላይ ተጽእኖ አሳድሯል የሚባልለት ሻርል ቦድሌር 1867 ላይ በአባላዘር በሽታ ህይወቱ አልፏል።
news-50895605
https://www.bbc.com/amharic/news-50895605
ሲሰርቁ የታዩት አምባሳደር ሥልጣን ለቀቁ
በአርጀንቲና የሜክስኮ አምባሳደር የሆኑት ግለሰብ መጽሃፍ ሲሰርቁ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ከተለቀቀ በኋላ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ።
አምባሳደሩ መጽሃፍ ሰረቁበት የተባለው የመጽሃፍት መደብር አምባሳደሩ ከዚህ ቀደምም ከአንድ መደብር ውስጥ እቃ ሲሰርቁ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተቀባብለውታል። የ77 ዓመቱ ሪካርዶ ቫሌሮ፤ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸው ላይ፤ የጤና መቃወስ ሥራቸው በአግባቡ ማከናወን እንዳላስቻላቸው ጠቅሰዋል። ባሳለፍነው ወር በአርጀንቲና ቦነስ አየርስ አንድ መደብር ውስጥ መጽሃፍ ለመስረቅ ጥረት ሲያደርጉ የሚያሳይ ምስል ይፋ ከሆነ በኋላ የሃገራቸው መንግሥት ወደ ሜክሲኮች ጠርቷቸዋል። በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ መጽሃፉን በያዙት ጋዜጣ ከጠቀለሉ በኋላ ከመደብሩ ለመውጣት ሙከራ አድርገው ነበር። አምባሳደሩ ሊሰርቁት የነበረው የ10 ዶላር መጽሃፍ በ18ኛው ክፍለ ዘመን ስለኖረ ጣሊያናዊ ጸሐፊ፣ ወታደር እና ሰላይ የሕይወት ታሪክ የሚዘክር ነበር ተብሏል። • ልማደኛው ሌባ ደቦል ሰርቆ ተያዘ ከዚያ በኋላ በሌላ አጋጣሚ ሪካርዶ ቫሌሮ አየር ማረፊያ ውስጥ ከሚገኝ ሱቅ ውስጥ ቲሸርት ለመስረቅ ሞክረዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ቫሌሮ ከቀረጥ ነጻ በሆነው መደብር ቲሸርቱን ለመስረቅ የሞከሩት የሜክሲኮ መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ቦነስ አየርስ አየር ማረፊያ ሳሉ ነበር። የሜክሲኮ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር የአምባሳደሩን የሥራ መልቀቂያ ተቀብሏል። "ሪካርዶ መልካም ሰው ነው። የአእምሮ ህክምና እየተከታተለ ነው። በቶሎ እንዲሻለው እመኛለሁ" በማለት የሜክሲኮ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማርሴሎ ኤብራርድ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
53263715
https://www.bbc.com/amharic/53263715
"ከዚህ በኋላ በየትኛውም ሚዲያ፤ . . . ሕዝብን ማዕከል ያደረገ የጥላቻ፤ የፕሮፖጋንዳ ሥራ አንታገስም" ታከለ ኡማ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ሐሙስ ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ የሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ አዲስ አበባ ላይ እንዲደርስ ታስቦ የነበረው "እልቂት" ሙሉ በሙሉ መክሸፉን ተናገሩ።
አክለውም ከአርብ ጀምሮ ሁሉም የመንግሥትና መንግሥታዊ የሆኑ ድርጅት ሠራተኞች ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲመለሱ አዝዘዋል። "ከነገ [አርብ] ጀምሮ ሁሉም የመንግሥት ኃላፊዎች ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ሁሉም በከተማው ውስጥ የሚንቀሳቀስ የከተማው ነዋሪ መደበኛ ሥራውን እንዲጀምር አዛለሁ" ካሉ በኋላ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። በማሳሰቢያቸውም አገርም፣ ከተማም ትውልድም ሂደታቸውን ይቀጥላሉ ካሉ በኋላ "በዚህ ሂደቱ ላይ እንቅፋት እሆናለሁ፣ የጀመርኩትን ድራማ እቀጥላለሁ የሚልን በሕግም፣ በሥርዓትም፣ በሞራልም፣ በታሪክም እንፋረዳለን" ብለዋል። አርቲስት ሃጫሉ "በተሰዋበት" ከተማ ላይ ከሥራ ባልደረቦቹና ከወንድሞቹ ጋር በመሆን መሃል ከተማ ላይ ለማስታወሻነት ሐውልት እንደሚቆም የተናገሩት ምክትል ከንቲባው፤የመታሰቢያ ሐውልቱም ድምጻዊውን የሚመጥን ብቻ ሳይሆን "ለዛሬው ትውልድ ስንቅና ቁጭት ሊፈጥር የሚችል ለሚቀጥለው ትውልድ ደግሞ ታሪክ" እንደሚሆን ተናግረዋል። ምክትል ከንቲባው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ ጥምር የፀጥታ ኃይሉ የከተማዋን ሰላምና ሥርዓት ማስከበር መጀመሩንም ተናግረዋል። "ማናችንም ብንሆን ከአገር በታች ነን፣ ከሕግ በታች ነን" በማለት አገርንና ትውልድን ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ጠቅሰው፤ አገር የማስተዳደር ሂደትን ለማደናቀፍ የሚሞክር የትኛውም አካልን "ትዕግስት ልክ አለው" በማለት "ከዚህ በኋላ በየትኛውም ሚዲያ፤ በየትኛውም ጽሁፍ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ፤ ግለሰብን ማዕከል ያደረገ፤ ሕዝብን ማዕከል ያደረገ የጥላቻ፤ የፕሮፖጋንዳ ሥራ አንታገስም" ብለዋል።
news-49470326
https://www.bbc.com/amharic/news-49470326
እስራኤል 'የኢራንን ሰው አልባ አውሮፕላን ጣቢያ ከጥቅም ውጭ አድርግያለሁ' እያለች ነው
እስራኤል፤ ሶሪያ ውስጥ የሚገኝ አንድ የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጣቢያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት መፈፀሟን አስታውቃለች።
በሶሪያ ስላላት ተሳትፎ ብዙም መረጃ የማትሰጠው እስራኤል 'ሰው አልባ አውሮፕላን ጣቢያው የቴል-አቪቭ መንግሥት ላይ ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጀ ነበር' ብላለች። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ የወታደራዊ ኃይላቸውን እርምጃ 'አብይ እና ስኬታማ ኦፕሬሽን' ሲሉ ገልፀውታል። የሶሪያ የእርስ በርስ ግጭት ከተቀሰቀሰበት 2011 [እ.አ.አ.] ጀምሮ እስራኤል በርካታ ወታደራዊ እርምጃዎችን ስትወስድ ነበር። ዋነኛ ዓላማዋም ኢራን በሶሪያ ያላትን ቦታ መጋፋት ነው። የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ቃል-አቀባይ የሆኑ ሰው ቅዳሜ ዕለት የተካሄደው ኦፕሬሽን፤ ደቡብ ምስራቅ ደማስቆ የከተሙት በኢራን የሚደገፉት ኩርድስ የተሰኙ ታጣቂዎችን ዒላማ ያደረገ ነው። 'ሰንዓ ኒውስ ኤጀንሲ' የተባለ አንድ የሶሪያ ዜና ወኪል የእስራኤል ፀረ-አየር ኃይል አባላት የጠላት ይዞታን ዒላማ አድርገዋል ሲል ዘግቧል። ነገር ግን የእስራኤል ሚሳዔሎች ዒላማቻውን ከመምታቸው በፊት ከጥቅም ውጭ ሆነዋል ሲል ነው ወኪሉ ያተተው። ጠ/ሚ ኔታኒያሁ ግን በትዊተር ገፃቸው ድል ማስመዝገባቸውን የሚናገር መልዕክት ነው ያስተላለፉት፤ 'ኢራን ሁሉም ቦታ መከላከያ የላትም። የኛ ኃይሎች የኢራንን ወረራ ለመመከት ሁሉም ቦታ ይገኛሉ። አንድ ኃይል ሊገልህ ከተነሳ ቀድመህ ግድለው' ሲሉ። ሌላኛው በኢራን የሚደገፈው 'ሄዝቦላህ' ሁለት የሌባኖስ ዜጎች በእስራኤል ጥቃት መሞታቸውን ይፋ አድርጓል። ድርጅቱ የእስራኤል ንብረት ናቸው ያላቸውን ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች መትቶ መጣሉንም አስታውቋል። ምንም እንኳ ስለጥቃቱ ጥርት ያለ መረጃ ሊገኝ ባይቻልም እስራኤል ትቃት ፈፅሜያለሁ ከማለት አልቦዘነችም፤ ኢራን በጉዳዩ ላይ እስካሁን መግለጫ አልሰጠችም።
news-53956812
https://www.bbc.com/amharic/news-53956812
ጄኮብ ብሌክ በሆስፒታል ታስሮበት የነበረው ካቴና ወልቋል ተባለ
በአሜሪካ ዊስኮንሲን ግዛት ፖሊሶች ከጀርባው ተኩሰውበት ሆስፒታል የገባው ጄኮብ ብላክ፤ ሆስፒታል ሳለ ታስሮ እንደነበረ መገለጹ ብዙዎችን አስቆጥቶ ነበር። አሁን ከጄኮብ እጆች ላይ ካቴና መውለቁ ተዘግቧል።
በጄኮብ ብሌክ ላይ መተኮስ በኬኖሻ እና ሌሎች ከተሞች ለቀናት የዘለቀ ተቃውሞ ቀስቅሷል የኪኖሻ ፖሊስ፤ ጄኮብ ከዚህ በፊት በቁጥጥር ሥር እንዲውል ማዘዣ ወጥቶበት ስለነበረ እንደታሰረ ገልጿል። ጠበቃው በበኩላቸው የእስር ማዘዣው እንደተሰረዘና ጄኮብን ይጠብቁ የነበሩ ፖሊሶች ከሆስፒታሉ እንደወጡ ተናግረዋል። ጄኮብ ላይ ፖሊሶች ሰባት ጊዜ ከተኮሱበት በኋላ ሰውነቱን ማንቀሳቀስ ተስኖታል። • ጥቁሮች 'ባሪያ' እየተባሉ የሚጠሩባት አፍሪካዊት አገር • የባርያ ንግድ በዘረ መል ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ የሚያሳይ ጥናት ይፋ ተደረገ • የእምቦጭ አረምን ማጥፋት ያልተቻለው ለምንድን ነው? ክስተቱን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ ላይ ሁለት ሰዎች በመግደል የተከሰሰው ወጣት የፍርድ ሂደቱ በአንድ ወር ተገፍቷል። ካይል ሪተንሀውስ የተባለው የ17 ዓመት ወጣት ግድያን ጨምሮ ስድስት ክስ ይጠብቀዋል ተብሏል። ወጣቱ “የኪኖሻ ህንጻዎችን ከተቃዋሚዎች መጠበቅ ሥራዬ ነው” ሲል ለጋዜጠኛ ተናግሯል። ሰዎች አንድ መሣሪያ የያዘ ግለሰብን ሲያባርሩና መሬት ላይ ከወደቀ በኋላ ሲተኩስባቸው የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ነው። ጆሴፍ ሮሰንበርን የተባለ የ36 ዓመት ግለሰብና የ26 ዓመቱ አንቶኒ ኸበር ተገድለዋል። ተኳሹ ኋላ ላይ እናቱ ቤት ሳለ በፖሊስ ተይዟል። ለወጣቱ ጠበቃ ያቆመው ተቋም ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ ለበርካታ ታዋቂ ሰዎች የተከላከለ ነው። የጄኮብ ቤተሰቦች ምን አሉ? የጄኮብ አባት “ልጄ ከሆስፒታል አልጋ ጋር በካቴና ታስሮ ማየት አሳዝኖኛል። የትም መሄድ አይችልም። ታዲያ ለምን በካቴና ያስሩታል” ብለዋል። የኪኖሻ ግዛት ፖሊስ ኃላፊ ሉተነንት ኤሪክ ክሊንክሽመር፤ ጄኮብ የታሰረው ከዚህ ቀደም የእስር ማዘዣ ወጥቶበት ስለነበረ ነው ብለዋል። አገረ ገዢው ቶኒ ኤቨርስ ጄኮብ ከሆስፒታል አልጋ ጋር በካቴና መታሰሩ አያሳስብዎትም ተብለው ሲጠየቁ፤ “ማሰር ለምን እንዳስፈለገ አይገባኝም። ሰባት ጊዜ ከጀርባው የተተኮሰበት ሰው ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የአሜሪካ ሲቪል ሊበርቲስ ዩኒየን የኪኖሻ ግዛት የፖሊስ ኃላፊ ከሥራ እንዲነሱ ጠይቋል። ኃላፊው “የነጭ የበላይነትን የሚደግፉ” እና “የፖሊስ ጭካኔን በመቃወም ድምጻቸውን ያሰሙ ሰዎችን የኮነኑ” ተብለዋል። የከተማው ከንቲባ ግን የፖሊስ ኃላፊው እንደማይነሱ ተናግረዋል። የተፈጠረው ምን ነበር? ነገሮች ጄኮብ ላይ ወደመተኮስ እንዴት እንዳመሩ ገና በምርመራ ላይ እንደሆነ ተገልጿል። የዊስኮንሰን ዓቃቤ ሕግ ጆሽ ኩዋል ፖሊሶች በቦታው የተገኙት “የወንድ ጓደኛዬ ያለሁበት ቦታ መምጣት ባይኖርበትም መጥቷል” የሚል ሪፖርት ስለደረሳቸው መሆኑን ተናግረዋል። • አውስትራሊያ ለምን የዓሥር ዓመት ልጆችን ታስራለች? ሦስት ፖሊሶች ጄኮብን ለማሰር አስለቃሽ ጭስ ተጠቅመው ነበር። ከዛም ጄኮብ ወደ መኪናው ሲገባ ረስተን ሸስኪ የተባለ ፖሊስ ከጀርባው ሰባት ጊዜ ተኩሶበታል። ፖሊሶች ከጄኮብ መኪና ስለት እንዳገኙ ገልጸዋል። ጄኮብ ላይ የተኮሰውን ፖሊስ ጨምሮ ሌሎችም ፖሊሶች በጊዜያዊነት ከሥራ ታግደዋል።
news-49368024
https://www.bbc.com/amharic/news-49368024
የቴክሳስ ፖሊስ ልማደኛዋን ድንኳን ሰባሪ እየፈለገ ነው
የአሜሪካ ፖሊስ በደቡብ ቴክሳስ ውስጥ በየሠርግ ቤቱ እየተዘዋወረች በርካታ ስጦታዎችን ሰርቃለች የተባለችን 'ድንኳን ሰባሪ' ሴት እያፈላለኩ ነው አለ።
ማንነቷ ያልታወቀውና እየተፈለገች ያለችው ሴት ካለፈው ኅዳር ወር ጀምሮ ቢያንስ አራት የሰርግ ሥነ ሥርዓቶች ላይ ሳትጋበዝ በመገኘት ለሙሽሮች የተበረከቱ ስጦታዎችን ዘርፋለች። ፖሊስ ግለሰቧን ለመያዝ እንዲረዳው ለአዲስ ተጋቢዎች የተሰጠን የስጦታ መግዣ ኩፖንን በአንድ መደብር ውስጥ ልትጠቀምበት ስትል የተነሳ የተጠርጣሪዋን ፎቶግራፍ አሰራጭቷል። • በደቡብ ወሎ ሙሽራና ሚዜውን የገደለው ቦምብ በተጨማሪም ፖሊስ ሴትዮዋ ያለችበትን ለሚጠቁመው ሰው የ4 ሺህ ዶላር ሽልማት እሰጣለሁ ብሏል። የኮማል አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ባወጣው መግለጫ "ይህችን ልማደኛ ድንኳን ሰባሪ ለሕግ በማቅረብ የሌሎችን ሰዎች የደስታ ቀን እንዳታበላሽ እናድርግ" ሲል ጥሪ አቀርቧል። በአካባቢው ያለ የሠርግ ሥነ ሥርዓቶችን የሚያዘጋጅ አንድ ድርጅት ኃላፊ እንደተናገረው የግለሰቧን ፎቶ ከተመለከተ በኋላ እንደሚያውቃት ተናግሯል። በግለሰቧ ተዘርፈናል ከሚሉት አዲስ ተጋቢ ጥንዶች መካከል የሆኑ ባልና ሚስት እንደተናገሩት ንብረት እንደተወሰደባቸው ያወቁት በጫጉላ ሽርሽር ላይ ሳሉ እንደነበርና ስሜታቸው እንደተጎዳና የደስታ ጊዜያቸው እንደተበላሸም ገልጸዋል። • ሙሽሪት እጮኛዋ መቃብር ላይ ድል ባለ ሠርግ ተሞሸረች ጥንዶቹ ድንኳን ሰባሪዋን ሴት ለይተው ያወቋት ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዶላሮች በጥሬ ገንዘብና በበርካታ ሺህዎች የሚቆጠር ዶላር የሚመነዘሩ ቼኮችና የስጦታ ኩፖኖችን እንደሰረቀቻቸው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ባጋጠማቸው ነገር የተበሳጨችው ሚስት ፍሎሪስ ግለሰቧ "ፍቅራችንን ግን ልትሰርቅ አትችልም" በማለት ፖሊስ ድንኳን ሰባሪዋን አግኝቶ ሕግ ፊት እንደሚያቀርባት ያላትን ተስፋ ገልጻለች።
news-55717275
https://www.bbc.com/amharic/news-55717275
አሜሪካ፡ ከአፈጉባኤዋ ጽህፈት ቤት መረጃ ሰርቃለች የተባለችው የትራምፕ ደጋፊ ተያዘች
በአሜሪካ ካፒቶል አመፅ ወቅት ከዴሞክራቷ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ጽህፈት ቤት ላፕቶፕ ወይም ሃርድ ድራይቭ ሰርቃለች የተባለች የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ በቁጥጥር ስር ዋለች።
ራይሊ ጁን ዊሊያምስ የ22 ዓመቷ ራይሊ ጁን ዊሊያምስ በኃይልና በሕገወጥ መንገድ ወደ ሕንፃው በመግባት እንዲሁም በሥርዓት አልበኝነት ተከሳ ፔንሲልቬንያ ውስጥ ተይዛለች። አንድ የቀድሞ የፍቅር አጋሯ፣ ራይሊ መረጃውን ለሩሲያ የስለላ ተቋም ለመሸጥ አስባ እንደነበር ተናግሯል። ከሁለት ሳምንት በፊት የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሒልን የወረሩ ሲሆን፣ በተፈጠረው ግርግርም የአምስት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ይታወሳል። የጆ ባይደን የምርጫ ውጤትን ለማረጋገጥ ተሰብስበው የነበሩትን ሕግ አውጪዎች የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ወደ ካፒቶል ህንፃ ገብተው ከረበሹ በኋላ ራይሊን ጨምሮ ከ200 በላይ ሰዎች ጉዳያቸው እየታየ ነው። ራይሊ ሰኞ ዕለት በማዕከላዊ ፔንሲልቬንያ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሏን የፖሊስ መረጃ ያመለክታል። ራይሊ በፈቃዷ ለባለስልጣናት እጇን መስጠቷን ምንጮች ለሲቢኤስ ኒውስ ተናግረዋል። ካፒቶል ሒልን ጥሰው የገቡ አመጸኞችን ለመያዝ የኤፍቢአይ አደን ነውጠኞች የደፈሩት ታላቁ ካፒቶል ሒል ምንድነው? የትራምፕ ካቢኔ አባላት በፈቃዳቸው ስልጣናቸው እየለቀቁ ነው የክስ ዝርዝሯ "ያለ ፈቃድ እያወቁ ወደ ተከለከለ ሕጋዊ ቦታ መግባት ወይም በካፒቶል ግቢ ውስጥ ሥነ ምግባር በጎደለው ድርጊት ላይ መሠማራትን" ያካትታል። ክሱ ከመረጃ ስርቆት ጋር የተያያዘ ጉዳይን አይጠቅስም። ኤፍቢአይ ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑም ተዘግቧል። ራይሊ በቴሌቪዥን መስኮቶች ወደ ካፒቶል ሒል ህንጻ ዘልቀው የገቡ ሰዎችን ስትመራ እንደታየች ተነግሯል። የኤፍቢአይ ወኪል የግለሰቧ የቀድሞ የፍቅር አጋር፣ ራይሊ የፔሎሲን ላፕቶፕ ወይም ሃርድ ድራይቭ [የመረጃ ማከማቻ] ለመውሰድ አስባ እንደነበር ጥቆማ እንደተሰጠ ተገልጿል። ምስክሩ፣ ራይሊ "ኮምፒውተሩን ሩሲያ ለሚገኘው አንድ ጓደኛዋ ለመላክ እንዳሰበች ገልጾ፣ ከዚያ ለሩሲያ የውጭ የስለላ አገልግሎት (SVR) ለመሸጥ አቅዳ ነበር" ብሏል። መረጃውን የማስተላለፉ ፍላጎት "ባልታወቁ ምክንያቶች አለመሳካቱንና ራይሊ አሁንም ኮምፒውተሩ በእጇ አለ አልያም አጥፍታዋለች" ሲል ምስከሩ መናገሩ ተገልጿል። የፔሎሲ ሠራተኞች ምክትል ኃላፊ ድሪው ሃሚል፣ ጥቃቱ ከተፈፀመ ከሁለት ቀናት በኋላ በትዊተር ገፃቸው ላይ አንድ ላፕቶፕ ከአፈጉባኤዋ ቢሮ እንደተሰረቀ ገልጸው ነበር። ራይሊ የምትባል አንዲት ሴት በቴሌቪዥን መስኮት የታየች ሲሆን ሕዝቡ ወደ ፔሎሲ ቢሮ በሚወስደው ደረጃ እንዲሄድ ስትመራ ተሰምታለች። ከጥቂት ቀናት በኋላ አይቲቪ ከራይሊ እናት ጋር በሃሪስበርግ ፔንሲልቬንያ በሚገኘው ቤታቸው በሠራው ቃለመጠይቅ በቴሌቪዥን የታየችው ልጃቸው መሆኗን አረጋግጠዋል። ልጃቸው ወዴት እንደምትሄድ ሳትናገር ከቤት እንደወጣች ተናግረዋል። ባልተረጋገጠ መረጃ የፕሬዚዳንት ትራምፕ ድምጽ ተሰርቋል ብለው የሚያምኑ የቀኝ ዘመም ቡድኖች እና ሌሎችም ተጨማሪ ጥቃቶች እንዳይሰነዝሩ በመስጋት ረቡዕ ዕለት ከሚካሄደው የጆ ባይደን በዓለ ሲመት በፊት የደኅንነቱ እርምጃው ተጠናክሯል። የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ከቀሰቀሱት ግርግር ጋር በተያያዘ አራት ሰዎች ሞቱ
news-45899606
https://www.bbc.com/amharic/news-45899606
በሥራ ቃለ መጠይቅ ወቅት ልንላቸው የማይገቡ 7 ነጥቦች
በሥራ ቃለ-መጠይቅ ወቅት ያልተጠበቁ ነገሮች ይፈጠራሉ። ለምሳሌ መቼ እረፍት እንደሚወጡ የሚጠይቁ፣ ስልክ የሚያናግሩ፣ ስለቀድሞ አለቃቸው መጥፎ ነገር የሚያወሩ እና ሌሎችም. . . እነዚህ ነገሮች ብዙ ሲሆኑ የማይገባ ነገር በመናገርም ሥራውን የማጣት ዕጣም ይገጥማል።
በሥራ ቃለ-መጠይቅ ወቅት ልንናገሯቸው የማይገቡ ነገሮችን ከቅጥር ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር እንደሚከተለው ቀርበዋል። 1. "አለቃዬ ብቁ አይደለም" ባለሙያዎች በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ። "የቀድሞ አለቃዎትን የሚያጣጥል ነገር የሚያወሩ ከሆነ ቀጣይ አለቃዎን ስላለማጣጣልዎ ምንም ማረጋገጫ አይገኝም" ይላሉ የቢቢሲ ሙንዶው ሠራተኞች ዳይሬክተር ሉዊስ ሪቫስ። ስለዚህ ከቀድሞ አለቃችን ጋር አለመግባባት ካለ ብንተወዉ ይመረጣል። • ዛሚ ሬዲዮ ሊዘጋ ይሆን? • ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወታደሮቹ ድርጊት ተበሳጭተው እንደነበር ተናገሩ 2. "የአሁኑን ሥራዬን አልወደውም" ይህ ትክክል ቢሆንም ማለቱ ግን ተገቢ አይደለም። አሉታዊ ስሜት ያለውን አስተያየት ወደጎን መተው አስፈላጊ መሆኑን እና እንደ "አዲስ ፈተና ለመቀበል ዝግጁ ነኝ" የሚሉ አይነት አስተያየቶችን እንድንጠቀም ባለሙያዎች ይመክራሉ። 3. "ምንም ደካማ ጎን የለኝም" ይህ ቃለ መጠይቅ የሚደረገውን ሰው እብሪት ከማሳቱም በላይ እራስን መለስ ብሎ ለመመልከት የማይፈልግ ሰው እንደሆንና በበጎ መልኩ የሚሰጡ አስተያየቶችንም ለመቀበል አለመፈለግ እንዳለ የሚያሳይ ነው። "ብቸኛው ችግሬ ሁሉም ነገር ፍጹም እንዲሆን መጠበቄ ነው" የሚል አይነት የተለመዱ አገላለጾችን ማስወገድ እንደሚገባም ባለሙያዎች ይጠቁማሉ። 4. "ይህ ሥራ ምን ያህል የዕረፍት ቀናት አሉት?" የመጀመሪያ የሥራ ቃለ መጠይቅ ከሆነ ሥራውንም እንዳገኘን ስላልተረጋገጠ እና የሚከፈለው የደሞዝ መጠንና ጥቅማጥቅሞችን ጨምሮ ሌሎች ነጥቦች ስለማይታወቁ በጥልቀት ወደ ጉዳዮች መግባት አያስፈልግም። "ለዕረፍት የሚሆን ትኬቶች አገኛለሁ?" ተብሎ የሚጠየቀው ሥራውን እንዳገኘን ሲነገረን ወይም ሥራው ቢሰጠን ምን ያህል ጊዜ ውስት እንደምንጀምር ስንጠየቅ ብቻ ነው። 5. "ድርጅትዎ ምን ይሠራል" ይህንን በፍጹም ልንጠይቅ አይገባም። "ብዙ ጊዜ ስለድርጅቱ የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ አለብዎት" ሲሉ በሠራተኞች ጉዳይ ባለሙያ የሆኑት አሊሰን ዶይል ለቢቢሲ ዎርልድ ገልጸዋል። "ቀጣሪዎችዎ እነማን እንደሆኑ ያጥኑ፣ ድረ ገጻቸውን ይጎብኙ፣ የማህበራዊ ሚዲያዎቻቸውን እና ስለድርጅቱ የሚያትቱ ዜናዎችን መከታትል አስፈላጊ ነው" ብለዋል። ስለድርጅቱ በይፋ የማይታወቁ ነገር ግን በምናውቃቸው ሠዎች በኩል የሚገኙ መረጃዎች ካሉ መፈለግ ጥሩ መሆኑን ዶይል ያብራራሉ። • ስለድምጻችን ልናውቃቸው የሚገቡ ሰባት ነገሮች • ሞባይል ስልክዎ ላይ መከራን አይጫኑ 6. "ደሞዙ ምን ያህል ነው?" ስለደሞዝ ጉዳይ ቀደመን አናንሳ። ቃለ መጠይቅ የሚያደርገን ሠው እስኪያነሳው ድረስ እንጠብቅ። "ቀደም ብለው ስለደሞዝ ጥያቄ ማቅረብ የለብዎትም። ምክንያቱም ለሥራው ብቁ ተብለው ለቅጥር አልታሰቡ ይሆናል" ይላሉ ዶይል። "ጥሩ የሚሆነው የሚጠይቅዎት ሠው ስለደሞዝ ካነሳ ነው። ይህ ደግሞ በጉዳዩ ላይ በስፋት ለማውራት ዕድል የሚፈጥር ይሆናል" ሲሉም ይመክራሉ። 7. "ይህን ሥራ በጣም እፈልገዋለሁ" ሥራውን በጣም የምንፈልገው መሆኑን መሳየት ተገቢ አይደለም። ሊናገሩ የሚገባዎት በሥራው ላይ ጥሩ ፍላጎት እንዳለንና እና ለዚህም የሚሆን ብቃት እንዳለን ብቻ ነው። ቃለ መጠይቅ አድራጊዉን ለማማለል አይሞከሩ። ስለፖለቲካ ወይንም በራስ መተማመን ማሳየት በሚገባዎት ቦታ እየማሉ አይናገሩ። በመጨረሻው ባለሙያዎችን የማያስማማው ነጥብ "ከማንም በላይ ለዚህ ሥራ የምመጥነው እኔ ነኝ" በሚለው በዚህ አባባል ላይ በባለሙያዎች ዘንድ መግባባት የለም። አንዳንዶች ይህ ያለንን ጥንካሬ እና በራስ መተማመን ያሳያል ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ተፎካካሪዎቻችንን በማናውቁበት ሁኔታ ራስን ይህን ያህል ከፍ ማድረግ ተገቢ አይደለም በሚል ይሞግታሉ። በሌላ ጥግ ደግሞ "ለዚህ ሥራ በጣም ብቁ ነኝ ብዬ ባላስብም እማራለሁ . . ." ማለትም አይመከርም። በአጠቃላይ ለሥራ ቃለ መጠይቅ በምንቀርብበት ወቅት ያለንን ደካማ ጎን ከማሳየት ይልቅ ያለንን ተግባራዊ ልምድ መግለጽ ተገቢ ነው። በተጨማሪም ፈጽሞ "አላውቅም" ማለት የለብንም።
54557167
https://www.bbc.com/amharic/54557167
አሌክሲ ናቫንሊ፡ የአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ የሩስያ ባለሥልጣኖችን አገደ
ፑቲንን አጥብቆ የሚተቸው አሌክሲ ናቫንሊ በኖቪቾክ መመረዙን ተከትሎ፤ የአውሮፓ ሕብረት ስድስት ከፍተኛ የሩስያ ባለሥልጣኖችን አገደ።
አሌክሲ፣ ባለቤቱና ልጁ ሕብረቱ ኖቪቾክ ላይ ምርምር የሚያካሂድ ማዕከል ላይም እገዳ ጥሏል። የአውሮፓ ሕብረት ጉዞ ላይና የገንዘብ እንቅስቃሴ ላይ እገዳ ከጣለባቸው መካከል የፌደራል ደህንነት ኃላፊ አሌክሳንደር ቦርትኒኮቭ ይገኙበታል። ሁለት ምክትል የመከላከያ ሚንስትሮችም በእገዳው ተካተዋል። የፑቲን የሳይቤሪያ ልዩ ልዑክ ሰርጌ ሜንያሎም ታግደዋል። . ሩስያዊው ተቃዋሚ አሌክሲ ናቫልኒ፡ “ልሞት ይሆን? ብዬ አስብ ነበር” . የተመረዘው ሩስያዊ አሌክሲ ናቫልኒ ወደ ሩስያ ሊመለስ ነው . የሩሲያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ "ተመርዘዋል" - ቃለ አቀባያቸው ተቃዋሚው አሌክሲ በርሊን ውስጥ እያገገመ ሲሆን፤ ከመመረዙ ጀርባ ያሉት ቭላድሚር ፑቲን እንደሆኑ ተናግሯል። ሩስያ ግን ክሱን አጣጥላለች። የአውሮፓ ሕብረት የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች እገዳው እንዲጣል ተስማምተዋል። በተለይ ፈረንሳይ እና ጀርመን መርዙ ከመንግሥት ተቋም እንደመጣ በማመን እገዳው እንዲጣል ገፋፍተዋል። "አሌክሲ ናቫንሊ በተመረዘበት ወቅት ክትትል እየተደረገበት እንደነበረ ከግምት በማስገባት ሊመረዝ የቻለው በፌደራል ደህንነት እንደሆነ መደምደም ይቻላል" ሲል ሕብረቱ መግለጫ አውጥቷል። የአውሮፓ ባለሙያዎችን ድምዳሜ ሩስያ አትስማማበትም። ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ ሩስያ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ያረቀቀችው ኖቪቾክ አሌክሲን ለመመረዝ ጥቅም ላይ ውሏል። የአውሮፓ ሕብረት እገዳው ኬሚካል መሣሪያን ለማስቆም የሚደረግ ጥረት አካል ነው ብሏል። የሕብረቱ መሪዎች በብራሰልስ የሁለት ቀናት ጉባኤ ያካሂዳሉ። የሩስያ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የአውሮፓ ሕብረት "በመከባበር የተሞላ ውይይትን" አይረዳም ሲሉ ወንጅለዋል። ሩስያ እገዳ ከተጣለባት አጸፋውን እንደምትመልስም አስረግጠዋል። አሌክሲ የጸረ ሙስና አቀንቃኞችን ይመራል። ነሐሴ ላይ ከሰርቢያ ሲመለስ፣ አውሮፕላን ውስጥ ሳለ መመረዙ ይታወሳል። ከዛም በርሊን በሚገኝ ሆስፒታል የጽኑ ሕሙማን ማቆያ ውስጥ ነበር። አገራት የተጣመሩበት የጸረ ኬሚካል መሣሪያ ድርጅት፤ አሌክሲ በኖቪቾክ መመረዙን አረጋግጧል። የአውሮፓ ሕብረት ሩስያ ጉዳዩን እንድትመረምር እና ከድርጅቱ ጋር እንድትተባበር አሳስቦ ነበር። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት እንደሚለው፤ እአአ 2018 ላይ የቀድሞው ሩስያዊ ሰላይ ሰርጌ ስኪርፓል እና ልጁ የተመረዙት በኖቪቾክ ነው። አባትና ልጅ አሁን በሚስጥራዊ ቦታ ይገኛሉ። የአውሮፓ ሕብረት የቭገንሊ ፕሪጎዚን ወይም 'የፑቲን ሼፍ' በመባል የሚታወቁት ነጋዴ ላይ እገዳ እንደሚጥል የጀርመን ሚዲያ ዘግቧል። ግለሰቡ ወደ ሊቢያ መሣሪያ በማስገባታቸው እገዳ ሊጣልባቸው እንደሚችልም ተጠቁሟል።
news-53985156
https://www.bbc.com/amharic/news-53985156
ዚምባብዌ፡ መንግሥት ነጭ ገበሬዎች መሬታቸውን መልሰው ማግኘት ይችላሉ ብሏል
የዚምባብዌ መንግሥት ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት በመንግሥት በኃይል ከይዞታቸው እንዲነሱ ተደርገው የነበሩ ነጭ ገበሬዎች ማመልከቻ ለመንግሥት በማቅረብ ይዞታቸውን ማስመለስ ይችላሉ አለ።
ነጭ ገበሬዎቹ የተነጠቁት መሬት ሊመለስላቸው የማይቻል ከሆነ፤ በምትኩ ሌላ ስፍራ ላይ መሬት ይሰጣቸዋል ተብሏል። እ.አ.አ. 2000 እና 2001 ላይ የወቅቱ የዚምባብዌ ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ ከነጭ ገበሬዎች መሬት ነጥቀው ለጥቁር ዚምባብዌውያን አድለው ነበር። የፋይናንስ ሚንስትሩ መቱሊ ነኩቤ እና የመሬትና ግብርና ሚንስትሩ አንክሸስ ማሱካ በጋራ በሰጡት መግለጫ የቀደመው የዚምባብዌ መንግሥት ውሳኔ እንደሚቀለበስ አስታውቀዋል። ከዚህ ቀደም ከነጭ ገበሬዎች ተነጥቆ ጥቆሮችን የመሬት ባለቤት ያደረገው ሕግ ውድቅ ተደርጎ ጥቁሮችን ባለመብት ያደረገው የመሬት ባለቤትነት እውቅና ይሰረዛል ብለዋል ባለስልጣናቱ። ነጭ ገበሬዎቹ ለመንግሥት አቤቱታ በማቅረብ የመሬት ይዞታቸውን ለ99 ዓመት መልሰው በሊዝ ማግኘት ይችላሉ ብለዋል ሚኒስትሮቹ። ከ20 ዓመታት በፊት ተፈጻሚ በተደረገው አጨቃጫቂው የመሬት ሪፎርም ወደ 3500 የሚጠጉ ነጭ ገበሬዎችን ከመሬታቸው አፈናቅሎ ነበር። ፕሬዝደንት ሮበርት ሙጋቤ ብዙሃን የሆኑት ጥቁሮች መሬት ይገባቸዋል በማለት ከነጭ ገበሬዎች መሬት መንጠቃቸው ከምዕራባውያን አገራት ጋር አጋጭቷቸው ነበር። 1980 ላይ ዚምባበዌ አናሳ ከሆኑት የነጭ አገዛዝ ነጻነቷን አግኝታ ነበር። በወቅቱ ለእርሻ ምቹ የሆነው አብዛኛው የአገሪቱ የእርሻ መሬት 4000 በሚሆኑ ነጭ ገበሬዎች ተይዞ ነበር። ሙጋቤ ‘በቅኝ ግዛት የተበላሸውን የሃብት ክፍፍል ለማስተካከል’ በማለም ነበር የመሬት ይዞታዎችን ከነጭ ገበሬዎች የቀሙት። ባለፈው ግንቦት ወር ላይ የፕሬዝደንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ መንግሥት በኃይል ከይዞታቸው ላይ እንዲፈናቀሉ ለተደረጉ ነጭ ገበሬዎች 3.5 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል መስማማቱ ይታወሳል።
news-48960646
https://www.bbc.com/amharic/news-48960646
ደቡብ አፍሪካ በወሮበሎች ላይ ሠራዊቷን ኬፕታውን ውስጥ አሰማራች
የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት ኬፕታውን ውስጥ በብጥብጥ ወደሚታመሱት አካባቢዎች መሰማራቱ ተነገረ።
ከደቡብ አፍሪካ ትላልቅ ከተሞች አንዷ በሆነችው ኬፕታውን ውስጥ በሚገኙ ሦስት አካባቢዎች ውስጥ ያለመረጋጋት በማጋጠሙ ነው ወታደሮች እንዲሰማሩ የተደረገው። ከከተማዋ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፤ ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ከባድ ግጭት በከተማዋ የሚገኙ የወሮበላ ቡድኖች በሚቆጣጠሩት አካባቢ በይገባኛል ሳቢያ የተቀሰቀሰ ነው። ግጭቱን ተከትሎም የበቀል ጥቃት ተባብሷል። • ራማፎሳ አዲሱን ካቢኔያቸውን ይፋ አደረጉ ቅዳሜና እሁድ ፊሊፕ ኢስት በተባለው የከተማዋ አካባቢ በጥይት የተገደሉትን ጨምሮ ከባለፈው ከአርብ ጀምሮ ቢያንስ 20 ሰዎች በግጭቱ ተገድለዋል። የከተማዋ የፖሊስ ኃይል ኃላፊ የሆኑት ቤኪ ሲሌ፤ የሠራዊቱን በከተማዋ ውስጥ መሰማራትን በተመለተ ሲናገሩ፤ የነዋሪውን ደህንነት ለማስጠበቅ "ለየት" ያለ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል። "ቤት ለቤት በመሄድ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎችን እንሰበስባለን፣ የሚፈለጉ ወንጀለኞችን እንይዛለን እንዲሁም የቀሩትና በዋስ ከእስር የወጡ ወንጀለኞችንም በቁጥጥር ስር እናውላለን" ሲሉ የፖሊስ ኃላፊው ለመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል። • ኢትዮጵያዊያን ዛምቢያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ የሚጠበቁት ወታደሮች እስኪደርሱ ድረስ የጦር ሠራዊቱ እስካሁን ባልተሰማራባቸው የከተማዋ አካባቢዎች ከፍተኛ መጠን ያለው የፖሊስ ኃይል ተሰማርቷል። ምንም እንኳን የከተማዋ ባለስልጣናትም የነዋሪውን ሰላምና መረጋጋት ለመጠበቅ ለዓመታት ጥረት ቢያደርጉም፤ ለአጭር ጊዜ ጋብ ከማለት ውጪ በኬፕታውን ውስጥ ከወሮበላ ቡድኖች ጋር በተያያዘ የሚከሰተው ችግር ለበርካታ አስርት ዓመታት የዘለቀ ነው።
news-52271997
https://www.bbc.com/amharic/news-52271997
ልደት፣ ሠርግ እና ሞት በኮሮናቫይረስ ዘመን
ዶ/ር ሺላ አቲኖ (ለዚህ ጽሑፍ ሲባል ስሟ ተቀይሯል) ብዙ ልጆች አዋልዳለች።
በቅርቡ ህክምና መስጫ ውስጥ ያገኘቻት ነፍሰ ጡር ግን ከሌሎቹ ትለያለች። የ32 ሳምንት ነፍሰ ጡር የነበረችው ሴት ኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ኬንያውያን አንዷ ናት። ናይሮቢ የሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ሴቲቱን ለማዋለድ ከተመረጡ ዶክተሮች አንዷ የሁለት ልጆች እናቷ ሺላ ናት። “ቫይረሱ ያለባትን ሴት አንደማዋልድ ማወቅ እጅግ ከባድ ነው” ትላለች። ነፍሰ ጡሯን ለማዋለድ ቀዶ ህክምና ማድረግ ነበረባት። ህክምናውን ስታደርግ ሰውነቷን ብትሸፍንም፤ ከነፍሰ ጡሯ ሴት ሰውነት ፈሳሽ እንደሚወጣና ንክኪ ሊኖር እንደሚችል ማሰብ አስጨንቋታል። “ህክምናውን ጨርሼ ቤቴ ስገባ ልጆቼ ሊያቅፉኝ እጃቸውን ይዘረጋሉ፤ ልብሴን አውልቄ እስክታጠብ ድረስ ግን አልጠጋቸውም።” ይሄ በአካልም በመንፈስም ያደክማል። ወረርሽኙ ኖረም አልኖረም ህጻናት ወደዚህ ዓለም ሲመጡ መቀበል ሥራዬ ስለሆነ አማራጭ የለኝም።” አዲሶቹ ሙሽሮች ፍራንሲስ እና ቬሮኒካ አዲስ ሙሽሮች ናቸው። ኒያሁሩ በተባለ የኬንያ ግዛት የጫጉላ ሽርሽር እያደረጉ ነው። 500 ዘመድ አዝማድ የሚታደመው ሠርግ ደግሰው ነበር። ያልጠበቁት ደርሰና በኮሮናቫይረስ ምክንያት ዓለም እንዳልነበረች ሆነች። ጥንዶቹ እንዳሰቡት 500 ሰው አልጠሩም። ስድስት ሰው ብቻ በተገኘበት በቤተ ክርስትያን ተጋቡ። ቤተሰቦቻቸውና ዘመዶቻቸው ሠርጉ ላይ መታደም አልቻሉም። ጥንዶቹ ኮቪድ-19 ስጋት መሆኑ ሲያበቃ መጋባት ይችሉ ነበር። ነገር ግን “የፈጣሪ ፍቃድ ነው” ብለው ሠርጋቸውን በጣት የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት ማድረጋቸውን ይናገራሉ። “እኔና ቬሮኒካ እንዋደዳለን። መጋባት የምንፈልገው በፈጣሪ ፊት ነው” ይላል የቤተ ክርስቲያን አገልጋዩ ፍራንሲስ። ሠርጋቸው 300 ሺህ የኬንያ ሽልንግ ይፈጃል ተብሎ ነበር። ስድስት ታዳሚ ብቻ ሲኖረው ግን 50 ሺህ ሽልንግ እንዳወጡ ሙሽራው ይናገራል። “ብዙ ወጣት ጥንዶች እየደወሉልን ነው። ድል ያለ ድግስ ደግሰን እዳ ውስጥ ከምንገባ እንደናንተ በቀላል ሠርግ ለመጋባት ወስነናል ብለውናል።” ሀዘን ያጠላበት ቤተሰብ ኬንያ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥላለች። የአገሪቱ ፖሊሶች ይህን ገደብ ለማስጠበቅ ሲዘዋወሩ ያሲን ሁሴን ማዮ የተባለ የ13 ዓመት ታዳጊ መገደሉ ይታወሳል። የሰዓት እላፊ ገደቡ ከታወጀ በኋላ በመላው አገሪቱ በፖሊስ እንግልት የደረሰባቸው ብዙዎች ናቸው። የያሲን አባት ሁሴን ማዮ “ቀን ቫይረሱ ያሰጋናል፤ ማታ ደግሞ ፖሊሶች ያሸብሩናል” ሲሉ የልጃቸው ቀብር ላይ ተናግረዋል። በተለያዩ ኢ-መደበኛ ዘርፎች የተሰማሩ አቅመ ደካማ ኬንያውያን ጭንቅ ውስጥ ናቸው። አንድም በኮሮናቫይረስ በሌላ በኩል ደግሞ በረሀብ እና ፖሊስ በሚሰነዝርባቸው ጥቃት። በያሲን ቀብር ላይ ዘመዶቹና ጓደኞቹ ጸሎት ሲያደርጉ መሳለቂያ የሆኑት ፖለቲከኛ ጄምስ ኦሬንጎ የተቃዋሚው ኦሬንጅ ዴሞክራቲክ ፓርቲ አባል ናቸው። “መኪናዬን እያሽከረከርኩ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ለማድረግ ሄድኩ” ብለው ፖለቲከኛው ትዊት ማድረጋቸው በበርካቶች አስተችቷቸዋል። “እነዚህ ፖለቲከኞች የራሳቸውን መኪና መንዳት ያስገርማቸዋል እንዴ?” ሲሉ ብዙ ኬንያውን በፖለቲከኛው ተሳልቀዋል። ሕዝቡ በወረርሽኙ ሰበብ ጭንቅ ውስጥ ሳለ መኪና መንዳታቸውን ከሚገባው በላይ ያዳነቁት ፖለቲከኛ፤ የብዙሀኑ እውነታ ግድ የማይሰጣቸው ፖለቲከኞች ምሳሌም ተደርገዋል። እድለኛው እስረኛ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መሰራጨቱን ተከትሎ በኬንያ ፍርድ ቤቶች ችሎት በዲጂታል መሣሪያዎች እየተካሄደ ነው። መንግሥት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ከሳለፋቸው ውሳኔዎች አንዱ እስረኞችን መፍታትም ነው። በዚህ ወቅት ፍርድ ቤት ከቀረቡ አንዱ ከመደብር መጽሐፍ ቅዱስ በመስረቅ ተከሶ የነበረው ግለሰብ ነው። እድለኛው እስረኛ ክሱ የተነሳለት ሲሆን፤ መንግሥት 4,800 እስረኞችንም ፈቷል። መጽሐፍ ቅዱስ በመስረቅ የተከሰሰው እስረኛ ነፃ ወጥቶ፤ የኮሮናቫይረስ ስርጭት እንዲቆም መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው እየጸለዩ ያሉ ኬንያውያንን ተቀላቅሏል። (ይህ ጽሑፍ በጆሴፍ ዋሩንጉ ተጽፎ፤ “ሌተርስ ፍሮም አፍሪካን ጆርናሊስትስ” የተባለውና የአፍሪካ ጋዜጠኞችን ጽሑፍ የሚያስተናግደው አምድ ላይ የወጣ ነው።)
news-51188560
https://www.bbc.com/amharic/news-51188560
ማሽተት የማይችሉ ሰዎች ምን ዓይነት ሕይወት ይመራሉ?
መቼም የምንወደው ሽታ ይኖራል፤ የምግብ ወይንም የልብስ አሊያም የምንወደው ሰው ሸታ። ከአንድ ጥሩ ወይንም መጥፎ ትዝታ ጋር አጣምረነውም ይሆናል።
አምስቱ የስሜት ህዋሳት መካከል አንዱ ማሽተት ነው። ጋብሪዬላ ግን ከመወለዷ ጀምሮ ማሽተት አትችልም። እውን ማሽተት አለመቻል ምን ይመስላል? «ምግብ ምን ምን እንደሚል አላውቅም። ትኩስ ነገርም ሆነ ጣፋጭ ወይም የሚያቃጥል ነገር ምን አይነት ሽታ እንዳለው አላውቅም» ትላለች የ22 ዓመቷ ጋብሪዬላ። ብዙዎች ማሽተት አለመቻል ምን እንደሚመስል አያውቁት ይሆናል። የማሽተት ችግር ያለባቸው ሰዎች ቁጥር ከ5 በመቶ እንማይዘል ይገመታል። ማሽተት ያለመቻል ጉዳቶች በሁለት ሊከፈሉ ይችላሉ፤ ልማዳዊና ስሜታዊ በሚል። ከልጅነት እስከ አዋቂነት ተከትሎ የሚመጣ ነው። «ከልጅነቴ ጀምሮ ማሽተት አልችልም። በጣም የሚገርመው ከእኔና እህቴ በቀር ቤተሰባችን ውስጥ ማንም እንዲህ ዓይነት ችግር የለበትም። ምናልባት ከቤተሰብ ዘር ጋር የተገናኘ ሊሆን ይችላል።» ማሽተት እንደማንችል እንዴት እናውቃለን? ጋብሪዬላ ልጅ እያለች በተዘጋጀ አንድ የትምህርት ቤት ዝግጅት ላይ ምን ያህል ባይተዋርነት ተሰምቷት እንደነበር አትዘነጋውም። «ሁሉም ጓደኞቼ ስለሽታ ነበር የሚያወሩት። የዚያኔ ነው ማሽተት እንደማልችል የገባኝ። ሁሉም ምሳሌ እያጣቀሰ ሲያወራ እኔ ግን ምንም የማስታወሰው ነገር አልነበረም።» ጋብሪዬላ ማሽተት አለመቻሏ በልጅነቷ ልታስታውሳቸው የማትፈልጋቸው ክስተቶች እንዲገጥሟት አድርጓል። «እሣት በጣም ነው የምፈራው። ሁሌም የሚያሳቅቀኝ ተኝቼ እያለሁ ቤቴ ቢቃጠል ሽታው እንደማይቀሰቅሰኝ ሳስብ ነው።» ልጅ እያለች የእሣቱ ሃሳብ በጣም ያስጭንቃት እንደነበር የምታወሳው ጋብሪዬላ አሁን ግን ሁኔታዎችን እየተለማመደች እንደመጣች ትናገራለች። ልማዳዊ ችግር ማሽተት የተሳናቸው ሰዎች ላይ ጥናት ያካሄዱት ተመራማሪው ፕሮፌሰር ካርል ፊልፖት ማሽተት አለመቻል ችግር ላይ ሊጥል እንዲሚችል ያሳስባሉ። ጭስ ወይንም የጋዝ ሽታ ማሽተት የማይችሉ ሰዎች ለችግር ሊጋለጡ ይችላሉ ይላሉ። ጋቢም የምትለው ይሄንኑ ነው። «አስታውሳለሁ አንድ ጊዜ ምግብ እያበሰልኩ እናቴ መጣችና ቤቱ በጋዝ ሽታ መታፈኑን ነገረችኝ። ሁኔታው በጣም አስደንግጦኝ ነበር።» በመሰል ክስተቶች የታጀበ ሕይወት እንዳሳለፈች የምትናገረው ጋብሪዬላ አሁን እጅግ በጣም ጠንቃቃ ሰው እንደሆነች ትናገራለች። የውጭውን ዓለም ማሽተት ብቻ አይደለም ትልቅ ችግር የሆነው ይላሉ ተመራማሪው። ጥናቱ ላይ የተሳተፉ ሰዎች ከፍተኛ መሸማቀቅ የሚያደርስባቸው ራሳቸውን ማሽተት ያለመቻላቸው ጉዳይ መሆኑን በመጨመር። ይህ ያስጨነቃት ጋብሪዬላ አንድ መላ ፈጥራለች። «ከወላጆቼ ጋር ሆነን አንድ መላ ዘየድን - የምልክት ቋንቋ። ከጓደኞቼ ጋር ቤት ስመጣ ጠረኔ ትክክል ካልሆነ አንድ ምልክት ይሰጡኛል፤ የዚያኔ ወደ መታጠቢያ ቤት እሮጣለሁ። ጋብሪዬላ 'ኮንቴምፖራሪ' የተሰኘ ዳንስ ባለሙያ ናት። ዳንስ ደግሞ ብዙ እንቅስሴ ይጠይቃል። «ሽቶም ሆነ ሌላ ሽታ ያለው ነገር ኖሮኝ አያውቅም፤ የአበባ ሽታም ሆነ መዓዛ ያለው የገላ መታጠቢያ ኖሮኝ አያውቅም፤ አይመቸኝምም። ቢሆንም ዳንሰኛ ስለሆንኩ 'ዲዮዶራንት' እጠቀማለሁ።» ጋቢ ማሽተት አለመቻል የሚታፈርበት አይደለም ትላለች። ዋናው ነገር በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች ማሽተት እንደማይችሉ ማሳወቅ ነው። ግልፅ መሆን ይጠቅማል ስትል ትመክራለች። «ሁሌም አጠገቤ ያሉ ሰዎች ማሽተት እንደማልችል እንዲያውቁ አደርጋለሁ። 'እባካችሁ ንገሩኝ፤ አይዟችሁ አልቀየማችሁም' እላቸዋለሁ።» ጋብሪዬላ ማሽተት ብችል ብላ ተመኝታ ታውቅ ይሆን? - «ኖሮኝ የማያውቅ ስለሆነ ያስፈልገኛል ብዬ ድርቅ አልልም። ብሞክረው ግን ደስ ይለኛል፤ ላጣጥማቸው የማልችላቸወን ነገሮች ማጣጣም እፈልጋለሁ።»
news-53742959
https://www.bbc.com/amharic/news-53742959
ኮሮናቫይረስ፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተገለፀ
የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችና በተለያዩ መስኮች ላይ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ለኮሮናቫይረስ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል።
ይህንን በተመለከተም ባለፈው ሐምሌ ወር ላይ የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለው በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 ከተያዙት ሰዎች መካከል 10 በመቶዎቹ የጤና ሠራተኞች ሲሆኑ በአፍሪካም ከ10 ሺህ በላይ የህክምና ባለሙያዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ወረርሽኙ መኖሩ ከታወቀ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘ ተነግሯል። ይህንን በተመለከተ ቢቢሲ በአገሪቱ ውስጥ አንዳንድ አካባቢዎች ያሉ የጤና ባለሙያዎች ስላሉበት ሁኔታ ለማወቅ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በሲዳማ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የዳሰሳ ቅኝት አድርጓል። በዚህም በሁሉም ክልሎች የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ለኮቪድ-19 ያላቸው ተጋላጭነት አሳሳቢ መሆኑን ተገንዝቧል። በተጨማሪም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ዘንድ እየተስፋፋ መሆኑን ያነጋገርናቸው ክልሎች የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። የጤና ቢሮ ኃላፊዎቹ ለቢቢሲ እንዳሉት ባለሙያዎቹ በተለያየ ምክንያት ለቫይረሱ የተጋለጡ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ከጥንቃቄ ጉድለት፣ ለመከላከያነት የሚያገለግሉ የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት እጥረት መኖር እና በሌሎች ስፍራዎች በሚኖር የቫይረሱ ተጋላጭነት ምክንያት መያዛቸውን ተናግረዋል። በትግራይ ክልል እስካሁን ድረስ ከ30 በላይ በኮቪድ-19 የተያዙ የህክምና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች መኖራቸውን የክልሉ የኮሮናቫይረስ ሎጀስቲክስ አስተባባሪ አቶ ጣዕመ አረዶ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ባለሙያዎቹ ከሥራ ቦታ ውጪ በነበራቸው ተጋላጭነት፣ ከቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር በነበራቸው ንክኪ፣ በጤና ተቋማት ውስጥ የኮሮናቫይረስ መከላከያ በቂ አቅርቦት ባለመኖሩ ምክንያት መያዛቸውን ጨምረው ተናግረዋል። በማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል ለይቶ ማቆያ የሚሰሩት ዶ/ር ሳምሶን ነጋሲ የቫይረሱ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ለቢቢሲ ገልፀዋል። "በአላማጣ በላብራቶሪ ቴክኒሺያንነት የሚሰሩ ሰባት ባለሙያዎች በቫይረሱ ተይዘዋል" ያሉት ዶ/ር ሳምሶን፣ በአይደር ሆስፒታል ሦስት ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ በርካታ የህክምና ባለሙያዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል ሲሉ ይናገራሉ። በዚህም የተነሳ ሆስፒታሉ ከድንገተኛ፣ ማዋለጃ እና አንዳንድ ህክምናዎች ውጪ ሌላው ክፍል ህክምና እየሰጠ አለመሆኑን ገልፀዋል። ዶ/ር ሳምሶን በህክምና ማዕከላቱ የሕክምና እቃዎች አቅርቦት ችግር መኖሩንም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ለክልሉም ሆነ ለፌደራል አካላት ያለባቸውን ችግር ቢያቀርቡም እስካሁን መፍትሄ አለማግኘታቸውን ጨምረው አስረድተዋል። በአማራ ክልል በአሁኑ ሰዓት በስፋት በኮሮናቫይረስ ከተያዙት የኅብረተሰብ ክፍሎች መካከል የህክምና ባለሙያዎች እንደሚገኙበት የገለፁት ደግሞ የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኅብረተሰብ ጤና ኢመርጀንሲ ማኔጅመንት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ አሌ አያል ናቸው። ጨምረውም ለወረርሽኙ ተጋላጭ ናቸው የሚባሉት የህክምና ባለሙያዎች በክልሉ በተለየ ሁኔታ ተጠቅተዋል ባይባልም፤ አሁን ግን ቁጥሩ እየጨመረ በመምጣት 23 ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መረጋገጡን ለቢቢሲ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ አስተዳደር 21 የሕክምና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን የከተማዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለቢቢሲ ማረጋገጡ ይታወሳል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ስንታየሁ ደበሳ እንደተናገሩት በሕክምና ዘርፍ ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸው እተደረገ ያለውን ወረርሽኙን የመከላከል ሥራን ያዳክመዋል የሚል ስጋት አለ ብለዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። "የጤና ባለሙያዎቻችን በቫይረሱ እየተያዙ መምጣት ወረርሽኙን ለመከላከል የምናደርገውን ጥረት ያዳክማል" ሲሉም በአስተዳደሩ በኩል ያለውን ስጋት ለቢቢሲ ተናግረዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪዋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጤና ባለሙያዎቹና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቹ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡት በሥራ ቦታቸው ላይ እያሉ ነው። በሽታውን ለመከላከል አስፈጊ የሆኑ አቅርቦቶችን አስተዳደሩ በበቂ ሁኔታ ማቅቡንና ገልጸው "እስካሁን ድረስ እጥረት የለብንም" ብለዋል። ነገር ግን በሕክምና ተቋማቱ የሚኖሩ ንክኪዎች ባለሙያዎቹን ለቫይረሱ ማጋለጡን የሚናገሩት አስተባባሪዋ፤ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገ ውይይት ለቫይረሱ የተጋለጡት በየትኛው ጊዜ እንደሆነ ለማለየት እንደሚቸገሩ ገልፀዋል። በህክምና ተቋማቱ ያሉ ሁኔታዎች እንደሚያሳዩት ግን ይላሉ ባለሙያዋ "በሕክምና ሥራ ላይ እያሉ ተጋላጭ መሆናቸውን ነው" በማለት ባለሙያዎቹ እየወሰዱ ያሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎችን መፈተሽ እንደሚያስፈልግም ለቢቢሲ ተናግረዋል። በኦሮሚያ ክልል በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን በሁሉም የክልሉ ዞኖችና ከተሞች ቫይረሱ መከሰቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል። በክልሉ እስካሁን ድረስ 1827 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል 34 የሚሆኑት የጤና ባለሙያዎች መሆናቸውን የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ኃላፊ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረጃ አብደና ለቢቢሲ ገልጸዋል። የጤና ባለሙያዎች በብዛት የተገኙት መደበኛ ህክምና በሚሰጡ ሆስፒታሎችና ጤና ጣብያዎች ውስጥ መሆናቸውን አቶ ደረጀ ጨምረው ተናግረዋል። የሲዳማ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ማቴ መንገሻ በበኩላቸውእስከ ዛሬ ድረስ በሲዳማ ክልል 13 የሕክምና ባለሙያዎች እና ሁለት ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተናግረዋል። በኮቪድ-19 ከተያዙት የህክምና ባለሙያዎች መካከል ወደተለያየ ስፍራ ሄደው ራሳቸውን ለቫይረሱ ያጋለጡ፣ በሚሰሩባቸው ተቋማት አካባቢ ባለ የጥንቃቄ ጉድለት እንዲሁም የህክምና ቁሳቁስ እጥረት በመኖሩ የተነሳ የተጋለጡ እንደሚገኙበት አብራርተዋል።
news-45118554
https://www.bbc.com/amharic/news-45118554
ካለሁበት 43፡" የናይሮቢ ነዋሪ በጣም የዋህ ህዝብ ነው"
ፊልሞን አታኽልቲ እባላለሁ። በናይሮቢ ኬንያ ነው የምኖረው። ናይሮቢ መኖር ከጀመርኩኝ ሶስት አመታት ሆኖኛል። ቤተሰቦቼ እዚህ ስለሚኖሩ ከነእሱ ጋር አብሮ ለመስራት ብዬ ነው ወደ ናይሮቢ የመጣሁት።
በናይሮቢ ከተማ ኢስሊ በሚባል አካባቢ በአንድ የኢትዯጵያ ሬስቶራንት ስራ አስኪያጅ ነኝ። የምኖረው ደግሞ ዌስትላንድ በሚባል ሰፈር ነው። ኬንያን ከኢትዮጵያ ጋር ሳወዳድራት በተለይ ናይሮቢ በጣም በተፈጥሮ ሃብቷ የታደለች አረንጓዴ ከተማ ናት። የአየር ሁኔታዋም በጣም ደስ የሚልና ተስማሚ ነው። በናይሮቢም ይሁን በአጠቃላይ በኬንያ ብዙ ተፈጥሯዊ የመዝናኛ ስፍራዎች አሉ። ይህ ደግሞ ለናይሮቢ ከተማ ተጨማሪ ውበት ፈጥሮላታል። • ካለሁበት 40: "ካለ ቪዛ ወደ 127 አገራት መጓዝ እችላለሁ" • ካለሁበት 41: ከባሌ እስከ ቻድ የተደረገ የነጻነት ተጋድሎ ኡጋሊ፣ ማራጓይ እና ጊቴሪ፡ በጣም ተወዳጅ የኬንያ ባህላዊ ምግቦች ናቸው። እኔ ግን የእንጀራ አፍቃሪ ስለሆንኩኝ፤ ለኬንያ እና ለሌሎች ሀገራት ምግቦች እስከዚህም ነኝ። ኡጋሊና ጊቴሪ የሚባሉት የኬንያ ባህላዊ ምግቦች በተለይ ደግሞ እንጀራ በሽሮ በጣም ነው የምወደው። አብዛኛውን ጊዜ እንጀራ ነው የምመገበው። ሃገሬ ሁሌም ይናፍቀኛል፤ በተለይ ደግሞ በመቐለ ከተማ የምትገኘው ያደግኩባት ጅብሩኽ ቀበሌ እጅግ ትናፍቀኛለች። የሚገርመኝ ነገር ያደግኩበት አካባቢ አሁን ከምሰራበት ኢስሊ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ጋር በጣም ነው የሚመሳሰለው። ኢስሊ ማለት በናይሮቢ ትልቁ የንግድ ገበያ ነው። ከተለያዩ አገሮች የሚመጡ ነጋዴዎች ኢስሊን ሳይረግጡ፤ ሳይገበያዩ አይመለሱም። በተለይ ደግሞ የሶማሌያ ዜጎች። በጦርነት ምክንያት ቀዬያቸውን ጥለው ለሚመጡ ስደተኛ ሶማልያውያን ሁለተኛ ቤታቸው እንደ ማለት ነች። በጣም በርካታ ሶማልያውያን በዚሁ አከባቢ ይገኛሉ። • ካለሁበት ልዩ መሰናዶ፡ ሎስ አንጀለስ ከዐብይ አህመድ በፊትና በኋላ • ካለሁበት 38፡ ''ሳላስበው ወደ ትምህርት ዓለሙ የመቀላቀሉን ሕልሜን አሳካሁኝ'' ኢስሊ ትልቅ ገበያ ስለሆነ ሁሌም ግርግር አይለየዉም። ለዚህም ነው ካደግኩበት ጅብሩክ ጋር የሚመሳሰልብኝ። ጅብሩክ በመቐለ ከተማ በሰፊው የሚታወቅና ግርግር የሚበዛበት ሰፈር ነው። እናም አብሮ አደጎቼን ሳገኛቸው ከጅብሩክ ወደ ጅብሩክ ነው መጣሁት እላቸዋለሁ። ኢስሊ፤ በኬንያ ትልቁ ገበያ መጀመሪያ የመጣሁ አካባቢ የሰዎቹን ባህሪ መረዳት ከብዶኝ ትንሽ ተቸግሬ ነበር። ከዚያ ውጪ ግን እምብዛም ያስቸገረኝ ነገር አልነበረም። በኬንያ አስቸጋሪ የሚባለው ወቅት ምርጫ ሲደርስ ፤ በተለይ የዛሬ ዓመት የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፍፁም አልረሳውም። የኬንያ ፖለቲካ ከባድ ነው። በምርጫ ወቅት ሁሉም የሚያሰፈልገውን ገዝቶ ቤቱን ዘግቶ ይቀመጣል። ምክንያቱም ንግድ ቤቶችም ዝግ ይሆናሉ። በሰላማዊ ሰልፍ ወቅት የድጋፍም ይሁን የተቃውሞ ሰልፍ ከሚያደርጉ ሰዎች ውጪ ማንም ሰው ዝር አይልም። በተቀናቃኝ የፖለቲካ ተወዳዳሪዎች ደጋፊዎች መካከል ደም ያፋሰሰ መጥፎ ሁኔታም ተፈጥሮ ያውቃል። ፊልሞን በሞምባሳ ባህር ዳርቻ በናይሮቢ ሁኔታው በጣም ከባድ ስለነበረ፤ ምርጫው እስኪጠናቀቅ ድረስ ሞምባሳ በምትባለው የባህር ዳርቻ ከተማ ነው ያሳለፍኩት። በተረፈ የናይሮቢ ነዋሪ በጣም የዋህ ህዝብ ነው። ይሁን እንጂ አንድ ከተማው የሚታወቅበት መጥፎ ልማድ አለ። እሱም ሙስና ነው። ናይሮቢን የመቀየር ዕድል ቢሰጠኝ፤ መጀመሪያ የማጠፋው በሰፊው ተንሰራፍቶ የሚገኘውን ሙስና ነበር። ሃገሬ ኢትዮጵያ ሁሌም ከአይኔ አትጠፋም። ሁሌም ትናፍቀኛለች። አሁን በቅፅበት ራሴን የሆነ ቦታ መላክ ብችል፤ በሃገሬ በተለይ መቐለ ላይ ብገኝ ደስ ይለኛል። ለላየን ፅጋብ እንደነገራት የ'ካለሁበት' ቀጣይ ክፍሎችን ለማግኘት ፦ ካለሁበት 44፡ "ዘላቂ ሰላም መኖሩን ሳረጋግጥ ነው ወደ ሃገሬ የምመለሰው’’
news-56520049
https://www.bbc.com/amharic/news-56520049
ኬንያ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የሚገኙባቸውን ጣቢያዎች ልትዘጋ ነው
ኬንያ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የሚገኙባቸውን የዳዳብ እና የካኩማ መጠለያ ጣቢያዎችን እዘጋለሁ አለች።
በኬንያ የሚገኘው የደደብ መጠለያ ጣቢያ ይህ የኬንያ መንግሥት ውሳኔ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የምሥራቅ አፍሪካ ስደተኞችን እታ ፈንታ አጣብቂኝ ውስጥ የከተተ ሆኗል። የኬንያ መንግሥት ዳዳባ እና ካኩማ የሰደተኛ መጠለያ ጣቢያዎችን እንደሚዘጋ ይፋ ያደረገው ትናንት ሲሆን፤ ኬንያ የተባበሩት መንግሥታት ስደተኞቹን ወዴት እንደሚወስድ እንዲያሳውቃት የ14 ቀናት የጊዜ ገደብ ሰጥታለች። በሁለቱ መጠለያ ጣቢያዎቹ ውስጥ በዋናነት ከሶማሊያ እና ከደቡብ ሱዳን የመጡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰደተኞች ይገኛሉ። በዳዳብ የሰደተኞ መጠለያ ጣቢያ ከ218 ሺህ በላይ ስደተኞች የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹ የሱማሊያ ዜጎች ናቸው። በካኩማ ደግሞ ወደ 200 ሺህ የሚጠጉ ሰደተኞች የሚገኙ ሲሆን በዚህ መጠለያ ጣቢያ ደግሞ ትልቁን ቁጥር የሚይዙት ከደቡብ ሱዳን የተፈናቀሉ ናቸው። የተባበሩት መንግሥት የሰደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እንደሚለው ጥር 2013 ዓ.ም ላይ 29 ሺህ 718 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኬንያ ይገኛሉ። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሚገኙት በካኩማ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ነው። ኬንያ እነዚህን ሁለት የሰደተኛ መጠለያ ጣቢያዎችን ለመዝጋት ስትወስን የአሁኑ የመጀመሪያዋ አይደለም። በተለያዩ ወቅቶች ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በሚደረግ ንግግር ኬንያ መጠለያ ጣቢያዎቹን ለመዝጋት የሰጠቻቸውን ውሳኔዎች ስትሽር ቆይታ ነበር። ይሁን እንጂ የኬንያ የአገር ውስጥ ሚንስትር ፍሬድ ማቲያንጊ፤ ትናንት መጠለያ ጣቢያዎቹን የመዝጋት ወሳኔን በተመለከተ ኬንያ ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ምንም አይነት ንግግር እንደማይኖራት ተናግረዋል። የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትሩ በኬንያ ላይ የሚቃጡ የሽብር ጥቃቶች መነሻ መጠለያ ጣቢያዎቹ መሆናቸውን እንደ ምክንያት በማንሳት አገራቸው መጠለያ ጣቢያዎቹን ለመዝጋት መወሰኗን አስረድተዋል። ፍሬድ ማቲያንጊ በቅርቡ የኬንያ እና የሱማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት መሻከር መጠለያ ጣቢያውን ለመዝጋት ውሳኔ ላይ ካደረሱ ምክንያቶች መካከል እንደሚጠቀስም አውስተዋል። በአሁኑ ወቅት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ስደተኞች በኬንያ የሚገኙ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ቁጥር የያዙት ደግሞ ሶማሊያውያን ናቸው። የተባበሩት መንግሥት የሰደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በበኩሉ የኬንያ መንግሥት መጠለያ ጣቢያዎቹን ከመዝጋቱ በፊት የሰጠው ቀነ ገደብ አነስተኛ መሆኑን አስታውቋል። ኮሚሽኑ የኬንያ መንግሥት ውሳኔ ስደተኞች ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ጫና ከፍተኛ መሆኑን እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝም ስጋት እንደሆነ አስታውቋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ከኬንያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክር አስታውቋል። የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ስጋት ኢትዮጵያዊው ስደተኛ ሞሐመድ አብዱላሂ ላለፉት 27 ዓመታት በዳዳብ የሰደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ መኖራቸውን ይናገራሉ። በቆይታቸውም ትዳር መስረተው ሰባት የቤተሰብ አባላትን እንደሚያስተዳድሩ ይናገራሉ። ስደተኛው አቶ ሞሐመድ የኬንያ መንግሥት ውሳኔ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ እጣ ፈንታቸውን አጣበቂኝ ሁኔታ ውስጥ ሊከት እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል። "በጣም ተጨንቀዋል። ሰው ሁሉ 'ምንድነው ምንሆነው' እያለ እየተጨነቀ ነው" በማለት ከኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች በተጨማሪ የደቡብ ሱዳን፣ የኡጋንዳ እና የቡሩንዲ ዜጎች ስጋት እንደገባቸው ያስረዳሉ። ሌላኛው በዳዳብ የሰደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ነዋሪ የሆነ እና ስሜ አይጠቀስ ያለ ኢትዮጵያ የኦሮሞ ማኅብረሰብ ተወካይ ውሳኔው ተግባራዊ የሚሆን አይመስለኝም ብሏል። ከዚህ ቀደም የኬንያ መንግሥት በተደጋጋሚ የሰደተኞች መጠለያ ጣቢያዎቹን እዘጋለሁ ካለ በኋላ ውሳኔው መሻሩን በማስታወስም፤ "መንግሥት ጣቢያዎቹን እዘጋለሁ ይበል እንጂ በውሳኔው ሊጸና አይችልም የሚል እምነት አለኝ" ይላል። ይህ ወጣት ምንም እንኳ መንግሥት ከሚለው በተቃራኒ ጣቢያዎቹ አይዘጉም የሚል ግምት ቢኖረውም፤ በመጠለያ ጣቢያዎቹ ውስጥ የሚኖሩ ስደተኞች ግን በውሳኔው ስጋት እንዳደረባቸው ለቢቢሲ ተናግሯል።
news-56651318
https://www.bbc.com/amharic/news-56651318
በቄለም ወለጋ ታጣቂዎች የኤሌክትሪክ መስመር ላይ በፈጸሙት ጥቃት መብራትና ውሃ ከተቋረጠ አንድ ወር አለፈው
የቄለም ወለጋ ደምቢዶሎን ጨምሮ በዘጠኝ የዞኑ ወረዳዎች የመብራት እና የውሃ አገልግሎት ከተቋረጠ ከአንድ ወር በላይ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ለቢቢሲ አስታወቀ።
በዞኑ የመብራት አገልግሎት የተቋረጠው ከደምቢዶሎ ወደ ጋምቤላ የተዘረጋው የኤሌትሪክ መስመር አንፊሎ የሚባል ቦታ ላይ በጠዓታቂዎች በመቋረጡ እና የኤሌትሪክ ተሸካሚ ምሰሶዎች ጉዳት ስለደረሰባቸው መሆኑን የዞኑ ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሃምባ ረጋ ተናግረዋል። የዞኑ ዋና ከተማ የሆነችውን ደምቢዶሎን ጨምሮ ሰዩ፣ ጅማ ሆሮ፣ ጋዎ ቄቤ፣ ያማ ሎጊ ወለል የሚባሉ ወረዳዎች የኤሌትሪክ ኃይል መቋረጥ ካጋጠማቸው መካከል ይጠቀሳሉ። ከዚህ በተጨማሪ የአብዛኛው የዞኑ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ከመብራት ኃይል ጋር የተገናኘ በመሆኑ ደምቢዶሎን ጨምሮ በዘጠኝ ወረዳዎች ውሃም ከተቋረጠ ከወር በላይ መሆኑን ኃላፊው ገልፀዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የደምቢዶሎ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ባለፈው አንድ ወር ከአካባቢያቸው ርቀው በመሄድ ውሃ ከወንዝ እየቀዱ እነደሚጠቀሙ፣ ሌሎቹ ደግሞ የዝናብ ውሃ እያጠራቀሙ እንደሚገለገሉ ተናግረዋል። እህል ለማስፈጨት ራቅ ብሎ ያለ በነዳጅ የሚሰራ ወፍጮ ቤት በመሄድ እንደሚያስፈጩ የተናገሩት አንድ የደምቢዶሎ ነዋሪ፣ "ከባድ ችግር ውስጥ ነው ያለነው፤ የምንበላውን ልናጣ እንችላለን" ሲሉ ስጋታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የችግሩ መነሻ ምንድን ነው? ከደምቢዶሎ ወደ ጋምቤላ ኤሌትሪክ ለማስተላለፍ የተዘረጋው መስመር የተቋረጠው በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መሆኑን የዞኑ ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ ለቢቢሲ አስረድተዋል። "የተቆረጠውን መስመር ለመጠገን መንግሥት ባለሙያዎች ወደ ስፍራው ልኮ ነበር። ነገር ግን ታጣቂዎቹ የሚጠቀሙባቸውን ሁለት መኪኖች አቃጥለውባቸው እነርሱንም ለሦስት ቀናት አግተው ከደበደብዋቸው በኋላ በአራተኛው ቀን ለቅቀዋቸዋል" ይላሉ ኃላፊው። በኦነግ ሸኔ ታግተው የነበሩት የኤሌትሪክ ኃይል ባለሙያዎች ሰባት ሲሆኑ የተቃጠሉት መኪኖች ደግሞ የዞኑ ቅርንጫፍ ቢሮ መኪኖች የሆኑ አንድ ፒክ አፕና አንድ አይሱዙ መሆናቸውን ጨምረው ገልፀዋል። ይህ ድርጊት የተፈፀመው ባለፈው ሳምንት መሆኑን የሚናገሩት ኃላፊው ባለሙያዎቹ ጥቃቱ ያጋጠማቸው አንፊሎ ወረዳ ዳዎ ቶፒና ያሬድ የሚባል አካባቢ መካከል መሆኑን ተናግረዋል። እነዚህ ባለሙያዎች መታገታቸውን ተከትሎ የመንግሥት የፀጥታ አካላት ክትትል እያደረጉ የነበረ ቢሆንም፣ በአራተኛው ቀን ታጣቂዎቹ እንደለቀቋቸው ይናገራሉ። " ባለሙያዎቹ አሁን ተደብቀው ነው ያሉት፤ እነርሱን አግኝተን የጥገናው ሥራ እንዲቀጥል ማድረግ አልቻልንም" የሚሉት ኃላፊው፣ በዞን አስተዳደሩ በኩል የተቋረጠውን መብራት የማስቀጠል ዝግጁነት መኖሩን ገልፀዋል። ኃላፊው አክለውም ባለሙያዎቹን ስላላገኘን የጥገናውን ስራ አልጀመርንም ሲሉ ያለውን ሁኔታ ለቢቢሲ አስረድተዋል። በተጨማሪም አሁንም እንደ ጊዳሚ እና አንፊሎ ባሉ የዞኑ ወረዳዎች የፀጥታ ችግር መኖሩን የዞኑ ኃላፊ ይናገራሉ። በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ አራት ዞኖች በተለይም በምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች ውስጥ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው የተባሉ ታጣቂዎች በነዋሪዎች: በአካባቢ ባለስልጣናትና በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ እንደሆነ ሲነገር መቆየቱ ይታወቃል። ይህ ታጣቂ ቡድን በመንግሥት ኃላፊዎች እና በንፁኀን ዜጎች ግድያ በተደጋጋሚ ይወነጀላል።
news-55367983
https://www.bbc.com/amharic/news-55367983
ኮቪድ-19፡ የቺሊው ፕሬዚደንት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ 'ሰልፊ' በመነሳታቸው ተቀጡ
ደቡብ አሜሪካዊቷ አገር ቺሊ ፕሬዚደንት ሴባስቲያን ፒኔራ የኮሮናቫይረስ ሕግን በመጣሳቸው 3 ሺህ 500 ዶላር ገንዘብ ተቀጡ።
ፕሬዚደንቱ ቅጣቱ የተጣለባቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ 'ሰልፊ' በመነሳታቸው ነው። ሰባስቲያን በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ይኸው ከአንዲት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ካላደረገች ሴት ጋር የተነሱት ፎቶ በስፋት ከተሰራጨ በኋላ ይቅርታ ጠይቀዋል። ፕሬዚደንቱ በካቻጓ በሚገኘው ቤታቸው አቅራቢያ ባለ የባህር ዳርቻ ሴትዮዋ አብረዋት ፎቶ እንዲነሱ ስትጠይቃቸው "የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ነበረብኝ" ብለዋል። ቺሊ ሕዝብ በሚገለገልባቸው ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን የሚያዝ ጥብቅ ሕግ አላት። ይህንን ሕግ መጣስም የገንዘብና የእስር ቅጣትን ጨምሮ ሌሎች ቅጣቶችን ያስከትላል። ፕሬዚደንቱ በተለያዩ ጊዜ የሚነሷቸው አነጋጋሪ ፎቶግራፎች ፖለቲካዊ መዘዝ እያስከተሉ ነው። ባለፈው ዓመት በዋና መዲናዋ ሳንቲያጎ እኩልነትን የሚጠይቅ ተቃውሞ በተካሄደ ምሽት በአንድ የፒዛ ድግስ ላይ ፎቶ በመነሳታቸው ቁጣ አስነስቶ ነበር። በዚያው ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ገደብ ሳይጣል በፊት ፀረ- መንግሥት ተቃውሞ ማዕከል በነበረ አደባባይ ፎቶ በመነሳታቸው በርካቶችን አስቆጥቷል። በሳንቲያጎ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተጣሉ ገደቦችን ተከትሎ አለመረጋጋቶች ተከስተዋል። ከሰኔ ወር ወዲህም በአንድ ቀን ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ እየተያዙ ነው። በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ ፕሬዚደንቱ ሌሎች በሽታውን ለመቆጣጠር የተጣሉ ገደቦች እንዲቀጥሉ የሚያስችለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለ3 ወራት አራዝመዋል። በቺሊ የኮሮናቫይረስ ሥርጭት እየጨመረ ሲሆን በላቲን አሜሪካ በበሽታው የተያዙና የሞቱ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ከተመዘገበባቸው አገራት አንዷ ናት ። እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ በአገሪቷ እስካሁን 581 ሺህ 135 ሰዎች በቨይረሱ የተያዙ ሲሆን 16 ሺህ 051 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሕይወታቸው አልፏል።
news-55000109
https://www.bbc.com/amharic/news-55000109
ትግራይ ፡ ሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ተጠየቀ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማት ሁለት ሳምንት ያለፈውን በኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል የሚካሄደው ግጭት ለማስቆም የሚያስችል አስቸኳይና ጊዜያዊ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቁ።
ጄኔቫ ላይ በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ተቋም ዩኤንኤችሲአር ቃል አቀባይ ባርባር ባሎች "በአስቸኳይ ተግባራዊ የሚደረግ ተኩስ አቁምና የሚያስፈልገው የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ የሚያስችል መተላለፊያ ለማዘጋጀት ነው" ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ግጭቱ ባለበት አካባቢ በመድረስ የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ ማድረግ ያለመቻላቸውን የጠቀሱት ተቋማቱ ከተኩስ አቁሙ በተጨማሪ ለሰላማዊ ሰዎች የእርዳታ አቅርቦት ለመድረስ የሚያሰችል መተላላፊያ እንዲመቻችም ጠይቀዋል። የእርዳታ ድርጅቶቹ እንደሚሉት አስቸኳይ የተኩስ ማቆም ከተደረገና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር ከተከፈተ በግጭቱ ሳቢያ መውጫ አጥተው ለሚገኙ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ድጋፍ ለማቅረብ እንደሚረዳቸው ገልጸዋል። እስካሁን ቢያንስ 33 ሺህ የሚደርሱ ስደተኞች ከኢትዮጵያ የሱዳንን ድንበር ተሻግረው መግባታቸው የተነገረ ሲሆን፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች መርጃ እንደሚለው ግጭቱ የሚቀጥል ከሆነ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት አስከ 200 ሺህ የሚደርሱ ስደተኞች ወደ ሱዳን ሊገቡ ይችላሉ። የመንግሥታቱ ድርጅት ወደ ግጭቶቹ አካባቢዎች የመድረስ ዕድል እንደሌላቸው ገልጸው፤ ነገር ግን አስካሁን ባለው ሁኔታ በቀውሱ ሳቢያ በመቶዎች ምናልባትም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀሩ ስጋት አላቸው። ወደ ሱዳን እየገቡ የሚገኙት ስደተኞች በፍርሃት ውስጥ ያሉና የተራቡ ሲሆኑ ግማሽ የሚሆኑት ደግሞ ህጻናት እንደሆኑ ተነግሯል። ቀደም ብሎ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ተሰደው የመጡ በርካታ ሰዎችን የሚረዳው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤ እየጨመረ የመጣው የስደተኞች ቁጥር በሱዳን መረጋጋት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል የሚል ስጋት አለው። የእርዳታ ድርጅቶች ወደ ሱዳን እየገቡ ላሉት አዲስ ስደተኞች የምግብና የመጠለያ ድጋፍ ለማድረግ የ50 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋቸው ጥሪ አቅርበዋል። በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና በትግራይ ኃይሎች መካከል እተካሄደ ያለው ግጭት ሦስተኛ ሳምንቱን የያዘ ሲሆን፤ ይህንን በመሸሽ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ወደ ሱዳን እየገቡ መሆናቸውን የእርዳታ ድርጅቶች እገለጹ ይገኛሉ።
56179066
https://www.bbc.com/amharic/56179066
የቻይናው ፍርድ ቤት ባል ለቀድሞ ሚስቱ የጉልበት ካሳ እንዲከፍል ወሰነ
በቻይናዋ ዋና ከተማ ቤጂንግ የሚገኝ የፍቺ ክርክር ችሎት ሚስት በትዳር በቆዩባቸው ዓመታት ለሰራችው የቤት ውስጥ ሥራ ባል ካሳ እንዲከፍላት ውሳኔ ሰጠ።
ውሳኔው በቻይና በቅርቡ የፀደቀውን የፍትሃብሔር ሕግን ተከትሎ የተሰጠ ሲሆን ክፍያው ለቤት ሰራተኞች ከሚከፈለው ዋጋ ጋር ተነፃፅሮ በቻይና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሰፊ ክርክር አስነስቷል። የፍርድ ቤቱ መዝገብ እንደሚያስረዳው ቼን የተሰኘው ቻይናዊ ባል ባለፈው ዓመት ነበር ለችሎቱ የፍቺ ማመልከቻውን ያስገባው። ሚስት ዋንግ በበኩሏ ለፍቺው ፍላጎት ሳታሳይ ቆይታ ቼን የቤት ውስጥ ሥራ እንደማይሰራ እና ልጃቸውንም እንደማይንከባከብ ጠቅሳ የገንዘብ ካሳ ጠይቃለች። በቤጂንግ የፋንግሻን ቀጠና ፍርድ ቤትም ለሚስት የፈረደ ሲሆን ባል በየወሩ ሁለት ሺህ ዩአን ቀለብ እንዲቆርጥ ወስኗል። ሚስት በአምስት ዓመት የትዳር ቆይታ ወቅት ላበረከተችው የቤት ውስጥ ሥራ ደግሞ 50 ሺህ ዩአን ይከፈላት ብሏል። ከትላንት በስቲያ ሰኞ ችሎቱን ያስቻሉት ዳኛ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ጥንዶች ሲለያዩ የሚደረግ የንብረት ክፍፍል በተለይም ቁሳዊ የሃብት ክፍፍል ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል። ‹‹ነገር ግን የቤት ውስጥ ሥራ የማይታይ ሃብትን ይፈጥራል›› ሲሉ ዳኛው ገልፀዋል። በያዝነው ዓመት የፀደቀው የቻይና አዲሱ የፍትሃ ብሔር ሕግ ጥንዶች በፍቺ ወቅት ልጆችን በማሳደግ፣ አዛውንት ቤተሰቦቻቸውን በመንከባከብ ወይም ወላጆቻቸውን በመርዳት ላይ አንዱ የበዛ ጫና ከነበረበት በፍቺ ወቅት ካሳ መጠይቅ እንደሚችል ይደነግጋል። ከዚህ ቀደም እንዲህ ያለ ጥያቄ ማንሳት የሚቻለው በጋብቻ ወቅት ቀድመው ከተስማሙ ብቻ ሲሆን ይህም በቻይና ያልተለመደ ድርጊት ነው። ታዲያ በቻይና ሞቅ ያለ ክርክር ያስነሳው ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔን የሚመለከተው ሃሽታግ 570 ሚሊዮን ግዜ የታየ ሆኖ ተመዝገቧል። አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች 50 ሺህ ዩአን ለአምስት ዓመት የቤት ውስጥ ሥራ በጣም ያነሰ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። ‹‹በቤጂንግ አንድ የቤት ሰራተኛ ለአንድ ዓመት ያህል እንኳን ለመቅጠር ይህ ገንዘብ አይበቃም። ውሳኔው ቃላት እስከሚያጥሩኝ አስገርሞኛል፣ ይህ የቤት አመቤትነትን አሳንሶ ማየት ነው›› ሲሉ አንድ አስተያየት ሰጪ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ወንዶች ቀድሞውንም የቤት ውስጥ ሥራዎችን ሃላፊነት መጋራት አለባቸው ሲሉ ሌሎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በተጨማሪም ሴቶች ከጋብቻ በኋላ የሥራ ህይወታቸውን እርግፍ አድርገው መተው እንደሌለባቸው ሌሎች ሃሳባቸውን ሲገልፁ ተደምጠዋል። ‹‹ሴቶች ሁሌም ራሳችሁን ችላችሁ ቁሙ። ሥራችሁን ከጋብቻ በኋላ አትተዉ፤ ለራሳችሁ የራሳችሁ ማምለጫ መንገድ ይኑራችሁ›› የሚለው በማህበራዊ ሚዲያ በጉዳዩ ላይ ከተጋሩ አስተያየቶች አንዱ ነው። አንድ የኢኮኖሚ እና ልማት ትብብር የተሰኘ ተቋም እንዳጠናው ቻይናዊያን ሴቶች በቀን አራት ሰዓት ገደማ ያለክፍያ ሥራ ላይ ያጠፋሉ፤ ይህም ከወንዶች 2.5 እጥፍ ይበልጣል።
news-50670464
https://www.bbc.com/amharic/news-50670464
ከ11 ኪሎ በላይ የኮኬይን ዕጽ አዲስ አበባ ውስጥ ተያዘ
የገቢዎች ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት [ረቡዕ] በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል ሊዘወወር የነበረ ከ11 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን የኮኬይን ዕጽ መያዙን አስታወቀ።
ይህ የተያዘው ኮኬይን የተባለው አደንዛዥ ዕጽ፤ ገበያ ላይ ቢውል ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ዋጋ ሊያወጣ ይችል እንደነበር ሚኒስቴሩ ገልጿል። ዕጹን ከተለያዩ አገራት አንስቶ፣ በአዲስ አበባ በኩል በማለፍ ወደ ሌላ ቦታ ለማዘዋወር ሲሞከር፤ በጉምሩክ የምርመራ ሠራተኞችና በብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት አባላት አማካይነት መያዙ ተገልጿል። የገቢዎች ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ አደንዛዥ እጹን ሲያዘዋውሩ ነበር ተብለው የተያዙት ሁለቱም ሴቶች ሲሆኑ፤ ከተለያዩ አገራትና በተለያዩ በረራዎች ተጉዘው አዲስ አበባ የደረሱ መሆናቸውም ተጠቅሷል። • ዕጽ በማዘዋወር የተጠረጠረችው ናይጄሪያዊት ከእስር ተለቀቀች • "በጥሩ ጤንነት ላይ አይደለችም" የስምረት ካህሳይ ቤተሰቦች • ከፍተኛ መጠን ያለው ዕፅ በአሜሪካና ሜክሲኮ ድንበር ተያዘ በዚህም መሰረት ከደቡብ አፍሪካ የተነሳችውና የዚያው አገር ዜጋ የሆነችው ኖምዛሞ ግላዲየስ ቦዛ 7.4 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን ይዛ በአዲስ አበባ በኩል ወደ ህንዷ ዴልሂ ከተማ የመጓዝ እቅድ ነበራት ተብሏል። ሌላዋ ተጠርጣሪ አንቲቃ ሱለይማን ቂዚ አባሶባ ደግሞ ደግሞ የአዘርባጃን ዜጋ ስትሆን፤ የተነሳችው ከሩሲያዋ ሞስኮ ከተማ ነበር። ግለሰቧ 4 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን ይዛ በአዲስ አበባ በኩል በማቋረጥ ወደ ታይላንዷ ባንኮክ ልትጓዝ ነበር ተብሏል። የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳሳወቀው፤ በአንድ ቀን ብቻ ከሁለቱ ግለሰቦች 11.4 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን በኢትዮጵያ በኩል ወደ ሌሎች አገራት ሊተላለፍ ሲል ተያዟል።
news-45140341
https://www.bbc.com/amharic/news-45140341
በየመን በሳዑዲ የሚመራው ቡድን ከአየር ላይ በሰነዘረው ጥቃት በአውቶቡስ ውስጥ የነበሩ 29 ህፃናት ተገደሉ
በሳዑዲ የሚመራው ቡድን የመን ላይ በሚያደርገው የአየር ጥቃት ቢያንስ 29 ህፃናት እንደተገደሉና 30 እንደቆሰሉ አለም አቀፉ የቀይመስቀል ድርጅት አስታወቀ።
ህፃናቱ በአውቶብስ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ነው ዳህያን በምትባል የገበያ ስፍራ ላይ የተመቱት። በአማፂው ሁቲ የሚመራው የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የሆኑት ግለሰብ የሟቾች ቁጥር 43 የቆሰሉት ደግሞ 61 እንደሆነ ገልጿል። • "የምንመለሰው ያፈረሰን የምርጫ ቦርድ እራሱ ከፈረሰ ብቻ ነው'' ልደቱ አያሌው • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ታጭተዋል? • ሰመጉ በወልዲያ እና አካባቢው የመብት ጥሰት ተፈጽሟል አለ ከሁቲዎች ጋር በሚደረገው ጦርነት በየመን መንግስት የሚደገፈው ጥምረት ድርጊቱ "አግባብ" ነው ሲል ገልጾታል፤ ሆን ተብሎ ንፁኀን ላይ ያነጣጠረ አለመሆኑን ጨምሮ አስታውቋል። የሰብዓዊ መብት ቡድኖች ግን የገበያ ስፍራዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና የመኖሪያ ስፍራዎች ሆን ተብለው ጥቃት ይደርስባቸዋል ሲሉ ይከሳሉ። በዚህ መካከል በተባበሩት መንግስታት የየመን ልዩ ልዑክ የሆኑት የቀድሞው የእንግሊዝ መንግስት ዲፕሎማት፣ ማርቲን ግሪፊትሽ፣ በጦርነቱ ተፋላሚ የሆኑትን ወገኖች መስከረም ላይ ወደ ጄኔቫ በመጋበዝ ለስምምነት በሚረዱ ነጥቦች ላይ ለማወያየት አቅደዋል። ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጦርነቱ ሳይፈታ ከቆየ "የአለም ህዝብ ልክ እንደሶሪያ የፈራረሰች የመንን በቅርብ አመት ውስጥ ይመለከታል። "በየመን የሚደረገው ጦርነት በገፋ ቁጥር የበለጠ እየተወሳሰበ ይሄዳል። የበለጠ የአለም አቀፍ አካላት ፍላጎትና ውጥረት ይኖራል፤ አሁን ካለው በባሰ ሁኔታ ለመፍታትም አስቸጋሪ ይሆናል" ብለዋል። የሁቲ ቃል አቀባይ የሆኑት መሃመድ አብዱል ሳላም ንፁኀን ዜጎች በተሰበሰቡበት ስፍራ ላይ የደረሰውን ጥቃት በሚመለከት ሲናገሩ "ለሰላማዊ ዜጎች ግድ የሌለው" በማለት ጥምረቱን ተችተዋል። አለም አቀፉ የቀይመስቀል ኮሚቴ "በአለም አቀፍ የሰብዓዊ ህግ በጦርነት ወቅት ንፁኀን ከለላ ሊሰጣቸው ይገባል" ያለ ሲሆን የኖርዌይ የስደተኞች ጉባዔ ዋና ፀሀፊ ደግሞ "ማፈሪያ" የሆነ ተግባር በማለት "የህግ የበላይነትን በግድ የለሽነት አሽንቀጥሮ የጣለ" በማለት ድርጊቱን አውግዘዋል። ሴቭ ዘ ችልድረን በበኩሉ ድርጊቱን "ዘግናኝ" ያለ ሲሆን ከዚህ ቀደም በንፁኀን ዜጎች ላይ የደረሱ ጥቃቶችን አካቶ በአፋጣኝ በገለልተኛ ወገን ጥናት እንዲደረግ አሳስቧል።
news-49148614
https://www.bbc.com/amharic/news-49148614
በካሊፎርኒያ ከተገደሉት መካከል የስድስት ዓመት ታዳጊ ይገኝበታል
በካሊፎርኒያ ''ግሎሪ ጋርሊክ'' በተሰኘ የምግብ ፌስቲቫል ላይ በደረሰ ጥቃት ቢያንስ ሶስት ሰዎች መገደላቸውንና 11 ግለሰቦች መቁሰላቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ከሟቾቹ መካከል የስድስት ዓመቱ ታዳጊ ስቴፈን ሮሜሮ ይገኝበታል። በፌስቲቫሉ በመጠናቀቂያ ላይ አንድ ታጣቂ ተኩሶ ከፍቶ ሰዎቹን ገድሏል ተብሏል። ከሟቾቹ መካከል የስድስት ዓመቱ ታዳጊ ስቴፈን ሮሜሮ የሚገኝበት ሲሆን እናቱ እና አያቱ በጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የስቴፈን አባት ሜርኩሪ ኒውስ ለተሰኘ መገናኛ ብዙሃን ሲናገር፤ ጥቃቱ ሲፈጸም እሱ ከ9 ዓመት ሴት ልጁ ጋር በመኖሪያ ቤቱ እንደነበረ እና ባለቤቱ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ሆና እየተፈጸመ ያለውን ነገር በስልክ እንደነገረችው ያስታውሳል። "ልጃችን ከጀርባ በኩል በጥይት እንደተመታ ነገረችኝ" ሲል ተናግሯል። ጥቃት አድራሹ ከፖሊስ ጋር የተኩስ ልውውጥ ካደረገ በኋላ መገደሉ ይፋ ተደርጓል። የጥቃት አድራሹ ማንነት እስካሁን ይፋ ባይደረግም፤ በሰላሳዎቹ አጋማሽ እድሜ የሚገኝ ነጭ ግለሰብ ሲተኩስ እንዳየች ጁሊሳ ኮንትሪራስ የተባለች የአይን እማኝ ለኤንቢሲ ተናግራለች። ሌሎች የዓይን እማኞች እንዳሉት ተኳሹ የወታደር ልብስ ለብሶ ነበር ብለዋል። ፖሊስ ጥቆማው እንደደረሰን ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ሰዓት በቦታው ደርሻለሁ ያለ ሲሆን፤ ከተኳሹ በተጨማሪ በጥቃቱ ላይ ረዳት ሆኖ የተሳተፈ ግለሰብ ስለመኖሩ መረጃው አለኝ ብሏል። •የጠቅላይ ሚኒስትሩ 200 ሚሊዮን ችግኞች •"ኦሮሞ እና ማዳጋስካርን የሚያገናኝ ፖለቲካ እንዳለ አላውቅም" የትነበርሽ ንጉሤ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተሰራጨ አንድ ቪዲዮም የፌስቲቫሉ ታዳሚዎች ሲሯሯጡ ታይቷል። "ምን እየተካሄደ ነው? እንዴት የምግብ ፌስቲቫል ላይ ሰው ይተኩሳል?" የምትልም ሴት ድምፅ በቪዲዮው ላይ ተሰምቷል። •ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ይባላል? የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰዎች እንዲጠነቀቁ በትዊተር ገፃቸው መልእክት አስተላልፈዋል። የግሎሪ ከተማ አስተዳደር ዲዮን ብራኮ ለአሜሪካ ሚዲያ እንዳሳወቁት ሶስቱ ግለሰቦች መሞታቸውን ነው። አስራ አንዱ ግለሰቦች ደግሞ በአስጊ ሁኔታ ላይ መሆናቸውንና በህክምናም ላይ እንደሚገኙ የሳንታ ክላራ የጤና ማዕከል ቃለ አቀባይ አስታውቀዋል።
news-46601685
https://www.bbc.com/amharic/news-46601685
በየመን ተኩስ አቁም ተግባራዊ በሆነ በደቂቃዎች ውስጥ ተጣሰ
በየመን ጦርነት ወሳኝ የእርዳታ መስመር በሆነችው ሁደይዳህ ከተማ በሃውቲ አማፅያንና በመንግስት ደጋፊ ሃይሎች መካከል የተደረገውተኩስ የማቆም ስምምነት ተፈፃሚ በሆነ በደቂቃዎች ውስጥ ተጣሰ።
የሃውቲ አማፅያንና የመንግስት ደጋፊ ሃይሎች ተኩስ አቁሙን በመጣስ እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ ነው ሁለቱ የየመን ተዋጊ ሃይሎች የተኩስ አቁም ስምምነቱን ያደረጉት በተባበሩት መንግስታት አስተባባሪነት ባለፈው ሳምንት ስዊድን ውስጥ ነበር። ስምምነቱ ከሞላ ጎደል አራት ዓመታት ላስቆጠረው የየመን የእርስ በርስ ጦርነት መፍትሄ ለማበጀት ጅማሮ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት ነበር። ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት በሁደይዳህ አማፅያኑ በመንግስት ደጋፊዎች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል። • ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ በቅዳሜው ውይይት ላይ ምን አሉ? የመንግስት ደጋፊ ሃይሎችም ሁለቱ ሃይሎች እየተታኮሱ እንደሆነ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ገልፀዋል። ሁደይዳህ ከየመን መዲና ሰንዓ 140 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ አራተኛ ትልቅ የአገሪቱ ከተማ ነች። ከተማዋ የአገሪቱ ኢኮኖሚ እምብርት ስትሆን እንደ አውሮፓውያኑ በ2014 ማብቂያ ላይ በሁቲ አማፅያን እጅ ወድቃለች። ላለፉት ስድስት ወራት በሳውዲ አረቢያና አጋሮቿ ጥምረት የሚደገፈው የየመን መንግስት እዚህች ከተማ ላይ ጥቃት ሰንዝሯል። ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የየመን ህዝብ ህይወት በዚህች የወደብ ከተማ በሚገባ የምግብ፣ የመድሃኒትና የነዳጅ አቅርቦት ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ይነገራል። በአሁኑ ወቅት 22 ሚሊዮን የሚሆኑ የመናዊያን የምግብ እርዳታ ሲያስፈልጋቸው ስምንት ሚሊዮን የሚሆኑ ደግሞ ለወዲያው የሚሆን ምግብ እንኳ የሌላቸው እንደሆኑ ተገልጿል። • ሀና እና ጓደኞቿ የሰሩት የእናቶች ምጥ መቆጣጠሪያ
news-54883967
https://www.bbc.com/amharic/news-54883967
በሞዛምቢክ ከ50 በላይ ሰዎች በጽንፈኞች 'አንገታቸው ተቀላ'
በሞዛምቢክ ጽንፈኛ ኢስላማዊ ታጣቂዎች በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ከ50 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን 'አንገት መቅላታቸውን' የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ።
ታጣቂዎቹ በአንዲት መንደር የሚገኝ የእግር ኳስ ሜዳ ውስጥ ሰዎቹን የገደሉ ሲሆን ሟቾቹ እጅግ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን የሚጠቁሙ ሌሎች ሪፖርቶችም እየወጡ ይገኛሉ። በሌላ መንደር ደግሞ በተመሳሳይ የበርካታ ሰዎች አንገት እንደተቀላ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በሞዛምቢክ ከፍተኛ የነዳጅ ሀብት በሚገኝባት ካቦ ዴልጋዶ ግዛት ታጣቂዎች ይህን መሰል ጥቃት ሲፈጽሙ የመጀመሪያቸው አይደለም። በአካባቢው እንዲህ አይነት ጥቃቶች መፈጸም የጀመሩት በአውሮፓውያኑ 2017 ላይ ነበር። አብዛኛዎቹ ነዋሪዎቿ የእስልምና እምነት ተከታይ በሆኑባት በዚች ግዛት እየተካሄደ ባሉ ግችቶች መክንያት እስካሁን እስከ 2 ሺ የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን 430ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገድደዋል። ግድያውን የፈጸመውና ከኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት የታጣቂ ቡድን በደቡባ አፍሪካዊቷ አገር ሞዛምቢክ አካባቢዎችን ለመቆጣጠር እየሞከረ ይገኛል። በአገሪቱ የተንሰራፋውን ድህነትና ስራ አጥነት በመጠቀም በርካታ ወጣቶችን እየመለመለ ሲሆን በአካባቢው ኢስላማዊ አስተዳደር ለመመመስረት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በርካታ ነዋሪዎችም ከአካባቢው ከሚወጣው ነዳጅ ሃብት እምብዛም ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ቅሬታቸውን ይገልጻሉ። ናንጃባ በምትባለው መንደር ታጣቂዎቹ ተኩስ በመክፈትና መኖሪያ ቤቶችን በማቃጠል ነዋሪዎቹን ማሸበር እንደጀመሩ ከመንግስት ጋር ግንኙነት ያለው የዜና አውታር አንድ ከጥቃቱ የተረፈ ሰውን ጠቅሶ ዘግቧል። አክሎም ታጣቂዎቹ የሁለት ሰዎችን አንገት ከቀሉ በኋላ በርካታ ሴቶችን አግተው እንደወሰዱ ዘግቧል። ሌላ ታጣቂ ቡድን ደግሞ ሙቲዴ በምትባል መንደር ከ50 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን እንደቀላ ጠቅሷል። ታጣቂዎቹ ሲመጡ ለማምለጥ የሞከሩ ነዋሪዎች በአካባቢው በሚገኝ የእግር ኳስ ሜዳ ውስጥ እንዲገቡ ተደርገው አንገታቸው እየተቀላ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን 'ፒናክል' የተባለ የግል የዜና ወኪል ዘግቧል። የሞዛምቢክ መንግስት ወታደሮቹ ታጣቂዎችን ለመዋጋት ልዩ የሆነ ስልጠና እንደሚያስፈልጋቸው በመግለጽ የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን እርዳታ ጠይቋል።
news-53563619
https://www.bbc.com/amharic/news-53563619
ሪፐብሊካኖች ለኮቪድ ማገገምያ አንድ ትሪሊዮን ዶላር መደቡ
ሪፐብሊካኖች ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ክፉኛ የተሸመደመደውን ምጣኔ ሀብት ለማነቃቃት አንድ ትሪሊዮን ዶላር እንዲለቀቅ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡
እቅዱ ካካተታቸው መሀል መቶ ቢሊዮን ዶላሩ ለትምህርት ቤቶች ድጎማ፣ እንዲሁም ለብዙ አሜሪካዊያን 1,200 ዶላር ክፍያ መስጠትን ይጨምራል፡፡ ይህ እቅድ ተግባራዊ ከሆነ ለሥራ አጦች ይከፈል የነበረውን 600 ዶላር ይተካል ተብሏል፡፡ ይህ የገንዘብ መጠን ገና ከዲሞክራቶች ጋር ክርክር ከተደረገበት በኋላ የሚጸድቅ ሲሆን ዲሞክራቶች ግን እቅዱን ገና ከወዲሁ እየተቹት ነው፡፡ 'አንድ ትሪሊዮን ዶላር ምን አላት'፣ ሲሉ የገንዘቡን መጠን ማነስ አብጠልጥለዋል ዲሞክራቶች፡፡ አሜሪካ እስከዛሬ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ እስካሁን 2.4 ትሪሊዮን ዶላር ማገገምያ ገንዘብ አውጥታለች፡፡ ከዚህ ውስጥ አብዛኛው የዋለው አሜሪካዊያን ቤተሰቦችን ለመደጎምና ቢዝነሶችን ለማነቃቃት ነበር፡፡ የምጣኔ ሀብት ተንታኞች ግን ገንዘቡ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም እያሉ ነው፡፡ ይህ አዲሱ የሪፐብሊካን ምክረ ሐሳብ ለሥራ አጥ አሜሪካዊያን ይሰጥ የነበረውን ሳምንታዊ የ600 ዶላር ድጎማ ወደ 200 ዶላር ዝቅ የሚያደርግ ሲሆን ይህ ግን የሚቆየው ሌላ ውጤታማና የዜጎችን 70 ከመቶ ገቢ የሚደጉም አዲስ መርሀግብር እስኪጀመር ብቻ ነው፡፡ አዲሱ ምክረ ሐሳብ ለሥራ አጥ አሜሪካዊያን ይሰጥ የነበረውን የገንዘብ መጠን ለመቀነስ ያለመው በርካታ ዜጎች በድጎማው የሚያገኙት የገንዘብ መጠን ሥራ ሠርተው ከሚያገኙት የተሻለ ስለሆነ ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዳይመለሱ አድርጓቸዋል በሚል ነው፡፡ ሴናተር ሚች መክኔል ‹ሪፐብሊካኖች በዚህ ሳምንት ቀነ ገደቡ የሚያበቃውን የሥራ አጥ ዜጎችን የገንዘብ ድጎማ ማርሀ ግብር መቀጠል ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ከዚህ በኋላ ይህን ስናደርግ ሕዝቡ ወደ ሥራ እንዲመለስ በሚያበረታታ መልኩ መሆን እንዳለበት አምነናል› ብለዋል፡፡ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት የዲሞክራቶች ተጠሪ ሴናተር ሹመር የሪፐብሊካኑን ምክረ ሐሳብ፣ ‹በጣም የዘገየና በጣም ትንሽ› ሲሉ አጣጥለውታል፡፡ አሜሪካ ካለፈው የካቲት ጀምሮ 15 ሚሊዮን ዜጎች ሥራ አጥ ሆነውባታል፡፡ በዚህም የተነሳ ከአምስት አሜሪካዊያን አንዱ የሥራ አጥነት ድጎማ ገንዘብ እየወሰደ ይገኛል፡፡ ‹ይህ እጅግ አደገኛ ቀውስ ነው፤ ጊዜ እየቀደመን ነው፤ እርምጃ መውሰድ አለብን› ብለዋል ሴናተር ሹመር፡፡ ‹የሪፐብሊካኑ አዲስ እቅድ ዜጎች ያገኙት የነበረውን ድጎማ በ30 እጅ የሚቀንስ ነው፤ በዚህ ዜጎች ወደ ሥራ ለመመለስ በማይችሉበት ሁኔታ ድጎማን መቀነስ ስሜት አይሰጥም› ብለዋል፡፡ ዲሞክራቶች በበኩላቸው ያቀረቡት ምክረ ሐሳብ አሜሪካ 3 ትሪሊዮን ዶላር የኮቪድ ማገገምያ ገንዘብ እንድታዘጋጅ ይጠይቃል፡፡ ይህም ገንዘብ በዋናነት የግዛት አስተዳደሮችን ለመደጎም የሚውል ነው፡፡ የአሜሪካ ብዙ ግዛቶች በኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ምክንያት የበጀት ቀውስ ገጥሟቸዋል፡፡
news-53831243
https://www.bbc.com/amharic/news-53831243
የአሜሪካ ምርጫ፡ ጆ ባይደን ዶናልድ ትራምፕን እንዲገዳደሩ በይፋ ተመረጡ
የቀድሞው የባራክ ኦባማ ምክትል ጆ ባይደን በይፋ የዲሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ሆነው ተመረጡ፡፡
ምርጫው የተካሄደው በፓርቲው ታላቅ ጉባኤ ነው፡፡ በአሜሪካ የፓርቲዎች አሰራር ባሕል እጩው ቀደም ብሎ ቢታወቅም ይፋዊ ውክልና የሚሰጠው በጠቅላላ ጉባኤ ነው፡፡ በዚህ የማጠቃለያ ጉባኤ ላይ ሥመ ጥር ሰዎች፣ የፓርቲ መሪዎች፣ የቀድሞ የአገር ግዛት አስተዳዳሪዎችና ሌሎች ተገኝተዋል፡፡ በጉባኤው ላይ ትልቅ ቦታ የተሰጣቸው ሁለቱ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች መገኘታቸው ነው፡፡ ቢል ክሊንተንና ጂሚ ካርተር እንዲሁም የቀደውሞ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮሊን ፖል ጉባኤውን አድምቀውታል፡፡ ኮሊን ፖል ሪፐብሊካን ቢሆኑም በዶናልድ ትራምፕ ደስተኛ ባለመሆናቸው ለጆ ባይደን ድጋፋቸውን ሰጥተዋል፡፡ ቢል ክሊንተን በጉባኤው እንደተናገሩት ‹‹ዶናልድ ትራምፕ ታላቋን አሜሪካንን ቀውስ ውስጥ ከቷታል››፡፡ በኅዳሩ ምርጫ ከሕዝብ የተሰበሰበ ቅድመ አስተያየት ትንበያ (opinion polls) ጆ ባይደን ትራምፕን በትንሽ ልዩነት መምራት ጀምረዋል፡፡ በ50ዎቹም ግዛቶች የሚገኙ የፓርቲ ወኪሎች (ዴሊገትስ) በሰጡት ድምጽ መሰረት ነው ጆ ባይደን በይፋ የትራምፕ ቀጣይ ተገዳዳሪ ሆነው የተመረጡት፡፡ ጆ ባይደን በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ በትንሹ ለ30 ዓመታት ቆይተዋል፡፡ ነጩ ቤተ መንግሥት ለመግባት ሲፎካከሩም ይህ ለ3ኛ ጊዜ ነው፡፡ የ77 ዓመቱ ባይደን በዲሞክራቲክ ምርጫ መጀመርያ ላይ በሳንደርሰን ተበልጠው ስለነበር ተስፋ እንደሌላቸው ታስቦ ነበር፡፡ ኋላ ላይ ማርሽ ቀይረው ለዚህ በቅተዋል፡፡ ይህ የፓርቲ ታላቁ ጉባኤን ልዩ የሚያደርገው በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በቪዲዮ ስብሰባ መደረጉ ነው፡፡ በጉባኤው ላይ የአምስት ደቂቃ ንግግር ያደረጉት ቢል ክሊንተን ትራምፕን ክፉኛ ተችተዋቸዋል፡፡ ቢል ንግግራቸውን ያደረጉት ኒውዮርክ ከሚገኘው ቤታቸው ሆነው ነው፡፡ ሪፐብሊካኑ ፖል በበኩላቸው ዶናልድ ትረምፕ ቀጣፊ መሪ ናቸው ሲሉ ለጆ ባይደን ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡ ኮሊን ፖል በጆርጅ ቡሽ ጊዜ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡ የሟቹ የሴናተር ጆን ማኬይን ባለቤት የነበሩት ሲንዲ ማኬይን ለጆ ባይደን ድጋፍ ንግግር አድርገዋል፡፡ ከነዚህ በተጨማሪ የቀድሞው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስር ጆን ኬሪ፣ የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት ተወዳጇ ሚሼል ኦባማ የድጋፍ ንግግሮችን አሰምተዋል፡፡ የዲሞክራቶች ታላቅ ጉባኤ ዛሬና ነገም ይቀጥላል፡፡ ካሚላ ሐሪስ፣ ሂላሪ ክሊንተንና ባራክ ኦባማ የሚያደርጓቸው ንግግሮች በጉጉት ይጠበቃሉ፡፡
news-54884202
https://www.bbc.com/amharic/news-54884202
የኮሮናቫይረስ ክትባት መገኘት ተስፋ የዓለም ገበያን እያነቃቃው ነው
ኮቪድ-19ን ለመከላከል ይረዳሉ የተባሉ ክትባቶች ወደመጨረሻ ደረጃቸው ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ የዓለም ገበያ እንደ አዲስ እየተነቃቃ መሆኑ ተዘግቧል።
ፋይዘር የተባለው መድሀኒት አምራች ኩባንያ ኮሮናቫይረስን የመከላከል አቅሙ 90 በመቶ ነው ያለውን ክትባት ይፋ ካደረገ በኋላ የድርጅቱ ድርሻ በዓለም ገበያ በ9 መቶ ከፍ ማለቱ ተስተውሏል። በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊው ጆ ባይደን መሆናቸው ከተነገረ ወዲህ መነቃቃት እያሳየ የነበረው ዓለም ገበያ አሁን ደግሞ ክትባቱን ተከትሎ ሌላ እሽቅድድምን ፈጥሯል። የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአክስዮን ገበያ ከአውሮፓውያኑ የ2008 የዓለም የገንዘብ ቀውስ ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ መቀነሱ የሚታወስ ነው። በሞዛምቢክ ከ50 በላይ ሰዎች በጽንፈኞች 'አንገታቸው ተቀላ' አርሜኒያ "እጅግ በጣም የሚያም" ያለችውን የሰላም ስምምነት ከአዘርባጃን ጋር ለመፈረም ተገደደች 90 በመቶ ውጤታማ ነው የተባለ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ተሰራ በአሜሪካ የሚገኙ ድርጅቶች የአክሲዮን ዋጋቸው ከ1.1 በመቶ እስከ 5.6 በመቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍ ያለ ሲሆን በእሲያና አውሮፓ የሚገኙ ድርጅቶችም ድርሻቸው በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ አሳይቷል። ክትባቱን ይፋ ያደረጉት ፋይዘርና ባዮኤንቴክ ክትባቱን በሶስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል። በቁጥር የበዙ ክትባቶች የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን ይህ ክትባት ተስፋ ከተጣለባቸው ውስጥ ቀዳሚው ነው። ከዚህ ቀደም የተደረገው ሙከራ ክትባቱ ሰውነታችን ከበሽታው ጋር እንዲለማመድና አንቲቦዲዎችን እንዲያዳብር መርዳቱ የተስተዋለ ሲሆን ሌላው ደግሞ ቲ-ሴል በመባል የሚታወቀው የመከላከል አቅምን የኮሮናቫይረስን መዋጋት እንዲችል አድርጎታል ተብሏል። በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኘው 'ኤፍቲኤስኢ 100' የወረርሽኙ ዜና ከተሰማበት መጋቢት ወር ጀምሮ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በዓለም አቀፍ ገበያ ድርሻው ላይ የ82 ቢሊየን ፓውንድ ጭማሪ አግኝቷል። የተለያዩ መድሃኒት አምራች ኩባንያዎች እየሞከሯቸው ባሉት የክትባት ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያገኙ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ መግለጻቸውን ተከትሎ የዓለም አቀፍ ገበያው ከዚህም በበለጠ ሊያድግ እንደሚችል ተጠቁሟል።
news-51368388
https://www.bbc.com/amharic/news-51368388
ተስፋ የተጣለበት የኤችአይቪ ክትባት ሳይሳካ ቀረ
የኤድስ በሽታን የሚያስከትለውን የኤችአይቪ ቫይረስን መከላከያ ይሆናል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የሙከራ ክትባት ሳይሳካ መቅረቱ ተነገረ።
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከአምስት ሺህ በሚልቁ ሰዎች ላይ የክትባቱን ሙከራ ሲያደርግ የነበረው ብሔራዊ የጤና ተቋም እንዳለው ክትባቱ ኤችአይቪን መከላከል እንዳልቻለ ስለደረሰበት ሙከራው እንዲቆም አድርጓል። በሥራው ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች በተገኘው ውጤት "በጣም ማዘናቸውን" ገልጸው፤ ነገር ግን ኤችአይቪን የሚከላከል ክትባት የማፈላለጉ ጥናት ግን መቀጠል አለበት ብለዋል። • ክትባት ከየት ተነስቶ የት ደረሰ? • ኢትዮጵያ የካንሰር መከላከያ ክትባት ከሚሰጡ ጥቂት አገራት አንዷ ናት ክትባቱ ታይላንድ ውስጥ በተደረገ ሙከራ ሰዎችን ከበሽታው ለመከላከል የሚያስችል አቅምን ይፈጥራል ተብለው ከታሰቡት የክትባት አይነቶች መካከል አንዱ ነበር። በዓለም ላይ በርካታ የተለያዩ አይነት የኤችአይቪ ዝርያዎች ያሉ ሲሆን ይህ ክትባት በተለይ ኤችአይቪ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ካለባቸው አገሮች አንዷ በሆነችው በደቡብ አፍሪካ ውስጥ በስፋት ለሚገኘው የቫይረሱ ዝርያ ታስቦ የተዘጋጀ ነበር። ክትባቱ በሙከራ ላይ ሳለ እንደታሰበው በመስራት በሌሎች የዓለም አካባቢ ላሉት የቫይረሱ አይነቶች የሚሆኑ ክትባቶችን ለማዘጋጀት ያግዛል ተብሎ ከፍ ያለ ተስፋ ተጥሎበት ነበር። • ኢትዮጵያዊያን ለክትባቶች ከፍተኛ የሆነ አውንታዊ አመለካከት አላቸው • ባልተጨበጡ የሤራ ትንተና ፅንሰ-ሐሳቦች ያምናሉ? ለክትባቱ ሙከራ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ተዘጋጅተው ለተወሰኑት ለበሽታው ይሆናል የተባለው ክትባትና ለሌሎቹ ደግሞ ምንም ሳይሰጣቸው ሙከራ ተደረገ። በተገኘው ውጤት ግን ክትባቱ ከተሰጣቸው መካከል 129ኙ በሽታው ሲገኝባቸው፤ ካልተሰጣቸው ውስጥ ደግሞ 123ቱ በበሽታው ተይዘዋል። ይህ የተገኘው ውጤት በምርምሩ ላይ የተሰማሩትን ባለሙያዎች ተስፋ አስቆርጧል። ነገር ግን በሽታውን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት ለማግኘት የሚደረገው ጥረት መቀጠል እንዳለበት ያምናሉ። ከዚህ ቀደም በበሽታው ከመያዝ የሚከላከል ውጤታማ የሆነ ህክምና ያለ ሲሆን ነገር ግን ከክትባት በተለየ መድሃኒቱን በመደበኝነት በየቀኑ መወሰድን ያስፈልጋል። ከዚህ በተለየ በሽታውን ለመከላከል እንደዋነኛ ዘዴ የሚመከረው በተገቢው ሁኔታ ኮንዶም መጠቀም ወይም ከግብረ ሥጋ ግንኙነት መታቀብ ነው። በበሽታው ለተያዙ ሰዎች ተመራማሪዎች ያዘጋጇቸው ፈር ቀዳጅ የጸረ ኤችአይቪ ህክምና መድሃኒቶች ቫይረሱ በደማቸው ያሉ ሰዎችን ጤንነትና በህይወት የመቆየት ዕድልን በከፍተኛ ደረጃ አሻሽሏል። ከኤችአይቪ አንጻር በሽታውን ለመከላከልና ለማከም የተለያዩ አማራጮች ቢኖሩም አሁንም ሰዎች በቫይረሱ እንዳይያዙ የሚያደርግ የመከላከያ ክትባት ማግኘት ወሳኝ ነገር መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ።
48508662
https://www.bbc.com/amharic/48508662
ጄይ-ዚ፡ የመጀመሪያው ቢሊየነር 'ራፐር' ሆኗል
ፎርብስ የተሰኘው መፅሄት እንደገለጠው ጄይ-ዚ ሙዚቃን ጨምሮ፣ ፋሽን እና ሌሎች ኢንቨስትመንቶቨች ላይ ያፈሰሰው ንዋይ ቱጃር አድርጎታል።
ዓለም ላይ ካሉ ራፐሮች ልቆ ቢሊየነር መሆን የቻለው የቢዮንሴ ባል ጄይ-ዚ ከሙዚቃ ብቻ ያካበተው ሃብት ቀላል የሚባል አይደለም። ሾን ካርተር በተሰኘ የመዝገብ ስሙ የሚታወቀው ጄይ-ዚ፤ ኒው ዮርክ ግዛት ውስጥ የሚገኝ ኑሮ የከበደበት ሥፍራ ነው ተወልዶ ያደገው። • አውታር - አዲስ የሙዚቃ መሸጫ አማራጭ 1996 ላይ ባወጣው የመጀመሪያ ዓልበሙ እውቅና ማትረፍ የቻለው ካርተር፤ 2001 ላይ የለቀቀው 'ብሉፕሪንት' የተሰኘ ዓልበሙ ባሕላዊ፣ ታሪካዊ እና ጥበባዊ ዳራው የላቀ ሆኖ በመገኘቱ ሙዚዬም ሊገባለት ችሏል። እጀ-ረዥሙ ጄይ-ዚ ከኮኛክ እስከ ኡበር ባለ ኢንቨስተመንቶች ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል። • የ'ምን ልታዘዝ' ድራማ ሰምና ወርቅ ባለቤቱ ቢዮንሴ በበኩሏ 335 ሚሊዮን ዶላር በማካበት አሉ ከሚባሉ እንስት ሙዚቀኞች አናት ላይ መቀመጥ ችላለች። ይህ ማለት የጥንዶቹ የሃብት መጠን ሲጠቃለል ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኖ ቁጭ። 2014 ላይ ሌላኛው ጥቁር የሙዚቃ ሰው ዶር ድሬ ቢሊየነር ሆኗል ተብሎ ቢነገርም ፎርብስ ግን የግለሰቡ ሃብት 770 ሚሊየን እንጂ ቢሊዮን አልገባም ሲል አጣጥሏል። ጄይ-ዚን በ40 ዓመት የሚበልጡት ሌላኛው ቢሊየነር ዋረን በፌት አንድ ጊዜ «እኔ ከጀይ-ዚ ብዙ ልማር የሚገባኝ ነኝ፤ ይህ ወጣት ሰው ገና ብዙ ቦታ ይደርሳል» ሲሉ ተናግረው ነበር። • ሙዚቃ ሳይሰሙ መወዛዋዝ ይችላሉ?
news-50001895
https://www.bbc.com/amharic/news-50001895
ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ምን አጋጠመው?
ታዋቂው የኦሮምኛ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ ጎዳና ላይ በመኪና እየተከተሉ ሲሰድቡኝ ነበር ካላቸው ሰዎች ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብቶ እንደነበር ተናገረ።
ሃጫሉ ማንነታቸው ካልታወቁ ሰዎች ጋር ሲነጋገርና ሌሎች ሰዎች ደግሞ ለመገላገል ሲጥሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በማሕበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ በስፋት ሲዘዋወር ቆይቷል። ነገሩ የተከሰተው ሜክሲኮ አካባቢ በተለምዶው ኮሜርስ የተባለው ስፍራ ላይ እንደሆነ በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ ይታያል። አንዳንዶች ድምጻዊው ጥቃት እንደተፈጸመበት ቢናገሩም በቪዲዮው ላይ እንደሚታየውና እርሱም እንደሚናገረው "ስሜታዊ ከሚያደርጉ" የቃላት ልውውጥ በስተቀር ጉዳት የሚያስከትል ጸብ አልነበረም። • ከነፍስ የተጠለሉ የዘሪቱ ከበደ ዜማዎች • የኤልያስ መልካ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሰኞ ይፈፀማል ክስተቱን በሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ድምጻዊው ከመኪናው ወርዶ በሚናገርበት ጊዜ ሌሎች ሰዎች ለመገላገል ሲሞክሩና ሌሎች ሰዎችም በስፍራው ሲሰበሰቡ ይታያል። በተጨማሪም መኪናው የቆመው ሌሎች ተሽከርካሪዎች በሚያልፉበት ቦታ ላይ በመሆኑ መንገድ የተዘጋባቸው መኪኖች የጡሩምባ ድምጽ ይሰማል። በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ሃጫሉን ወደመኪናው እንዲሄድ ሲያግባቡት በንዴት "ዐብይ ላይ ነው . . . " በማለት በቁጣ ስሜት ሲናገር ይደመጣል። ድምጻዊው እንደሚለው ድርጊቱ ያጋጠመው ማክሰኞ ዕለት ሲሆን ከአፍሪካ ኅብረት ጽህፈት ቤት ጀምረው ግለሰቦቹ እየተከታተሉ እስከሜክሲኮ ድረስ ሲሰድቡት እንደነበረ ገልጿል። ለቢቢሲ ሲናገር "እኔ ሰውን አከብራለሁ ነገር ግን እንዲህ መብቴን የሚጥስ ነገር ሲገጥመኝ ከማንም ፈቃድ አልጠይቅም" በማለት የሰዎቹ ድርጊት እንዳስቆጣው ጠቅሷል። ግለሰቦቹ ይሰንዝሯቸው የነበሩት ቃላት ስሜት ውስጥ የሚያስገቡ ስለነበሩ ሜክሲኮ አካባቢ መኪናውን አቁሞ ሲከተሉኝ ነበር ያላቸው አራት ሰዎች ወደነበሩበት ሊያናግራቸው መሄዱንና ሰዎች መሰብሰባቸውን ይናገራል። • ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ • ከድምፃዊት ቤቲ ጂ እና ቸሊና ጀርባ "የሰዎቹን ንግግር በዝምታ ማለፍ አስቸጋሪ ነበር" የሚለው ሃጫሉ "ፍላጎታቸው በሚሰነዝሯቸው ቃላት ስሜታዊ በማድረግ አምባ ጓሮ ለመፍጠር ነበር" ይላል። ድምጻዊው ሃጫሉ እንደሚለው እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ እንደተደጋገመበትና በዚህ ወር ውስጥ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑንም ተናግሯል። እንዲህ አይነቱን ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች ላይ መንግሥት ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ ሥርዓት አልበኝነትን ለማስቆም የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት ብሏል። ጎዳና ላይ ከተከሰተው ከዚህ ውዝግብ በኋላ ፖሊስ ከስፍራው በመድረስ እንደገላገላቸውና ለገሐር አካባቢ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ሄደው ግለሰቦቹ ጥፋተኛ መሆናቸውን አምነው ተለቅቀዋል ሲል ይናገራል። ግለሰቦቹ ይሰነዝሩት የነበሩት ቃላት ከጥላቻ የመነጩና ስሜታዊ ያደርጉ እንደነበር ሃጫሉ ቢናገርም ከግለሰቦቹ ጋር ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከሄዱ በኋላ ነገሩ በቀላሉ ማብቃቱን ገልጿል። በክስተቱ ወቅት እርሱም መንገድ በመዝጋቱ ይቅርታ መጠየቁንና ተገቢ ያልሆኑ ቃላት ሰንዝረዋል የተባሉት ግለሰቦችም ይቅርታ እንደጠየቁ ሃጨዓሉ ለቢቢሲ አስረድቷል።
news-52393705
https://www.bbc.com/amharic/news-52393705
ኮሮናቫይረስንና የፀሐይ ብርሃንን ምን አገናኛቸው?
እንግሊዝን ጨምሮ ሌሎች ሃገራት በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተጣለውን የእንቅሳቃሴ ገደብ ተከትሎ ዜጎቻቸው ቫይታሚን ዲ እንዲወስዱ እየመከሩ ነው።
ለወትሮው ብዙዎቻችን የማይከፈልበት ቫይታሚን ዲ ከፀሐይ እናገኛለን። ከፀሐይ የሚገኝው ቫይታሚን ዲ ከሌሎች የቫይታሚን ዓይነቶች ጋር ተዳምሮ ሰውነታችን እንዲነቃቃና በሽታን ወግድ እንዲል ይረዳል። የቫይታሚን ዲ ጥቅም የሚገባን ወረርሽኝ ሲመጣ ነው ይላሉ የዘርፉ ሰዎች። ዩናይት ኪንግደም ውስጥ ያሉ ሰዎች ቢያንስ በቀን 10 ማይክሮግራም ቫይታሚን ያለበት ኃይል ሰጭ እንዲወስዱ ይመከራሉ። በተለይ ደግሞ እያደገደገ ያለውን የክረምት ወቅት ተከትሎ ሰዎች ከቤታቸው መውጣት ካልቻሉ በሚል ነው ይህ ምክር የተለገሳቸው። ለመሆኑ እነማን ናቸው ቫይታሚን ዲ እንዲወስዱ በፅኑ የሚመከሩት? ጥቁር ቆዳ ያላቸው ሰዎች በቂ የሆነ የፀሐይ መጠን ካላገኙ ቫይታሚን ዲ ላያመርት ይችላል። ምክንያቱም ቆዳቸው በባሕሪው ከፀሐይ የሚገኝ ቫይታሚንን በቀላሉ መቀበል ስለማይችል። ብሪቲሽ ኒውቲሪሽን ፋውንዴሽን ለተሰኘ ድርጅት የምትሠራው ሳራ ስታነር 'አለመታደል ሆኖ የኮሮናቫይረስ አሉታዊ ተፅዕኖ ከእኛ ጋር ይቆያል። ይህ ማለት ደግሞ ውጭ የምንወጣበት ጊዜ ትንሽ ነው። ቤታችን መቀመጣችን ለእኛው ጥቅም ነው። ስለዚህ ከፀሐይ የምናገኝ የነበረውን ቫይታሚን በሌላ መተካት ይኖርብናል' ይላሉ። ቫይታሚን ዲ ወሰድኩ አልወሰድኩ. . . ? ቫይታሚን ዲ ለጤናማ አጥንት ወሳኝ ነው፤ ለጥርስና ጡንቻም እንዲህ። የቫይታሚን ዲ እጥረት በተለይ ሕፃናት ላይ የአጥንት መጣመም ሊያስከትል ይችላል፤ ይህ ደግሞ ውሎ አድሮ በአዋቂነት ዘመንም ጉዳት ይኖረዋል። አንዳንድ ጥናቶች ቫይታሚን ዲ ለጉንፋን በሽታዎች ያለንን ተጋላጭነት ይቀንሳል ይላሉ። ቢሆንም ቫይታሚን ዲ የመከላከል አቅምን ይጨምር አይጨምር ማስረገጫ አልተገኘም። በብዛት ብወስድስ? አይመከርም። ኃኪም ካዘዘው በላይ መውሰድ በጊዜ ሂደት ጉዳት ሊያመጣ ይችላል። ለሕፃናት በቀን ከ50 ማይክሮግራም በላይ አይመከርም። ከ12 ወራት በታች ያሉ ጨቅላዎች ከ25 ማይክሮግራም በላይ መውሰድ የለባቸውም። አዋቂዎች ደግሞ ከ100 ማይክሮግራም በላይ እንዳይወስዱ ይመከራል። ከተጠቀሱት በላይ መውሰድ የሚቻለው በኃኪም ትዕዛዝ ብቻ ነው። ኮሮናቫይረስን ይከላከላል? አይከላከልም። ቫይታሚን ዲ መውሰድ ከኮሮና ይታደግ አይታደግ የሚያረጋግጥ ምንም ዓይነት ሳይንሳዊ ጥናት የለም። ነገር ግን የጤና ባለሙያዎች ቫይታሚን ዲ እንዲህ ያለ ወረርሽኝ ሲከሰት ጠቀሜታው የጎላ ነው ይላሉ። ቫይታሚን ዲ አቅማቸው የደከመ ሰዎችን በእጅጉ ያግዛል። የስፔንና ፈረንሳይ ተመራማሪዎች ቫይታሚን ለኮሮናቫይረስ በሽተኞች ጥቅም ይኖረው እንደሆን ለማጣራት ምርምር ላይ ናቸው። ከየት መግዛት እችላለሁ? ቫይታሚን ዲ ገበያዎች ውስጥ እንዲሁም የፋርማሲ ሸልፍ ላይ በቀላሉ ሊገኝ ይችላል። እንዲሁ ቫይታሚን ዲ ተብለው ሊሸጡ ይችላሉ። ከሌሎች መድኃኒቶች ጋር ተቀይጠው ጥቅም ላይ ሊውሉም ይችላሉ። ለሕፃናት ደግሞ በጠብታ መልክ ይቀርባሉ። በምግብ ውስጥ ሊገኝ አይችልም? ከምግብ ብቻ ቫይታሚን ዲ ማግኘት ከባድ ነው። ምንም እንኳ የተመጣጠነ መግብ መብላት ቢመከርም ከምግብ ከተወሰነው በላይ ንጥረ-ነገር ማግኘት አይቻልም። ቫይታሚን ዲ ከዓሣ ዓይነቶች ከእንቁላል ሊገኝ ይችላል። አንዳንድ የቁርስ ሲሪያሎች፣ ማርገሪን እና እርጎ ቫይታሚን ዲ ይገኝባቸዋል።
51186657
https://www.bbc.com/amharic/51186657
ርዕደ መሬት፡ እውን አዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር?
ሰኞ ጥር 11/2012 ንጋት አካባቢ መሬት ስትነዘር ሰምተናል ያሉ ሰዎች በማሕበራዊ ድር-አምባዎች ያጋጠማቸውን ሲያጋሩ ነበር።
'አፍሪካ ኢንስቲቲዩት' የተባለ አንድ ገፅም ኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀት ተከስቶ እንደነበር የሚጠቁም አንድ ድረ-ገፅ አያይዞ ትዊተር ላይ ፅፎ ነበር። የ Twitter ይዘት መጨረሻ, 1 እውን አዲስ አበባም ሆነ በኢትዮጵያ ሌሎች ሥፍራዎች የመሬት መንቀጥቀት ተከስቶ ነበር? በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት አታላይ አየለ [ፒኤችዲ] የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪ ናቸው። ተመራማሪው፤ በፉሪ፣ በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር ያሉ ጣቢያዎችን ጨምሮ ከአምስት የተለያዩ ጣቢያዎች በተገኘ መረጃ መሠረት በምሥራቅ ኢትዮጵያ መኢሶ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር አጣርተናል ይላሉ። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተሰማቸው የመኢሶው ንዝረት ነው ሲሉ ያስረዳሉ። «መኢሶ አካባቢ በሪክተር ስኬል 5 የሚገመት የመሬት መንቀጥቀጥ ተፈጥሯል። ይህ የሆነው ዛሬ [ጥር 11/2012] 12 ሰዓት አካባቢ ነው። አዲስ አበባ ውስጥም ቢሆን ሰዎች ሊሰማቸው ይችላል። በተለይ ፎቅ ላይ ያሉ ሰዎች የበለጠ ሊሰማቸው ይችላል። በሪክተር ስኬል 5 ማለት እንግዲህ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል አይደለም፤ ነገር ግን ሰዎች ሊሰሙት ይችላሉ።» በተለይ አዋሽና አሰበ-ተፈሪ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጡ ጎልቶ የተሰማ ሲሆን፤ አዲስ አበባ ደግሞ ለስምጥ ሸለቆ ቅርብ በመሆኗ መሰል ክስተቶች ይሰሟታል። ከዚህ በፊት መሰል የመሬት መንቀጥቀጦች በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች ተከስተው ንዝረቱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ሲያስደነግጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም ይላሉ ባለሙያው። «2009 አንኮበር አካባቢ የተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር። ባልሳሳት 4.7 ሪክተር ስኬል አካባቢ ነበር የተመዘገበው። ታኅሣሥ ውስጥ ነበር። የዛኔም አዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ንዝረቱ ተሰምቶ ነበር።» አሁን በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ምናልባት መሬት ላይ ያሉ ቤቶችን ያፈርስ ይሆናል እንጂ ብዙ ጉዳት አያደርስም ይላሉ። የደረሰ ጉዳት እንዳለ ገና አለማረጋገጣቸውንም ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሚባል የመሬት መንቀጥቀጥ ያስተናገደችው 1953 ላይ ሲሆን ካራቆሬ ተበሎ በሚጠራው አካባቢ የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ በሪክተር ስኬል 6.5 ተመዝግቧል። በወቅቱ በደረሰ አደጋ 30 ሰዎች መሞታቸውም ተዘግቦ ነበር። ምንም እንኳ አንዳንድ አካባቢዎች በታላቁ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ቢገኙም የመሬት መንቀጥቀጥ ኢትዮጵያን ይህን ያህል የሚያሰጋት አይደለም።
news-48325704
https://www.bbc.com/amharic/news-48325704
ለጤንነትና ለአካባቢ ምቹ በመሆን የተመረጡ አምስት ምግቦች
በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች በአብዛኛው የሚመገቡት ከሦስት ሰብሎች የሚዘጋጁ ምግቦችን ነው። እነዚህም ሩዝ፣ በቆሎና ስንዴ ሲሆኑ እነሱም 60 በመቶውን የምድራችን ነዋሪ የሚያስፈልገውን የካሎሪ መጠን የሚያስገኙ ናቸው።
ነገር ግን ከእነዚህ ውስን ሰብሎች ከሚዘጋጁ ምግቦች በቂ ካሎሪ ቢያገኝም ቫይታሚንና ሚነራሎችን በበቂ ሁኔታ ለማግኘት ግን አዳጋች ነው። • ቁርስ የቀኑ እጅግ አስፈላጊ ምግብ ነውን? አንድ አዲስ ጥናት 50 ለጤናና ለተፈጥሮ አካባቢ ተስማሚ ያላቸውን ምግቦች "የመጪው ዘመን ምግቦች" በማለት ይፋ አድርጓል። የትኞቹ ምግቦች ናቸው ቀዳሚ ተብለው በዝርዝሩ ውስጥ የሰፈሩት? ሞሪንጋ (ሽፈራው) ድርቅን የሚቋቋመው ሞሪንጋ (ሽፈራው) የሞሪንጋ ዛፍ በስፋት የሚጠቀሰው "ተአምረኛው ዛፍ" እየተባለ ነው። ዛፉ በቶሎ የሚያድግና ድርቅን የሚቋቋም ሲሆን ምንጩም የእስያ አህጉር ነው። የዛፉ የተለያዩ ክፍሎች ለመድሃኒትነት ጭምር ያገለግላሉ። በቫይታሚን ኤ እና ሲ እንዲሁም በካልሺየምና በፖታሺየም የበለጸገው የዛፉን ቅጠል በዓመት ሰባት ጊዜ መሰብሰብ ይቻላል። ቅጠሉ የተለያዩ ሥጋ ነክ ምግቦችን ለመስራትም ያገለግላል። ፍሬውም ሾርባን በመሳሰሉ ምግቦች ውስጥ ቢጨመር ጤናማ የሆነ ኮሌስትሮል በሰውነታችን ውስጥ እንዲፈጠር ያደርጋል። የሞሪንጋ ቅጠል ተፈጭቶ ከተዘጋጀ ለወጥ፣ ለጭማቂ፣ ለሾርባና ለሻይ ያገለግላል። ዋካሜ (የባህር አረም) ዋካሜ ዓመቱን ሙሉ ሊመረት ይችላል ጃፓኖች ለክፍለ ዘመናት ዋካሜ የተባለውን የባህር ውስጥ አረም እያመረቱ ለምግብነት ሲጠቀሙ ኖረዋል። በተጨማሪም ይህን እጽዋት ለስጦታና ለግብርም ይሰጡ ነበር። ይህ አረም በአሁኑ ወቅት በፈረንሳይ፣ በኒውዚላንድና አርጀንቲና ባህሮች ላይ የሚመረት ሲሆን ያለምንም ማዳበሪያና ጸረ ተባይ ዓመቱን በሙሉ ምርት ይሰጣል። እንዲደርቅ የሚደረገውም በፀሐይ ሙቀት ነው። • የአለም የምግብ ቀን: አስገራሚ የአለማችን ምግቦች የደረቀው የባሕር አረም ጨዋማ ጣዕምን ምግብ ላይ ከመጨመሩ ባሻገር ለጤና ተስማሚ የሆነ ንጥረ ነገርን ለተመጋቢዎች ይሰጣል። ከተለያዩ አይነት የባሕር ውስጥ አረሞች መካከል ለስላሳውና ቡናማው ዋካሜ የተባለው የደም ግፊትን የመቀነስ፣ የደም መርጋትን የመከላከልና ሌሎችም የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ተመስክሮለታል። ይህ የባሕር ውስጥ አረም አዮዲንና ኦሜጋ 3 የተባሉ ንጥረ ነገሮች ዋነኛ ምንጭ ሲሆን በተለይ የእንስሳ ተዋጽኦዎችን ለማይመገቡ ሰዎች ጥቅማቸው የጎላ ነው። ፎኒዮ ጥንታዊው ፎኒዮ አዲሱ ተመራጭ ጥራጥሬ ሆኗል ማሊ ውስጥ የሚገኙት የባምባራ ማኅበረሰብ አባላት እንደሚሉት ይህ ጣፋጭ የምግብ አይነትን ለማዘጋጀት ቀላል ከመሆኑ የተነሳ "የሚያዘጋጀውን ሰው አያሳፍርም" ሲሉ ያሞካሹታል። ፎኒዮ ከ5 ሺህ ዓመታት በፊት ግብጽ ውስጥ ይመረት እንደነበር የሚነገርለት ሲሆን ድርቅን የሚቋቋሙ ጥቁርና ነጭ ዝርያዎች አሉት። ይህ የጥራጥሬ ዘር በምዕራብ አፍሪካ የሳህል አካባቢ ከ60 እስከ 70 ቀናት ውስጥ ይበቅላል። የፎኒዮ ፍሬ የአሸዋን ያህል ጥቃቅን ሲሆኑ ለምግብነት ከመዋሉ በፊት ገለባው መወገድ አለበት። ይህም በእጅ የሚሰራ ሲሆን ሴኔጋል ውስጥ አዲስ ሥራ የጀመረ ማምረቻ ይህንን ግሉትን ከተባለ ንጥረ ነገር ነጻ የሆነውን ምርት ለዓለም ገበያ ለማቅረብ አቅዷል። ፎኒዮ በአይረን፣ በዚንክና ማግኒዢየም የምግብ ንጥረ ነገሮች የዳበረ ሲሆን እንደሩዝ ሊበላ ይችላል። ከዚሁ ሰብል ቢራ ሊጠመቅ ይችላል ተብሏል። ኖፓሊስ ቁልቋል (በለስ) ኖፓሊስ ቁልቋል (በለስ)፣ ዓይነት ሁለት፣ የስኳር ታማሚዎችን ይረዳል። ይህ በሜክሲኳዊያን የተለመደ ምግብ የሆነው ቁልቋል (በለስ)፣ የተለያየ ክፍሉ በተለያየ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ለምግብነት ይውላል። ይህን የቁልቋል አይነት በማዕከላዊና ደቡብ አሜሪካ፣ በአውስትራሊያ እንዲሁም አውሮፓ ውስጥ በቀላሉ ይበቅላል። • ረሃብ የቀሰቀሰው ፈጠራ አንዳንድ ጥናቶች እንዳመለከቱት ከዚህ እጽዋት ውስጥ የሚገኘው አሰር ከሰውነታችን ውስጥ የተጠራቀመን ስብ ለማስወጣት ይረዳል። በተጨማሪም፣ አይነት ሁለት፣ የስኳር ህመም ላለባቸው ሰዎች ስኳር መጠናቸውን ለመቀነስ እንደሚያገለግልም ይነገርለታል። ይህንን የቁልቋል አይነት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመገቡ በአንዳንዶች ላይ ማስቀመጥ፣ ማቅለሽለሽና ባልተለመደ ሁኔታ የሆድ መነፋት ሊያጋጥማቸው ይችላል። ባምባራ (ጣፋጭ ለውዝ) ባምባራ (ጣፋጭ ለውዝ) የፕሮቲን ዋና ምንጭ ነው ባምባራ ብዙ ቅባት የሌለው ሲሆን የጣፋጭ ለውዝ ዓይነት ነው። የባምባራ ፍሬ ለም ባልሆነ አፈር ላይ የሚበቅል በመሆኑና የያዘውን የናይትሮጅን መጠን ወደ መሬት በመልቀቅ መሬቱን ለም የማድረግ ኃይል አለው። በዚህም ምክንያት በዘላቂ የምግብ ዋስትና ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎችን ትኩረት መሳብ ችሏል። በባህላዊ መልኩ በአፍሪካ የሚመረተው ባምባራ በደቡባዊ ታይላንድና በማሌዥያ አንዳንድ አካባቢዎችም ይበቅላል። በመቀቀል፣ በመቁላት፣ በመጥበስና በዳቦ ውስጥ በመጨመር ለምግብነትም ይሰናዳል። በምስራቅ አፍሪካ ሾርባ ለመስራትም ዋና ግብዓት በመሆን ያገለግላል። "የተሟላ ምግብ" በመባልም ይታወቃል። በፕሮቲን የበለፀገ በመሆኑ እንዲሁም የደም ስሮችን እድገት የሚያፋጥነውንና የሰውነትን በሽታ መከላከል አቅም የሚረዳውን -ዚንክ የያዘውን የአሚኖ አሲድ ሜቲኦናይን ምንጭ በመሆኑ፤ የታይሮይድ እጢን ሥራ የሚቆጣጠረውንና ለበሽታ መከላከል የሚረዳውን ሴሌኒየም ንጥረ ነገረ በመያዙ ነው የተሟላ የሚለው ስያሜ የተሰጠው። ባምባራ አትክልትን ብቻ ለሚመገቡ፣ ጥቂት የእንስሳት ተዋፅኦን ለሚመገቡ እንዲሁም እጽዋት ላይ የተመሠረተ የአመጋገብ ሥርዓት ላላቸው ሰዎች ፕሮቲን በመያዙ ወሳኝ ምግብ ነው ። አሁን እያጋጠመ ባለው የምግብ አቅርቦት ችግር ወደፊት የሚኖሩን ምግቦች በቀላሉ የሚመረቱና በቀላሉ የበለፀጉ መሆን እንዳለባቸውም ጥናቱ ይመክራል።
49771010
https://www.bbc.com/amharic/49771010
አሜሪካ ጦሯን ወደ ሳዑዲ ልትልክ ነው
አሜሪካ በሳዑዲ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ወታደሮቿን ልትልክ መሆኑን አስታወቀች።
በጥቃቱ ጉዳት የደረሰበት የሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ ማቀነባበሪያ የመከላከያ ሚኒስቴር ፀሐፊ የሆኑት ማርክ ኤስፐር፤ በሳዑዲ የሚሰማራው ጦር "መከላከል ላይ ያተኮረ" ተልዕኮ ሊሰጠው እንደሚችል ለጋዜጠኞች ጠቁመዋል። ምን ያህል ወታደር እንደሚሰማራ ግን ያሉት ነገር የለም። በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቱ አማፂያን ባለፈው ሳምንት በሳዑዲ ሁለት የነዳጅ ማቀነባበሪያ ላይ ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነቱን እንወስዳለን ብለዋል። ሆኖም አሜሪካም ሆነች ሳዑዲ አረቢያ ለጥቃቱ ተጠያቂ ያደረጉት ኢራንን ነው። • ሳዑዲ፡ ጥቅም ላይ የዋሉት መሣሪዎች ኢራን ተጠያቂ መሆኗን ያረጋግጣሉ • አሜሪካ፡ ''ሳዑዲን ያጠቁት ድሮን እና ሚሳዔሎች መነሻቸው ከኢራን ነው'' • ላሊበላ፡ የመፍትሔ ያለህ የሚለው ብሔራዊ ቅርስ አርብ ዕለት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ወታደራዊ እሰጥ አገባ ውስጥ ላለመግባት በሚል "ከፍተኛ የሆነ" ማዕቀብ ሊጣል እንደሚችል ተናግረው ነበር። አዲሱ ማዕቀብ የሚያነጣጥረው የኢራን ማዕከላዊ ባንክንና ሉዓላዊ የሀብት ፈንድን መሆኑን ትራምፕ ተናግረዋል። ሚስተር ኤስፐር መግለጫ የሰጡት የጥምር ጦሩ የበላይ ኃላፊ ከሆኑት ጄነራል ጆሴፍ ደንፎርድ ጁኒየር ጋር ነው። ሳዑዲ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስን ድጋፍ ጠይቀዋል ብለዋል ሚስተር ኤስፐር። የሚላከው ኃይል የአየርና የሚሳኤል መከላከል አቅምን ከፍ ያደርጋል ተብሎ የታቀደ ሲሆን፤ አሜሪካ ደግሞ ለሁለቱ አገራት "ወታደራዊ ቁሳቁስን ማቅረቡን ታፋጥናለች" ብለዋል። ጄነራል ደንፎርድ የወታደራዊ ስምሪቱን "የተለሳለሰ" ያሉ ሲሆን፤ በሺዎች የሚቆጠር እንዳልሆነም አስታውቀዋል። ከዚህ ውጪ ግን ምን ዓይነት ጦር እንደሚሰማራ ፍንጭ አልሰጡም። እንደ ኒውዮርክ ታይምስ ከሆነ፤ ጋዜጠኞች ሚስተር ኤስፐርን ኢራን ላይ የአየር ድብደባ ለማካሄድ ታቅዶ እንደሆነ ሲጠየቁ "በአሁኑ ሰዓት እዚያ ውሳኔ ላይ አልደረስንም" ማለታቸውን ዘግቧል። የሳዑዲ መከላከያ ሚንስትር፤ በአገሪቱ የነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማት ላይ ከደረሰው ጥቃት የተሰበሰቡ ናቸው ያላቸውን የድሮን እና የሚሳዔል ስብርባሪዎች በማሳየት "ጥቃቱን ያደረሰችው ኢራን ነች" ሲል ከስሷል። "18 ድሮኖች እና ሰባት ሚሳዔሎች ወደ ሳዑዲ ተተኩሰዋል" ያለው የሳዑዲ መከላከያ፤ የጥቃቶቹ መነሻ የመን አይደለችም ሲል አስረግጦ ይናገራል።
news-53328678
https://www.bbc.com/amharic/news-53328678
"አለመረጋጋቱ የተፈጠረው ቀድመው በተዘጋጁ ኃይሎች ነው" ዐቃቤ ሕግ አዳነች አቤቤ
ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ ከተገደሉት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረጉት ረብሻ ለመፍጠር ቀደም ብለው ሲዘጋጁ በነበሩ ኃይሎች መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጓ እንደተናገሩት ባለፈው ሳምንት ተከስቶ ከነበረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ ለበርካቶች ሞትና ለከፍተኛ የንብረት መውደም ጋር ተያይዞ በቁጥጥር የዋሉት ሰዎች ቁጥር ከ2700 በላይ መሆኑንም ተናግረዋል። ወ/ሮ አዳነች እንዳሉት ተቋማቸው እስካሁን ባለው መረጃ "በንጹሃን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው ረብሻ የመፈጸም ቀድመው ዝግጅት አድርገው ሲጠባበቁ በነበሩ ኃይሎች ነው" በድንገት የተፈጸመ ወንጀል አለመሆኑን ጠቅሰዋል። ከግድያው በፊት ዝግጅት ስለመደረጉ ዐቃቤ ሕጓ እንደማስረጃ የጠቀሱት የአርቲስት የመገደል ዜና እንደተሰማ፤ የጦር መሳሪያ እና የግንኙነት ሬዲዮ ታጥቀው፣ ሚዲያ አዘጋጅተው ሲንቀሳቀሱ ተይዘዋል ብለዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በግድያው ማግስት በተከሰተው ውጥረት ምክንያት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉት ከአቶ ጃዋር እና ከአቶ በቀለ ጋር የጦር መሳሪያ እና ከመንግሥት አካላት ውጪ መያዝ የማይፈቀድ የሬዲዮ መገናኛ ከመያዙ በተጨማሪ ሚዲያውም በፍጥነት የተለያየ ነገር ሲያውጅ እንደነበር ገልጸዋል። ባልደራስ በተመለከተ ደግሞ "ቄሮን የሚሳደቡ፣ ኦሮሞ አያስተዳደረንም የሚሉና የሚረብሹ ወጣቶች በከተማዋ አሰማርቷል" በማለት ለዚህም ሰው ተመልምልሎ፣ ሞተር እና ታክሲ ተመድቦ፣ ገንዘብ ተከፍሎ ስለት እና ብረት ይዘው እንዲወጡ ተደርጓል ብለዋል። "እነዚህ አካላት ይህን ቀድመው ባያዘጋጁ ኖሮ እንዲህ አይነት ነገር በዚያ ደቂቃ፣ በዚያ ሰዓት አይፈጸምም ነበር።" ዐቃቤ ሕግ አዳነች ከዚህ ባሻገርም "በኦሮሚያ ውስጥ በጣም በሚያሳፍር እና በአሰቃቂ ሁኔታ ከሃጫሉ ግድያ ጋር ግነኙነት የሌላቸው፣ በየትኛውም ወገን የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች በቤታቸው ውስጥ እንዲገደሉ ተደርጓል" ሲሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙትን ድርጊቶች አውግዘዋል። የጸጥታ ኃይሉ አባላት መስዋዕት ሆነው ይህን ረብሻ ለማስቆም ጥረት ባያደርጉ ኖሮ፤ ይህ አሰቃቂ ድርጊት ከቁጥጥር ውጪ ይወጣና ይደርስ የነበረው ጉዳት ከፍተኛ ሊሆን ይችል እንደነበር "እውነት ለመናገር በቁጥጥር ሥር ባይውል ኖሮ ሊደርስ የሚችለውን ማሰብ እንኳን በጣም ከባድ ነው" ብለዋል። በሁከቱ ውስጥ ተሳትፎ አላቸው ተብለው ከተጠረጠሩት በተጨማሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕጓ እንደተናገሩት በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰዎች ቁጥር ከ2700 በላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በኦሮሚያ 1714 ሰዎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ደግሞ ወደ 1ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በፖሊስ መያዛቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጠቅላይ አቃቤ ሕጓ አለመረጋጋቱን ተከትሎ መንግሥት እየወሰዳቸው ያሉት እርምጃዎች "ዋነኛው ትኩረት አገርን መታደግ ነው። ሕዝቡ በብሔር እና በሐይማኖት እንዲጋጭ የሚደረገው ሙከራ አስከፊ ስለሆነ ይህ እንዲቆም እንሰራለን" ሲሉ ግጭቶችን ለመቀስቀስና ለማባባስ የሚደረጉ ጥረቶች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አመልክተዋል። በዚህም መንገዶች እንዲዘጉና ሕዝቡ ወደ ገበያ እንዳይወጣ በአካል፣ በበራሪ ወረቀት፣ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ሲቀሰቀሰ እንደነበር አስታውሰው፤ "ፖሊስ ይህን ተከታትሎ አክሽፎታል። አሁንም ይህን ማን እየፈጸመ እንደሆነ እናጣራለን። በቁጥጥር ሥር እናውላለን። አስፈላጊውን ማጣራት አድርገን ነጻ የሆኑ ሰዎች ይለቀቃሉ።" የአገሪቱን መረጋጋት ክፉኛ ካናጋውና ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ከአስር በላይ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ሰሞኑን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ገልጾ የነበረ ሲሆን ከዚህ በፊት ከተከሰቱ ግድያዎች አንጻር የታየው የፍትህ ሂደት አዝጋሚ መሆኑ የሰሞኑ የግድያ ወንጀል ፍጻሜም ሊዘገይ ይችላል የሚል ስጋት በበርካቶች ዘንድ አለ። ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አዳነች ከዚህ አንጻር የሰኔ 15ቱን እና የሰኔ 16ቱን ጉዳዮችን አንስተው ለቢቢሲ በሰጡት ማብራሪያ እንዳሉት የሰኔ 15ቱ ጉዳይ የፍርድ ውሳኔ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። ለዚህ ጉዳይ መጓተት እንደምክንያት የጠቀሱት አንደኛ ተከሳሽ የቀድሞው የደኅንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ተይዘው እንዲቀርቡ ውሳኔ ተሰጥቶ የነበረ መሆኑን አስታውሰው "ነገር ግን በሕዝብ መካከል ተደብቆ ስላለ ኃይል ወደዚያ በመላክ አንድን ሰው ለመያዝ በሚረደረገው ጥረት ሌሎች ይጎዳሉ የሚል ስጋት በመመጣቱ፤ ግለሰቡ በሌለበት የፍርድ ውሳኔ እንዲሰጣቸው ተወስኗል።" በዚህም በጉዳዩ የተከሰሱት ሌሎች አምሰት ሰዎች ላይ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ተደምጦ ተከሳሾቹም መከላከያ በማቅረባቸው በክሱ ላይ ጉዳዩን የሚመለከተው ችሎት የፍርድ ውሳኔ ከሚሰጥበት ደረጃ ላይ እንደተደረሰ ገልጸዋል። የሰኔ 16ቱ ጉዳይን በተመለከተ በጀነራል ሰዓረ መኮንን ግድያ ተሳትፎ የነበረው ተጠርጣሪም እራሱን ሳያውቅ በመቆየቱ መዘግየት እንደነበር አስታውሰው ከዚያ በኋላ ግን ችሎት ሲካሄድ ቆይቶ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ለሁለት ወራት በመቋረጡ ምክንያት ሊዘገይ እንደቻለ ተናግረዋል። በእነዚህ ጉዳዮች በኩል የታየው መዘግየት በፍትህ ሥርዓቱ በኩል በነበረ ቸልተኝነት ሳይሆን ከጉዳዮቹ ጋር ባጋጠሙ ችግሮችና በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የፍርድ ቤት ሥራ በመስተጓጎሉ ነው ብለዋል። ከሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ተጠርጥረው በተያዙ ሰዎች ላይ አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎ በተገቢው ፍጥነት ውሳኔ ለመስጠት መስሪያ ቤታቸው እንደሚሰራ አመልክተዋል።
news-57167680
https://www.bbc.com/amharic/news-57167680
እስራኤል-ጋዛ፡ ኔታንያሁ የሃማስ ታጣቂዎች ለዓመታት ወደ ኋላ ተመልሰዋል አሉ
እስራኤል በጋዛ ያደረገችው የዘጠኝ ቀናት ድብደባ የሃማስ ታጣቂዎችን በበርካታ ዓመታት ወደ ኋላ የመለሰ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ ተናገሩ።
የእስራኤልና የፍልስጥኤም ግጭት አሁንም ጋብ አላለም። በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ወደ ደቡባዊ እስራኤል በተኮሱት ሮኬት ሁለት የውጭ አገር የእርሻ ሠራተኞች ተገድለዋል። እስራኤልም በጋዛ የምታደርገውን የአየር ድብደባ ቀጥላለች። በዌስት ባንክ በራማላህ አቅራቢያ በተደረገ ተቃውሞ ቢያንስ ሦስት ፍልስጥኤማዊያን በእስራኤል ፖሊሶች ተገድለዋል። ግጭቱ እንዲቆም የተደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችም ያን ያህል ውጤት አላመጡም። ፈረንሳይ ከግብጽ እና ጆርዳን ጋር በመተባበር ግጭቱን ለመፍታት የሚያስችል ረቂቅ ሃሳብ ለተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት አቅርባለች። አገራቱ የተኩስ አቁም ጥሪ አቅርበዋል። ማክሰኞ ዕለት እስራኤል እርዳታ እንዲገባ ለመፍቀድ ወደ ጋዛ የሚወስደውን ድንበር የከፈተች ቢሆንም ከፍልስጤም ወታደሮች ሮኬቶች በመተኮሱ በድጋሜ ድንበሩ ተዘግቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ምንድን ነው ያሉት? ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታንያሁ "ጋዛን የሚያስተዳድረው የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኑ ሃማስ ያልተጠበቀ ዱብ ዳ አጋጥሞታል፤ ይህ ዘመቻም በእስራኤል ዜጎች ዘንድ መረጋጋት እስከሚመጣ ድረስ ይቀጥላል" ብለዋል። እንደ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በጋዛ ቢያንስ 215 ሰዎች ተገድለዋል። ከእነዚህ መካከል 100 የሚሆኑት ሴቶችና ህጻናት ናቸው። የጤና አገልግሎት ተቋም እንዳለው በእስራኤል ደግሞ ሁለት ህጻናትን ጨምሮ 12 ሰዎች ተገድለዋል። ማክሰኞ ዕለት እስራኤል በጋዛ ከተገደሉት መካከል ቢያንስ 150 የሚሆኑት ታጣቂዎች እንደሆኑ አስታውቃለች። ይሁን እንጅ ሃማስ በወታደሮቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት በአሃዝ አልጠቀሰም። ግጭቱ ከተከሰተ ጀምሮ እስራኤል ሁለቱ የፍልስጤም ታጣቂዎች ክንፍ 120 ሺህ የሚደርሱ ሮኬቶች በጋዛ እንደነበራቸው ግምቷን አስቀምጣለች። ታጣቂዎቹ ከማክሰኞ ዕለት ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ 3 ሺህ 300 የሚሆኑ ሮኬቶችን እስራኤል ላይ ተኩሰዋል። ከእነዚህ መካከል ከ450 እስከ 500 የሚደርሱት ከታለመው ሳይደርሱ በአጭር ቀርተው በጋዛ ጉዳት ማድረሳቸውን የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ተናግረዋል። በዌስት ባንክ የተፈጠረው ምንድን ነው? በዌስት ባንክ እና በምስራቅ እየሩሳሌም ያሉ በርካታ ፍልስጥኤማዊያን እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ድብደባ በመቃወም አድማ መትተዋል። በእስራኤል የሚገኙና የእስራኤል አረቦች በብዛት በሚኖሩባቸው እንደ ሃይፋ ያሉ አካባቢዎች ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል። የሕዝብ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች እና በርካታ የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል። በተለያዩ አካባቢዎችም ግጭቶች ነበሩ። በዌስት ባንክ ከተማ ራማላህ ሰላማዊ ባልሆነው ተቃውሞ ወቅት መተኮሳቸውን የእስራኤል ፖሊስ ተናግሯል። በአካባቢው የነበሩ ሦስት ፍልስጥኤማውያን መገደላቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በሄብሮን ወታደሮችን ለማጥቃት የሞከረ ሌላ ፍልስጤማዊ መገደሉንም የእስራኤል ጦር አስታውቋል። በእየሩሳሌም የደማስቆ መግቢያም ግጭቶች የነበሩ ሲሆን የእስራኤል ወታደሮች በርካቶችን አስረዋል። የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ድርጅት- ኦቻ በጋዛ 52 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ከእነዚህ መካከል 47 ሺህ የሚሆኑት ወደ ተባበሩት መንግሥታት ትምህርት ቤቶች መሸሻቸውን አስታውቋል። ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በኒውዮርክ በቅርቡ በተደረገው ስብሰባ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ በድጋሚ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ ቀርቷል። ፈረንሳይ ያቀረበችው የመፍትሔ ሃሳብ የተዘጋጀው ከግብፁ መሪ አብደል ፈታህ አል ሲሲ እና ከጆርዳኑ ንጉስ አብዱላህ ሁለተኛ ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ ወቅት መሆኑን አስታውቃለች። አሜሪካ ከዚህ ቀደም የጸጥታው ምክር ቤት የተኩስ አቁም ጥሪ የሚያቀርብ የጋራ መግለጫ ለማውጣት የተደረጉ ጥረቶች ላይ ሳትስማማ ቀርታለች። አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት እና ሌሎች ኃያላን ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። ግብጽ እስራኤልና ሃማስን ለማሸማገል እንደምትፈልግ ገልጻለች። ይሁን እንጅ እስራኤል ሃማስን እና እስላማዊ ጅሃድን ለማጥፋት ጥቃት መፈፀሟን እንደምትቀጥል አስታውቃለች። በተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም አምባሳደር ሪያድ ማንሱር የጸጥታው ምክር ቤት ወጥ አቋም አለማሳየቱን "አሳፋሪ" ብለውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ የቱርኩ ፕሬዚደንትን ሬሲብ ታይፕ ኤርዶዋንን ስለ እስራኤል ተናግረዋል ባለችው 'ጸረ አይሁዳውያን' ንግግር ከሳለች። ፕሬዚደንቱ በንግግራቸው በፍልስጥኤማውያን ላይ በምትፈጽመው ጥቃት እስራኤልን ከሰዋል። በቅርቡም "ይህ ተፈጥሯቸው ነው" በማለት "እስራኤል ገዳይ ናት" በማለት 'ጸረ አይሁዳውያን' ተደርጎ በስፋት የሚታይ ንግግር ተናግረዋል። የአሜሪካ የፕሬዚደንት የታይፕ ኤርዶዋንን ንግግር በጥብቅ አውግዛለች። ፕሬዚደንት ኤርዶዋንና ሌሎች የቱርክ መሪዎች ተጨማሪ ግጭት ሊቀሰቅስ ከሚችል መሰል ንግግርም እንዲታቀቡ አሳስባለች። ግጭቱን የቀሰቀሰው ምንድን ነው? በእስራኤልና በሃማስ መካከል የተከሰተው ግጭት የተነሳው በፍልስጤማውያን እና እስራኤላውያን ፖሊስ መካከል በምሥራቅ እየሩሳሌም ቅዱስ ሥፍራ ለቀናት በተፈጠረ ግጭት ነው። ሥፍራው በሙስሊሞችም ክብር የሚሰጠው ሲሆን ሃራም አል ሻሪፍ እያሉ ይጠሩታል። አይሁዳውያን ደግሞ የተራራው ቤተ መቅደስ ይሉታል። ሃማስ እስራኤል ፖሊሶቿን ከአካባቢውና በርካታ ሙስሊሞች ከሚኖሩበት የአረቦች ግዛት ሼክ ጃራህ እንድታነሳ ትፈልጋለች። ሼክ ጃራህ በርካታ የፍልስጥኤም ቤተሰቦች በአይሁድ ነዋሪዎች የተገደሉበት ነው። ሃማስ ለዚህ ጥያቄው መልስ ሳያገኝ ቀረ። ከዚያም ሮኬት መተኮስ ጀመረ። በእርግጥ የፍልስጤማውያን ቁጣ ለሳምንታት በእየሩሳሌም በነበረው ውጥረት ታምቆ የቆየ ነበር። ከሚያዝያ ወር አጋማሽ ጀምሮም ከፖሊሶች ጋር ግቶች ነበሩ። ከዚያም እስራኤል እአአ1967 በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት፤ ምስራቅ እየሩሳሌምን በተቆጣጠረችበትና 'የእየሩሳሌም ቀን' ተብሎ በሚጠራው ዓመታዊ በዓል ላይ ሌላ ችግር ተቆሰቆሰ። ግጭቱ ለዓመታት የነበረ ይሁን እንጅ የሰሞኑ ግጭት መነሻ ግን ይኸው ነው። ለሁለቱም ወገኖች ሃይማኖታዊና ብሔራዊ መሠረት ያላት የከተማዋ እጣ ፈንታም ለአስርት ዓመታት በዘለቀው የእስራኤልና ፍልስጤም ግጭት ላይ የወደቀ ነው። እስራኤል እአአ በ1980 ምሥራቅ እየሩሳሌምና ጠቅላላ ከተማዋን እአአ በ2017 ዋና መዲናዋ አድርጋለች። ነገር ግን ይህ በአብዛኛው አገራት እውቅና አልተሰጠውም። ፍልስጤም ደግሞ እመሰርተዋለሁ ብላ ላሰበችው ለራሷ አገር ዋና መዲናነት የምሥራቃዊ እየሩሳሌም ግማሹ ክፍል ይገባኛል ትላለች።
news-55500054
https://www.bbc.com/amharic/news-55500054
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በታኅሣስ ወር ብቻ የደረሱ የእሳት አደጋዎች
በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች በዚህ ዓመት በታኅሣስ ወር ብቻ በርካታ የእሳት አደጋዎች ደርሰዋል። በዚህም የተነሳ በሚሊዮኖች ብሮች የሚገመት ንብረት ወድሟል።
እነዚህ አብዛኞቹ የእሳት አደጋዎች የደረሱት በተለይ በገበያ ሥፍራዎች ላይ ሲሆን በመኖሪያ አካባቢዎች ላይ ደረሱና ጥቂት የማይባሉ ነዋሪዎች የተፈናቀሉባቸውም አጋጣሚዎች አሉ። ቢቢሲ ከተለያዩ የዜና ዘገባዎች ካሰባሰባቸው የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች ውስጥ ባለንበት የታኅሣስ ወር ያጋጠሙት በቁጥር በርከት ይላሉ። ምክንያቱን ግን ለመገመት አስቸጋሪ ነው። ቢሆንም ይህ ተደጋጋሚ የእሳት አደጋ ትኩረት እንዲያገኝ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሽፋን ያገኙትን የእሳት አደጋዎችን በየቀናቸው በቅደም ተከተል እንደሚከተለው አጠናቅረናቸዋል። ነገር ግን በወሩ ውስጥ የተከሰቱት የእሳት አደጋዎች እነዚህ ብቻ ላይሆኑ ይችላሉ። በተለያዩ ምክንያቶች ያልተነገሩ እንዲሁም በዚህ ጥንቅር ውስጥ ያልተካተቱ ሊኖሩ የሚችሉብት ዕድል አለ። ታኅሣስ 8/2013 ዓ.ም ሐረማያ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ህንፃ 3 በሚባለውና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ከሚኖሩበት ህንፃ የኤሌክትሪክ መቆጣጠሪያ ላይ የተነሳ የእሳት አደጋ ተከስቶ እንደነበር የዩኒቨርስቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አስታውቆ ነበር። በአደጋው በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ቢሆንም በሰው ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱ ተገልጿል። ታኅሣስ 9/2013 ቡራዩ በቡራዩ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ 10 ሚሊየን ብር የሆነ ንብረት የወደመ ሲሆን፤ በወቅቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እሳቱ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ መቀስቀሱን ገልጾ ነበር። አደጋው የደረሰው በቡራዩ ከተማ ገፈርሳ ኖኖ ቀበሌ ልዩ ስሙ ገብርኤል በሚባል አካባቢ ሲሆን በ16 ሱቆች፣ በ3 መኖሪያ ቤቶችና 3 ባርና ሬስቶራንቶች ላይ ውድመት ቢያጋጥምም በሰው ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም ተብሏል። ታኅሣስ11/2013 ወላይታ ሶዶ በወላይታ ሶዶ ከተማ "መርካቶ ገበያ" መንስኤ ባልታወቀ ሁኔታ የእሳት አደጋ የተከሰተው ሲሆን በወቅቱ እሳቱን ለማጥፋት የወላይታ ሶዶ ከተማ እሳት አደጋ መከላከያ ቡድን ጥረት ያደረገ ቢሆንም በነበረው ከባድ ነፋስ እሳቱ በከፍተኛ ፍጥነት መዛመቱ ተገልጿል። አደጋው በበርካታ የንግድ ሱቆችና ተቋሟት ላይ ውድመት ያስከተለ ሲሆን፤ ማለዳ የተነሳውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር የተቻለውም ከ6:20 በኋላ እንደነበር በወቅቱ የከተማው አስተዳደር አሳውቋል። በሶዶ ከተማ የገበያ ቦታ ተመሳሳይ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ሲደርስ ለ5ኛ ጊዜ ሲሆን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የግብይት ማዕከሉን ዘመናዊ ለማድረግ እንደሚሰራም ተገልጿል። ታኅሣስ 13/2013 ባሕርዳር በአማራ ክልል መዲና በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 3 በተለምዶ ጉዶባሕር ተብሎ በሚጠራው ሰፈር በደረሰ የእሳት አደጋ በ22 የመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ሲደርስ፤ በቃጠሎው ከ300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙ ተነግሯል። ከቀኑ 7:00 ሰዓት ገደማ የተነሳውን ይህን የእሳት አደጋን ተከትሎ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ እንዳሰወቀው ቃጠሎው እንጀራ በሚጋገርበት ወቅት ከተቀጣጣይ ነገሮች የተነሳ መሆኑን በወቅቱ ተገልጾ ነበር። ታኅሣስ 14/2013 ጅግጅጋ የሶማሌ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው ጅግጅጋ ከተማ ቀበሌ 02 በልዩ ስሙ ድብኡራሾ ሱቅ ተብሎ በሚታወቀው ቦታ መንስኤው አልታወቀም የተባለ የእሳት አደጋ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ተከስቶ ነበር። ከአንድ ሱቅ እንደተነሳ በተገለጸው የእሳት አደጋ በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት ያላደረሰ ሲሆን በፍጥነት በተዛመተው እሳት ሰባት የንግድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ አድርሷል። በዚህም በድምሩ ወደ 1.2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት መውደሙ በወቅቱ ተገልጾ ነበር። ታኅሣስ 14/2013 መቅደላ ወረዳ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ አዲሱ መናኽሪያ ላይ ከምሽቱ 3፡30 ላይ በኤሌክትሪክ ምክንያት በተነሣ እሳት ሁለት የንግድ ቦታዎች በውስጣቸው ከነበረ ሙሉ ንብረት ጋር መውደማቸ ተገልጿል። በቃጠሎውም የ23 ግለሰቦችና የተለያዩ ተቋማት ንብረት የሆኑ በጥቅሉ ከ1.2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የወረዳው ኮምዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት አመልክቷል። ታኅሣስ 18/2013 ሀላባ ዞን በደቡብ ክልል በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ላይኛ በደኔ ቀበሌ ላይ ውስጥ በተከሰተ የእሳት አደጋ 11 መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል። ለጊዜው ምክንያቱ ባልተወቀ ሁኔታ ከረፈዱ 5:00 ሰዓት አካባቢ የተነሳው ይህ የእሳት አደጋ ያደረሰው የንብረት ጉዳት ግምት አልተገለጸም። ታኅሣስ 18 እና 19/2013 ሀዲያ ዞን በደቡብ ክልል በሀዲያ ዞን ሁለት ወረዳዎች ላይ ባልታወቀ ምክንያት በደረሰ የእሳት አደጋ 510 የቤተሰብ አባላት መፈናቀላቸውን የዞኑ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ገልጾ ነበር። በወቅቱ እንደተነገረው በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ በሦስት ቀበሌዎች ኤራ ጌሜዶ፣ ኩናፋ፣ ጉና ሜጋቾ እንዲሁም በሌሞ ወረዳ ኦሞ ሾራ አራት ቀበሌዎች በደረሰ እሳት አደጋ ሁለት ቆርቆሮና 45 የሳር ክዳን ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ተገልጿል። በአደጋው በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም በርካታ ቁጥር ያላቸው በድምሩ ከ23 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል። በተጨማሪም በዞኑ ውስጥ በታኅሣስ ወር ብቻ በሆሳዕና ከተማ እና ወረዳዎች 15 ሱቆች 47 ቤቶች፣ በእሳት ተቃጥለው 33 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ዞን ገልጿል። ታኅሣስ 19/2013 ምዕራብ ኦሞ ዞን በደቡብ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ሾላ ቀበሌ ከቀኑ11፤00 ሰዓት በተከሰተ የእሳት አደጋ ከ586 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጿል። ከባድ ጉዳትን ባደረሰው በዚህ የእሳት አደጋ ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ 1ሺህ 840 መኖሪያ ቤቶችና 547 የንግድ ቤቶች እንዲሁም በወርቅ ሥራ የሚተዳደሩ 37 ማኅራት ንብረታቸ ሙሉ በሙሉ ወድሟል። በአደጋው 16 ሺህ 709 ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤታቸው በመፈናቀላቸው በሐይማኖት ተቋማትና ትምህርት ቤቶች ቤት መጠለላቸው ተገልጿል። ታኅሣስ 22/2013 በደብረ ማርቆስ በደብረማርቆስ ከተማ ቀበሌ 05 በተለምዶ ጉልት ገበያ ተብሎ በሚጠራ የገበያ ስፍራ የደረሰ የእሳት አደጋ ንብረት ሲያወድም በሰው ህይወት ላይ ጉዳት አለመድረሱ ተገልጿል። የእሳት አደጋው ሐሙስ ምሽት 3፡00 አካባቢ የተከሰተ ሲሆን ባደረሰው ጉዳት በገበያው የሚገኙ ሱቆችና ኮንቴይነሮች በአብዛኛው መውደማቸውን የተነገረ ሲሆን የእሳት አደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ይገኛል።
47493141
https://www.bbc.com/amharic/47493141
አልጀሪያውያን ለስድስት አመታት ያላዩዋቸውን መሪ ይውረዱ እያሉ ነው
የ82 ዓመቱ የአልጄሪያው መሪ አብዱላዚዝ ቡተፍሊካ ለአምስተኛ ጊዜ ለስልጣን መወዳደራቸውን በመቃወም ዛሬ ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ሊደረግ ነው።
ይህ ዜና ከተሰማበት ቀን አንስቶ ባለፈው ወር በእያንዳንዱ ቀን የተቃውሞ ሰልፍ ሲደረግ የነበረ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ህክምና እየተከታተሉ ነው። የተቃውሞ ሰልፉን የጠሩት የቃዋሚ ፓርቲ አቀንቃኞች ሰልፉን የ20 ሚሊየኖች ጉዞ የሚል ስያሜ ሰጥተውታል። አልጄሪያውያንም መንገዶችን እነዲያጥለቀልቁ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። • ከስድስት አመት በላይ መሪያቸውን ያላዩት አልጀሪያውያን • በ82 ዓመት አዛውንት የምትመራው አልጄሪያ ፈተና ገጥሟታል እንደ ጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር በ2014 በሀገሪቱ በተካሄደው ምርጫ አሸንፈው በ1999 የተረከቡትን ስልጣን ሲያስቀጥሉ በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ብለው መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ የውሃ ሽታ ሆነው የቀሩት ፕሬዝዳንቱ እራሳቸውንም መርዳት ስለማይችሉ በጋሪ (wheelchair) እየተገፉ ነው የሚንቀሳቀሱት። ፕሬዝዳንቱ ባስነበቡት ደብዳቤ በመጪው ሚያዚያ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚያሸንፉ ከሆነ ብሔራዊ መድረክ በማቋቋም እሳቸው የማይሳተፉበት አዲስ የምርጫ ስርአት እንደሚዘረጉ ገልጸው ነበር። ይህ ቃላቸው ግን አብዛኛውን አልጄሪያዊ ከማመጽ የሚያስቆመው ሆኖ አልተገኘም። በዚህ ሳምንት ፕሬዝዳንቱ ሃገሪቱን ለመምራት አካላዊም ስነልቦናዊም ብቃት የላቸውም በማለት በርካታ የህግ ባለሙያዎች ተቃውሟቸውን ገልጸው ነበር። ባለፈው ሳምንት ደግሞ በአዛውንት አንመራም ያሉ በርካታ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ወጣቶች በዋና ከተማዋ አልጀርስ ከባድ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። • "የጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልቁ ስኬት ብዙ ሰው በተስፋ እንዲኖር ማድረጋቸው ነው" ዶ/ር ዮናስ አዳዬ 30 በመቶ የሚሆነው የአልጄሪያ ወጣት ስራ የሌለው ሲሆን አብዛኛዎቹ ደግሞ ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ነው። በፈረንጆቹ 1999 ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቡተፍሊካ በሃገሪቱ ተከስቶ የነበረውንና የ100 ሺ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውን የእርስ በርስ ጦርነት ማስቆማቸው ይታወሳል። ነገር ግን አልጄሪያውያን ለሰሩት ነገር ሁሉ እናመሰግናለን፤ አሁን ግን ይበቃዎታል እያሏቸው ይመስላል።
news-57019410
https://www.bbc.com/amharic/news-57019410
ሕዋ ሳይንስ፡ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ግዙፍ የቻይና ሮኬት ወደ ምድር እየተምዘገዘገ ነው
ቻይና በቅርቡ ወደ ሕዋ ያስወነጨፈችው ሮኬት ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ስብርባሪው መሬት እንደሚደርስ ተነገረ።
ይህ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የሮኬት ስብርባሪዎች አካል በትክክል መቼ እና የት እንደሚወድቁ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም። 'ማርች 5ቢ' የሚል ስያሜ የተሰጠው ሮኬት ባሳለፍነው ወር መገባደጃ ላይ ነበር ቻይና በሕዋ ላይ ለመስራት ላሰበችው ማዕከል የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ይዞ ነው ወደ ህዋ የተወነጨፈው። 18ሺህ ኪሎ ግራም የሚመዝነው ሮኬት በአስርት ዓመታት ውስጥ ቁጥጥር ሳይደረግበት ወደ ምድር የሚወድቅ ግዙፍ ቁስ ይሆናል ተብሏል። አሜሪካ ትናንት ባወጣችው መግለጫ የሮኬቱን አቅጣጫ እና አካሄድ በቅርበት እየተከታተለች እንደሆነ በመግለጽ ተኩሳ የመጣል እቅድ ግን እንደሌላት አስታውቃለች። የአሜሪካ የመከላከያ ሚንስትሩ ሎይድ ኦስቲን "ሮኬቱ ጉዳት ሳያስከትል እንደሚወድቅ ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል። ምናልባት የባህር አካል ላይ ወይም ሰዎች በማይኖሩበት ቦታ ላይ ይወድቃል ብለው እንደሚገምቱ ተናግረዋል። የመሬት አካል አብዛኛው ክፍል በውሃ የተሸፈነ እና አብዛኛው የምድራችን ክፍል ሰዎች የማይኖርበት መሆኑን ከግምት በማስገባት ሮኬቶ በሰዎች ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት አነስተኛ ነው ተብሏል። ባለሙያዎች 75 ሜትር ቁመት ያለው ሮኬት ምድር ሳይደርስ አብዛኛው ክፍሉ ተቃጥሎ ሊያልቅ እንደሚችል ጠቁመዋል። ከፍተኛ ሙቀት መቋቋም የሚችሉ እና የማይቀልጡ የሮኬቱ አካላት እንደሚወድቁ ግን ይጠበቃል። ሮኬቱ ወደ ምድር ቢያንስ በሰዓት 60 ኪሎ ሜትር እየምዘገዘገም እንደሚወርድ ይጠበቃል። ከዚህ በፊት በተመሳሳይ አንድ የቻይና መንኩራኩር ስብርባሪ ከታሰበለት ጊዜና ቦታ ውጪ ወደ ምድር ከባቢ አየር በመግባት በአንዲት የአይቮሪ ኮስት የገጠር መንደር ውስጥ ወድቆ ነበር። የቻይና ሕዋ ሳይንስ ኤጀንሲ እስካሁን የሮኬቱን ስብርባሪ መቆጣጠር ይቻላል ወይ በሚለው ላይ ምንም አይነት አስተያየት አልሰጠም። ቻይና ከዚህ በኋላም ተጨማሪ 10 ተመሳሳይነት ያላቸው ሮኬቶችን ወደ ሕዋ ለማስወንጨፍ እቅድ ያላት ሲሆን የአውሮፓውያኑ 2022 ከመጠናቀቁ በፊት ደግሞ የራሷን የሕዋ ማዕከል ለመገንባት አቅዳለች።
news-47451865
https://www.bbc.com/amharic/news-47451865
አእምሯችን ሲጎዳ ልባችን ይሰበር ይሆን?
በጣም አሳዛኝ ከሆነ አጋጣሚ በኋላ ልባችን ሊጎዳ ይችላል። ይህን የሚፈጥረው ደግሞ አእምሯችን እንደሆነ የዘርፉ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።
የስዊዘርላንድ ተመራማሪዎች 'የተሰበረ ልብ ምልክቶች' (ብሮክን ኸርት ሲንድረም) የተባለው ያልተለመደ የልብ በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ሲያጠኑ ቆይተዋል። ይህ የልብ መድከም ድንገተኛ ሲሆን ብዙ ጊዜ ሰዎች በጥልቅ ሀዘን ሲወድቁና የሚያስጨንቅ ጊዜ ላይ ሲሆኑ ይከሰታል። • በሰው ክፋይ ሕይወት መዝራት - የኩላሊት ንቅለ ተከላ • በኢትዮጵያ ለካንሰር ተጋላጮች እነማን ናቸው? ምንም እንኳን ጉዳዩ በትንሹ የተጠና ቢሆንም የአውሮፓው የልብ መፅሄት ለአእምሮ ለጭንቀት መልስ የሚሰጥበት መንገድ ጋር እንደሚገናኝ ይጠቁማል። ትንፋሽ ማጣት እና ህመም በሽታው ያለባቸውን ሰዎች ልብ በማመላከት በሌላ ስሙ 'ታኮትሱቦ ሲንድረም' ተብሎ የተሰየመው ይህ የልብ በሽታ በድንጋጤም ሊከሰት ይችላል። በደም ትቦ መደፈን ምክንያት ከሚመጣው የልብ ድካም የተለየ ቢሆንም እንደ ትንፋሽ መቋረጥ እና የደረት ህምም አይነት ተመሳሳይ ምልክቶችን ያሳያል። ብዙ ጊዜ አሳዛኝ ክስተቶች የበሽታው መንስኤ ሲሆኑ እንደ ሰርግ እና አዲስ ሥራ ማግኘትን የመሳሰሉ የደስታ ሁኔታዎችም የበሽታው መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ። ህመሙ ጊዜያዊ ሆኖ የልብ ጡንቻ ከቀናት፣ ከሳምንታት ወይም ከወራት በኋላ ወደ ጤነኛ ሁኔታው ሊመለስ ይችላል። ለአንዳዶች ግን ህመሙ ገዳይ የሚሆንበት አጋጣሚ አለ። 'ብሮክን ኸርት ሲንድረም' እንግሊዝ ውስጥ በዓመት 2500 ሰዎችን ያጠቃል ተብሎ ይታሰባል። ትክክለኛ መንስኤው ባይታወቅም ተመራማሪዎች ከልክ ያለፈ እንደ 'አድሬናሊን' የመሳሰሉ የጭንቀት ሆርሞኖች በአካላችን ውስጥ መመረት ምክንያቱ ነው ይላሉ። ምስጢራዊነት ዶ/ር ጀሌና ግሃደሪ እና አጋሮቹ በዙሪክ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በ 'ብሮክን ኸርት ሲንድሮም' የተጠቁ 15 ህሙማንን አእምሮ አጥንተዋል። የህሙማኑ የአእምሮ ምስሎች ከ 39 ጤነኛ ሰዋች ጋር ሲነፃፀሩ ጉልህ ልዩነት አሳይተዋል። • "ወንዶች በጡት ካንሠር እንደሚያዙ አላውቅም ነበር" • ልብ የረሳው አውሮፕላን በሽታው ባለባቸው ሰዎች ላይ፤ ንቁ ሆኖ ስሜቶችን በሚቆጣጠረው የአእምሮ ክፍል እና ምንም ሳያስብ እንደ ልብ ምት ያሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በሚቆጣጠረው ክፍል መካከል አነስተኛ ተግባብቶ የመስራት ችግር ይስተዋላል። እነዚህ ሁለት የአእምሮ ክፍሎች አካላችን ለጭንቀት ምላሽ የሚሰጥበትን መንገድ ይቆጣጠራሉ ተብሎ ይታመናል። "ስሜቶች የሚብሰለሰሉት አእምሮ ውስጥ ነው። ስለዚህ በሽታው አእምሮ ውስጥ ጀምሮ ወደ ልብ ይወርዳል" በማለት ዶ/ር ግሃድሪ ያስረዳሉ። በሽታው እንዴት እንደሚጀምር እና እንዴት እንደሚበረታ እስካሁን በውል አይታወቅም። ለዚህም የበለጠ ጥናት መደረግ አለበት። ህመምተኞቹ በበሽታው ከመያዛቸው በፊት ወይም ልክ በበሽታው መያዝ ሲጀምሩ የሚያሳይ የአእምሮ ምስል አልተገኘም። ስለዚህም ተመራማሪዎቹ የአእምሮ ክፍሎቹ አለመግባባት በሽታውን ይፍጠረው ወይም በሽታዉ አለመግባባቱን ይፍጠር ለማወቅ ተቸግረዋል።
46121118
https://www.bbc.com/amharic/46121118
በኢራቅ አይ ኤስ 200 የጅምላ መቃብሮችን ትቶ መሄዱን የተባበሩት መንግሥታት ተናገረ
በኢራቅ እስላማዊ ቡድኑ አይ ኤስ ይቆጣጠራቸው በነበሩ አካባቢዎች ከ200 በላይ የጅምላ መቃብሮችና በሺዎች የሚቆጠሩ አስክሬኖች ማግኘቱን የተባበሩት መንግሥታት አጥኚ ቡድን ገለጠ።
መቃብሮቹ እስከ 12000 አስክሬን ድረስ እንደያዙ አጥኚው ቡድን ይፋ አድርጓል። እስላማዊ ቡድኑ ከፊል ኢራቅን በቁጥጥሩ ስር አውሎ የነበረው በ2014 ሲሆን ጨካኝ አገዛዝን በማስፈንና የሚቃወሙትን በመግደል ይታወቃል። የኢራቅ ጦር በአሜሪካ የአየር ጥቃት ተደግፎ ባካሄደው ዘመቻ አይ ኤስ ከበርካታ ቦታዎች ለቅቆ የወጣ ሲሆን በአንዳንድ ስፍራዎች ግን አሁንም ይንቀሰቀሳል። • በማክሮን ላይ ጥቀት ለመሰንዘር አሲረዋል የተባሉ ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ • የዲሞክራቶች ድል ለትራምፕ ድንጋጤ • ሕፃናትን በማቀዝቀዣ ውስጥ ጭኖ ወደ እንግሊዝ ለመግባት የሞከረ መኪና በቁጥጥር ስር ዋለ አሁን የተገኙት የጅምላ መቃብር ስፍራዎች ሟቾችን ለመለየት ብቻ ሳይሆን በሰብዓዊነት ላይ የደረሱ ግፎችን፣ የተፈፀሙ የጦር ወንጀሎችንና የዘር ማጥፋት እርምጃዎች ላይ ክስ ለመመስረት የሚያስችሉ መረጃዎች ይሆናሉ ተብሏል። እንደ ተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ከሆነ እስካሁን 202 የጅምላ መቃብሮች የተገኙ ሲሆን ከእነዚህም 95ቱ በናይንቫህ፣ 37ቱበኪርኩክ፣ 36ቱ በሳላህ አል ዲን እና 24ቱ በአንባር ናቸው። መርማሪ ቡድኑ ከ6000-12000 ሟቾች በጅምላ መቃብሩ ተቀብረው እንደሚገኙ የገመቱ ሲሆን፤ ሴቶች፣ ህፃናት፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች፣ የኢራቅ የፀጥታ ኃይሎችና የውጪ ሀገር ዜጎች ከሟቾቹ መካከል ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገምቷል።
news-49889300
https://www.bbc.com/amharic/news-49889300
ቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ የተመሰረተበትን 70ኛ አመት እያከበረች ነው
ቻይና- የቻይና ህዝቦች ሪፐብሊክ (ፒአርሲ) ተብሎ የሚጠራውን የኮሚዩኒስት ፓርቲ የተመሰረተበትን ሰባኛ አመት በደመቀ ሁኔታ እያከበረች ነው።
በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 1949 ማኦ ዜዱንግ ወይም ሊቀመንበር ማኦ የኮሚዩኒስት ጥምር ኃይሎች ደም አፋሳሹን የርስ በርስ ጦርነት ማሸነፋቸውን ተከትሎ ፒአርሲ መመስረቱን አወጁ። ዘመናዊት ቻይና በሚያስገርም ፍጥነት እያደገች ቢሆንም በብዙዎች ዘንድ ነፃነትን በመግታትም የሰላ ትችት ይቀርብባታል። •የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ትውስታዎች በኢትዮጵያውያን ዓይን •የጤፍ ቢራ አሜሪካ ውስጥ ገበያ ላይ ዋለ ፕሬዚዳንት ዢ ሺንፒንግ በቲናንማን አደባባይ የተደረገውን ከፍተኛ ወታደራዊ ትዕይንትን ተከትሎ እንደተናገሩት የትኛውም ኃይል ቻይናን እንደማያነቃንቃት ነው። "የትኛውም ኃይል ቢሆን ቻይናንም ሆነ ህዝቦቿን ወደፊት ከመሄድ አያግዳቸውም" በማለት ለተሰበሰበው ህዝብ ተናግረዋል። ማኦ የቻይና ህዝቦች ሪፐብሊክን መመስረት ባወጁበት ተመሳሳይ ቦታ ከመቆም በተጨማሪ ማኦ በጊዜው ለብሰውት የነበረውን ተመሳሳይ ልብስም ለብሰው ታይተዋል። ፕሬዚንዳት ዢ አብዮታዊውንና መስራቹን አባትም ራዕይም ሆነ ትዝታ ከማጋራትም አልተቆጠቡም። ነገር ግን በዛሬው ዕለት የሚደረገውን አከባባበር በሆንግ ኮንግ የሚደረገው ተቃውሞ እንዳያጠለሸው ተሰግጧል። •ቻይና የዶናልድ ትራምፕን ስልክ ጠልፋው ይሆን? በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ቤጂንግ በሆንግኮንግ ማህበረሰብና ፖለቲካ ላይ የምታደርገውን ቅጥ አልባ ቁጥጥር በመቃወም ተቃውሟቸውን ማሰማት ከጀመሩ ዋል አደር ያሉ ሲሆን፤ በዛሬውም ዕለት ተቃውሟቸውን ይቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል። የመከላከያ ሚኒስትር እንዳሳወቀው 15ሺ ወታደሮች፣ 580 ወታደራዊ ቁሶች እንዲሁም 160 የጦር አውሮፕላኖች በዚህ ወታደራዊ ትዕይንት ተሳታፊ ሆነዋል። የሃገሪቷ አዲስ ወታደራዊ የቴክኖሎጂ ግኝቶች በትእይንቱ ላይ የቀረቡ ሲሆን፤ ታንኮች፣ ሄሊኮፕተሮች፣ ዲኤፍ 41 የሚል መጠሪያ የተሰጠው የባሊስቲክ ሚሳይልም ይገኙበታል። ከወታደራዊ ትዕይንቱ በተጨማሪ ከተለያየ የማህበረሰቡ ክፍል የተውጣጡ ከመቶ ሺ በላይ ግለሰቦች የሚሳተፉበት ደመቅ ያለ ዝግጅትም የተደረገ ሲሆን፤ በዚህም አርሶ አደሮች፣መምህራን፣ ዶክተሮችና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል። ዝግጀቱ ለመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣ ለተጋበዙ ግለሰቦችና ለውጭ ኃገር ዲፕሎማቶች ክፍት ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰቦች በያሉበት ሆነው የሚከታተሉት ይሆናል። የፀጥታው ቁጥጥር በማዕከላዊ ቤጂንግ ለሳምንታት ያህል በጣም የጠበቀ ሲሆን በተለይም በትዕይንቱ አካባቢ ድሮን (ሰው አልባ አውሮፕላንን)ጨምሮ ለውድድር የሚሆኑ እርግቦችም ተከልክሏል። • ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ ሚዲያን ሳንሱር በማድረግ በምትተቸው ቻይና ወታደራዊ ትዕይንቱን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥጥር የጠበቀ ሲሆን የተለያዩ ፕሮግራሞችን የሚያስታላልፉ ሚዲያዎች የፕሮግራሞች ዝርዝር የተሰጣቸው ሲሆን በኦንላይንም ላይ የኮሚዩኒስት ፖርቲንም ሆነ መሪዎቹን መተቸት ክልክል ነው።
48277722
https://www.bbc.com/amharic/48277722
ዋትስአፕ ሲጠቀሙ እንዴት ራስዎን ከጥቃት መከላከል እንደሚችሉ ያውቃሉ?
ዋትስአፕን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች ደረሱ ሲባል 1.5 ቢሊየን የዋትስአፕ ተጠቃሚዎች ይደናገጣሉ።
እርሰዎም "እንዴት የመረጃዎቼን ደህንነት መጠበቅ እችላለሁ?" ብለው ሀሳብ ገብቶዎት ይሆናል። በተለይ ጋዜጠኛ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ወይም ጠበቃ ከሆኑ ለጥቃቱ ተጋለጭ ነዎት። ዋትስአፕ ሲጠቀሙ መውሰድ ያለብዎትን ጥንቃቄ እንነግርዎታለን። 1. 'አፕዴት' ያድርጉ በዚህ ሳምንት የኮምፒውተር መረጃ መዝባሪዎች (ሀከርስ) ዋትስአፕን ተጠቅመው የስለላ መተግበሪያ ጭነው እንደነበር ሲሰማ ብዙዎች መደናገጣቸው አልቀረም። • ዋትስአፕ በተደጋጋሚ መልዕክት ማጋራትን አገደ ጥቃቱ እንደደረሰ የታወቀው በዚህ ወር መባቻ ላይ ሲሆን፤ የፌስቡክ የደህንት ሰዎች እንዳሉት የስለላ መተግበሪያውን መጫን የተቻለው የዋትስፕ የድምፅ ጥሪን በመጠቀም ነበር። ዋትስአፕ ጥቃቱ መድረሱን እንዳወቀ ተጠቃሚዎች የዋትስአፕ መተግበሪያ በድጋሚ እንዲጭኑ (አፕዴት እንዲያደርጉ) ጠይቆ ነበር። እርስዎም ራስዎን ለመከላከል የዋትስአፕ መተግበሪያዎትን አዘውትረው 'አፕዴት' ማድረግ አለብዎት። በዋትስአፕ የሚላላኩትን መልዕክት ከእርሰዎና ከመልዕክት ተቀባዩ ውጪ ማየት ባይቻልም፤ ሀከሮች ኢላማ የሚያደርጉት የሚለዋወጡትን መልዕክት ነው። ስለዚህም 'አፕዴት' በማድረግ ራስዎን መከላከል አይዘንጉ። 2. 'ባክ አፕ' ሲያደርጉ ይጠንቀቁ ዋትስፕ ላይ የሚላላኩት መልዕክት በእርስዎና በተቀባዩ መካከል የሚጠበቅ ቢሆንም፤ መልዕክቶቹ ወደጉግል ድራይቭ እንዲሸጋገሩ 'ባክ አፕ' ካደረጉ ክፍተት ይፈጠራል። 'ባክአፕ' የሚደረግ መልዕክትን ደህንነት ዋትስአፕ አይጠብቅም። ስለዚህ አንድ ሰው ወደጉግል ክላውድዎ መድረስ ከቻለ መልዕክቶቹን ያገኛቸዋል። • 'ዋትስአፕ' በቻይና እክል ገጥሞታል የሚለዋወጡትን መልዕክት መጠበቅ ከፈለጉ ዋትስአፕ መልዕክቶችዎን 'ባክአፕ' እንዳያደርግ ይዘዙ። 'ሴቲንግ' ውስጥ ገብተው 'ቻት ባክአፕ' የሚለውን ማጥፋት ይችላሉ። 3. 'ቱ ፋክተር አውተንቲኬሽን' 'ቱ ፋክተር አውተንቲኬሽን' የመረጃዎትን ደህንነት መጠበቅ የሚችሉበት መንገድ ነው። ዋትስአፕን ጨምሮ የተለያዩ መተግበሪያዎችን ለመጠቀም የሚሞክሩ ሰዎችን ትክክለኛ ማንነት ለማወቅ የሚረዳ መንገድ ነው። • በሞባይልዎ የኢንተርኔት ወጪ ተማረዋል? ተጠቃሚዎች መጀመርያ ላይ ስማቸውን ይጽፉና የይለፍ ቃል (ፓስወርድ) ያስገባሉ። ወደተንቀሳቃሽ ስልክ በሚላክ መልዕክት የግለሰቡን ማንነት ማረጋገጥም ይቻላል። 4. ዋትስአፕዎን ይቆጣጠሩ ዋትስአፕና ሌሎችም መተግበሪያዎች ደህንነትዎን የሚጠብቁበት አሠራር አላቸው። ዋትስፕ ላይ 'ሴቲንግ' ውስጥ ገብተው 'አካውንት' የሚለውን ከመረጡ በኋላ የተለያዩ አማራጮች ያገኛሉ። • ወደ ድብቁ የዋትስአፕ መንደር ስንዘልቅ 'ላስት ሲን' ዋትስአፕ የተጠቀሙበትን የመጨረሻ ሰአት ማሳወቅ ወይም መደበቅ የሚችሉበት አማራጭ ነው። ፎቶዎ ወይም ያሉበትን ቦታ ማሳወቅና መሸሸግም ይችላሉ። የመረጃዎትን ደህንነት ለመጠበቅ ከሚረዱ መንገዶች አንዱ የሚልኩትን መልዕክትና የዋትስአፕ እንቅስቃሴዎን የሚያዩ ሰዎችን መምረጥ የሚችሉበት አሠራር ነው።
55040023
https://www.bbc.com/amharic/55040023
አሜሪካዊያን ከ20 ቀን በኋላ የኮቪድ ክትባት መከተብ ይጀምራሉ ተባለ
የአሜሪካ የኮሮናቫይረስ ክትባት መርሐግብር ቢሮ ኃላፊ የመጀመርያው አሜሪካዊ ተከታቢ በዲሴምበር 11 (ታኀሣሥ 2) ክትባት ሊያገኝ እንደሚችል ጠቆሙ።
ይህም ማለት የመጀመርያው ተከታቢ የኮቪድ ክትባት ለመውሰድ ከ20 ቀናት ያነሰ ጊዜ ነው የቀረው ማለት ነው። ኃላፊው ዶ/ር ሞንሴፍ ስሎይ ለሲኤንኤን እንደተናገሩት መሥሪያ ቤታቸው እያቀደ ያለው ይህ ክትባት ከሚመለከተው መሥሪያ ቤት ፍቃድ ባገኘ በ24 ሰዓታት ውስጥ ክትባቱን ወደ ጤና ጣቢያዎች ለማጓጓዝ ነው። ይህም ክትባቱን ወደ ዜጎች ለማድረስ አንዲትም ሰኮንድ እንዳትባክን ለማድረግ ነው። አሜሪካ በአሁን ሰዓት ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ፍጥነት በተህዋሲው ወረርሽኝ እየተጠቃች ነው። አሁን በተህዋሲው የተያዙት አሜሪካዊያን ቁጥር ከ12 ሚሊዮን ማለፉ ብቻ ሳይሆን በቀን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 200ሺ አካባቢ መጠጋቱ አገሪቱን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷታል። ወረርሽኙ አሜሪካ ከገባ ወዲህ 255ሺ ዜጎች ሕይታቸውን አጥተዋል። በዚህን ያህል ቁጥር ተህዋሲው ነፍስ ያጠፋበት ሌላ አገር የለም። ፋይዘር የተባለው እውቅ የመድኃት አምራች ኩባንያ ከጀርመኑ ባዯንቴክ ጋር በመሆን ላመረተውን መድኃኒት የእውቅና ጥያቄን ለሚመለከተው ክፍል ያቀረበው ባለፈው አርብ ነበር። ፋይዘርና አጋሩ ያመረቱት የክትባት ዓይነት የፈውስ ምጣኔው 95 ከመቶ ነው ተብሏል። አንድ ሰው ከኮቪድ ተህዋሲ ለመጠበቅ ይህን ክትባት በተለያየ ጊዜ ሁለት ጠብታ መውሰድ ይኖርበታል። ፋይዘርና አጋሩ እስከዚህ እስከያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ 50 ሚሊዮን የሚሆን ጠብታ ለማምረት ሁሉን ዓቀፍ ዝግጅቱን አጠናቋል። ይህም ማለት የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ሊገባደድ አንድ ወር ገደማ ብቻ ነው ስለቀረው በአንድ ወር 50 ሚሊዮን ጠብታ ያመርታል ማለት ነው። የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር የአማካሪዎች ምክር ቤት ልዩ ኮሚቴ በዲሴምበር 10 ይህን ክትባት ፍቃድ በመስጠት ጉዳይ ላይ ስብሰባ ይቀመጣል። ይህ ማለት ከ17 ቀናት በኋላ ነው የሚሆነው። ዶ/ር ስሎይ የሚሉት ታዲያ ይህ ኮሚቴ በተሰበሰበና መድኃኒቱ የምርት ይሁንታን ባገኘ በነገታው ክትባቶች ወደ ጤና ጣቢያዎች ይደርሳሉ። ሞዴርና የተሰኘው ሌላው የመድኃኒት አምራች በበኩሉ እንደ ፋይዘር ሁሉ የፈውስ ምጣኔው 95 ከመቶ የሆነ ሌላ ክትባት መሥራቱን ይፋ አድርጓል። ሞዴርና እንደ ፋይዘር ሁሉ በሚቀጥሉት ሳምንታት እውቅናና ፈቃድ እንዲሰጠው ማመልከቻ ያስገባል ተብሎ ይጠበቃል። ሀብታም አገራት ከነዚህ ሁለት ኩባንያዎች ጋር የመድኃኒት ምርት ስምምነት እያደረጉ ነው። ድሀ አገራት በዚህ ረገድ እጣ ፈንታቸው ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አሁንም እያነጋገረ ነው።
48442226
https://www.bbc.com/amharic/48442226
በምዕራብ ኦሮሚያ ስድስት ሰዎች መገደላቸው ተሰማ
ሰኞ አመሻሽ ላይ በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ዞን በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ተወረወረ በተባለ የእጅ ቦንብ ቢያንስ የስድስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ።
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የአካባቢ ነዋሪዎችና ባለስልጣናት ቦንብ መወርወሩን ለቢቢሲ አረጋግጠው ፍንዳታውን ተከትሎ ያገጠመ ጉዳትን በተመለከተ የተለያየ ሃሳብ ሰጥተዋል። የቄለም ዞን፣ የዞን ጽሕፈት ቤት ፐብሊሲቲ ኃላፊ አቶ ሐምዛ አብዱልቃድር አደጋው የደረሰው በዞናቸው አንጪሌ ወረዳ ሙጊ 02 ቀበሌ የሚባል ቦታ ላይ መሆኑን ተናግረዋል። ሰኞ አስር ሰዓት አካባቢ የኦነግ ሸኔ አባላት በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ የደፈጣ ጥቃት መፈፀማቸውን የሚናገሩት ኃላፊው የወረወሩት ቦንቡ ፈንድቶ በአካባቢው የሚገኙ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን አስረድተዋል። • "የግንቦት 20 ታሪካዊነት አጠያያቂ አይደለም" • 'መንፈስ ቅዱስ' ከቅጣት የጋረደው አሽከርካሪ • ቢሊየነሯ የሀብታቸውን ግማሽ ለበጎ አድራጎት ለመስጠት ወሰኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላቱ ከጋምቤላ ወደ ሙጊ ቀበሌ በእግርና በመኪና እየተጓዙ የነበሩ መሆናቸውን የጠቀሱት ኃላፊው በቦንቡ ጉዳት የደረሰባቸው ግን የደፈጣ ጥቃቱን ሊፈጽሙ በነበሩት የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ መሆኑን ተናግረዋል። በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ሰዎች ለቢቢሲ እንደገለፁት ሰኞ እለት ቦንብ መወርወሩን እንደሚያውቁ ነገር ግን የቦንብ ፍንዳታውን ተከትሎ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በወሰዱት የአፀፋ እርምጃ ሰባት ንፁሀን ተገለዋል ብለዋል።
news-55715931
https://www.bbc.com/amharic/news-55715931
የህንዷ መንደር በካማላ ሃሪስ ስኬት ደስታዋን እየገለፀች ነው
በደቡባዊ ህንድ፣ ናዱ ግዛት የምትገኘው ቱላሴንድራፑራም መንደር ከወትሮው ለየት ባለ ደስታና መንፈስ ተሞልታለች።
ለዚህም ደግሞ የመንደሯ ነዋሪዎች ተገቢ ምክንያት አላቸው። በዛሬው ዕለት በዓለ ሲመታቸውን የሚፈፅሙት የአሜሪካ ተመራጭ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ ቤተሰቦች ትውልድ መነሻ ስፍራ ናት። የመንደሯ ነዋሪዎች የየቀኑ ተግባራቸውን ገታ አድርገው በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያ ሴት ምክትል ፕሬዚዳንት የምትሆነውን ካማላ ሃሪስን ስኬት በማክበርም ላይ ናቸው። በመንደሯ ላይ ያሉ ዋና ዋና ጎዳናዎችም ምክትል ፕሬዚዳንቷን "እንኳን ደስ አለሽ" የሚሉ የደስታ መልዕክቶች ተሰቅለውባታል። ለዝግጅቱም ጣፋጮች፣ ከረሜላዎችና ብስኩቶች ተዘጋጅተዋል። ከዚህም በተጨማሪ የጆ ባይደንና የካማላ ሃሪስ ፎቶ ያለባቸው የቀን መቁጠሪያዎችም ለነዋሪዎች እየተሰጡ ነው። የሃሪስን ፎቶ የያዙ ነዋሪዎችም በአካባቢው ባለ የአምልኮ ቦታ ፀሎት እያደረሱላት ነው። አበባ፣ ጣፋጭና ከረሜላዎችንም ለካማላ ሃሪስ ቤተሰቦች አማልክት በማቅረብ ምስጋናና ችሮታቸውን እየገለፁ ነው። ርችቶች የተተኮሱ ሲሆን ቸኮሌትም ለምዕመናኑ ተከፋፍሏል። "ካማላ ሃሪስ መንደራችንን መጥታ ብትጎበኝ ደስ ይለናል። የደረሰችበት ስኬት የመንደራችን ነዋሪ ሴቶችን በትልቁ እንዲያልሙ አድርጓቸዋል" በማለት የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ ሱድሃካር ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሱድሃካር እንደሚሉት ጆ ባይደንና ካማላ ሃሪስ እንዲያሸንፉ ነዋሪዎች ሲፀልዩ ነበር። በንግድ ስራ የተመረቀው ሲቫራንጂኒ በበኩሉ የበዓለ ሲመታቸውን ዝግጅት በጉጉት እየጠበቀ እንደሆነ ተናግሯል። "ካማላ ሃሪስ ከመንደራችን በብዙ ሺዎች ርቀት ላይ የምትገኝ ብትሆንም ጥብቅ ቁርኝት አለን" ብሏል። ካማላ ሐሪስ የተወለደችው በካሊፎርኒያ ግዛት ኦክላንድ ከተማ ነው፡፡ እናቷ ሻየመላ ጎፓላን ሕንዳዊት ናት፡፡ አባቷ ዶናልድ ሐሪስ ደግሞ ጃማይካዊ ነበሩ፡፡ አባትና እናቷ ሁለቱም በስደት ነው ወደ አሜሪካ የመጡት፡፡ ሁለቱም እንግሊዝ በቅኝ ከገዛቻቸው አገራት ነው የመጡት፡፡ ሁለቱም እንግሊዝ ሄደው እንዲማሩ ተጠይቀው አሜሪካንን የመረጡ ናቸው፡፡ ቀጣይዋ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ ማን ናቸው?
news-55426023
https://www.bbc.com/amharic/news-55426023
ኮሮናቫይረስ፡ ፈረንሳይ ኮቪድ-19ን በመከላከል ግንባር ቀደም ለነበሩ ስደተኞች ዜግነት ልትሰጥ ነው
በፈረንሳይ በኮሮናቫይረስ መከላከል ላይ ተሰማርተው የነበሩ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ለአገሪቱ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከግምት ገብቶ ዜግነት እንዲያገኙ እየተደረገ ነው።
የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኮቪድ-19ን በመዋጋት ጥረት ውስጥ ግንባር ቀደም በመሆን የተሰለፉ ነዋሪዎችን በፍጥነት ለዜግነት እንዲያመለክቱ ጥሪ አቅርቧል። እስካሁን ድረስ ከ700 በላይ ስደተኞች ዜግነት ያገኙ አልያም ለማግኘት በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የደረሱ መሆናቸው ተገልጿል። የፈረንሳይ ዜግነት ከተሰጣቸው ስደተኞች መካከል የጤና ባለሙያዎች፣ የጽዳት ባለሙያዎች እና የንግድ ሱቅ ባለቤቶች ይገኙበታል። በመላው ዓለም ኮቪድ-19ን በመከላከል ረገድ ከፊት በመሆን ያገለገሉ ዜጎች ለኮሮናቫይረስ የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ሲሆን፣ በዚህም የተነሳ ዶክተሮችና ነርሶችን ጨምሮ በርካቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በዓለማችን ላይ በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከተጠቁ አስር አገራት መካከል ፈረንሳይ አንዷ ስትሆን ከ2.5 ሚሊየን በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ ሲያዙ 62 000 ደግሞ በዚሁ ተህዋሲ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። ለኮሮናቫይረስ መከላከል ግንባር ቀደም ለሆኑ ስደተኞች ዜግነት የመስጠት ወሬው የተሰማው በመስከረም ወር ላይ ነበር። 74 ስደተኞች የፈረንሳይ ፓስፖርት የተሰጣቸው ሲሆን 693 ሰዎች ደግሞ በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ናቸው ተብሏል። እስካሁን ድረስ 2,890 ስደተኞች ማመልከታቸውም ታውቋል። በአገር ውስጥ ሚኒስቴር የዜግነት ጉዳዮች ቢሮ " የጤና ባለሙያዎች፣ ሴት የጽዳት ሰራተኛ ፣ የሕጻናት ተንከባካቢዎች፣ የመደብር ሰራተኞች ለዜጎች ያላቸውን ታማኝነትና ቁርጠኝነት አስመስክረዋል። አሁን ደግሞ ብድር መመለስ ተራው የፈረንሳይ ነው" ብሏል። ከዚህ ቀደም ለዜግነት ማመልከት የሚችሉት ስደተኞች በፈረንሳይ ለአምስት ዓመት በቋሚነት የኖሩ፣ ቋሚ ገቢ ያላቸው እና ከፈረንሳይ ሕዝብ ጋረ ተስማምተውና ተቻችለው መኖርን ያስመሰከሩ ብቻ ነበሩ። ነገር ግን በኮሮናቫይረስ መከላከል ውስጥ ከፊት ከነበሩ ስደተኞች ከሆኑ ሁለት ዓመት መኖርና " መልካም ሥራቸው የተመሰከረላቸው" መሆናቸው ብቻ በቂ ነው ተብሏል። በ2017 የፈረንሳይ ስደተኞች ቁጥር 6.4 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን ዜግነት የማግኘት ሂደቱ ግን እጅጉን ዘገምተኛ ነበር ተብሏል። ዜግነት የተሰጣቸው ስደተኞች ቁጥርም ሲታይ እኤአ በ2018፣ በ2019 የተሰጣቸው ስደተኞች በ10 በመቶ ቀንሰዋል። ፈረንሳይ ማሊያዊ ስደተኛ አንድ ጨቅላን ከፎቅ እንዳይወድቅ በመታደጉ መልካም ስራውን በማድነቅ ዜግነት የሰጠችው በ2018 ነበር።
50279610
https://www.bbc.com/amharic/50279610
'የአሜሪካዊ ፉትቦል' አሰልጣኝ ቡድናቸው በሰፊ ውጤት በማሸነፉ ተቀጡ
አሜሪካዊያን 'ፉትቦል' እያሉ የሚጠሩት ስፖርት አሰልጣኝ የሆኑት ግለሰብ ቡድናቸው ተቀናቃኙን 61 ለ 13 በማሸነፉ ለጊዜው ከሥራ ታግደዋል።
የአሜሪካዋ ሎንግ አይላንድ ከተማ ትምህርት ቤት ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት ሮብ ሼቨር በከፍተኛ ውጤት በማሸነፍ የከተማይቱን ሕግ ጥሰዋል ተብለው ነው የታገዱት። ሕጉ አሸናፊ ቡድን ከ40 በላይ ነጥብ ካስቆጠረ የአሸናፊው ቡድን አሠልጣኝ ኮሚቴ ፊት ቀርበው ማብራሪያ እንዲሰጡ ያዛል። ይህ ሕጉ ከወጣ ሦስት ዓመት ሆኖታል። ዓላማው ደግሞ ስፖርታዊ ጨዋነትን ማስረፅ ነው። አሰልጣኝ ሼቨር በዚህ ሕግ የተቀጡ የመጀመሪያው አሰልጣኝ ናቸው። የተሸናፊው ቡድን አሰልጣኝ እኔ በውጤቱም ሆነ በጨዋታው ምንም ቅሬታ አልተሰማኝም፤ አሰልጣኙም ቢሆን ምንም ስህተት አልፈፀሙም ሲሉ የሙያ አጋራቸውን ተከላክለዋል። አጣሪ ኮሚቴው ፊት ቀርበው ለምን ቡድንዎ በሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ ዝም ብለው ተመለከቱ? ቢያንስ ሁለተኛ ቡድንዎን አያጫውቱም ነበር ወይ? ተብለው የተጠየቁት አሰልጣኝ ሼቨር አጥጋቢ ምላሽ አልሰጡም ተብለዋል። አሰልጣኙ ቅጣቱ ተገቢ አይደለም ብለው ቢከራከሩም ኮሚቴው አንድ ጨዋታ ሜዳ እንዳይገቡ ሲል በይኖባቸዋል። ቅጣቱ ብዘዎችን ቢያስገርምም ወጣቶች በከፋ ውጤት ቅስማቸው እንዳይሰበር ስለሚያደርግ ተገቢ ነው ብለው የተከራከሩም አልጠፉም። የአንድ ጨዋታ ቅጣት የተላለፈባቸው አሰልጣኝ ሼቨር የቡድናቸውን ቀጣይ ጨዋታ በአካል ተገኝተው መታደም እንዳይችሉ ታግደዋል።
news-49792730
https://www.bbc.com/amharic/news-49792730
ትራምፕ የሕንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር አሞካሹ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ በቴክሳስ ግዛት ሂውሰትን ከተማ በተዘጋጀ መደረክ ላይ ሲሞጋገሱ አምሽተዋል።
በዝግጅቱ ላይ ከ50ሺህ በላይ ታዳሚዎች ተሳታፊ ነበሩ "ዛሬ እዚህ በቴክስሳ ከአሜሪካ ቁልፍ አጋር፣ ታታሪ እና ታማኝ ወደጅ ከሆኑት ከጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር በመገኘቴ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል" በማለት ለ50ሺህ ታዳሚዎች የተናገሩት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው። • ትራምፕ ዲቪን ማስቀረት ይችላሉ? • ትራምፕ 'ሐውልት' ቆመላቸው ጠቅላይ ሚንስትር ሞዲ በበኩላቸው፤ ፕሬዝደንት ትራምፕን በዋኃይት ሃውስ የሚገኝ "እውነተኛ ጓደኛ" ብለው ከገለጹ በኋላ፤ "ከዋና ሥራ አስፈጻሚ ወደ የአሜሪካ ጦር ጠቅላይ አዛዥ፣ ከቦርድ ስብሰባ አዳራሽ ወደ ዋኃይት ሃውስ፣ . . . ትራምፕ በየሄዱበት አሻራቸውን ጥለው የሚያልፉ መሪ" ሲሉ አሞካሽተዋቸዋል። ትራምፕ "እጅግ አስደናቂ እና ታሪካዊ ክስተት'' ሲሉ በገለጹት መድረክ ከ50ሺህ በላይ ሰዎች ተሳታፊ ሆነውበታል። ለ 90 ደቂቃ የቆየው ዝግጅት በአሜሪካ ታሪከ ለውጪ ሃገር መሪ ከተሰናዱ ደማቅ አቀባበሎች መካከል አንዱ ነው ተብሎለታል። ዶናልድ ትራምፕ እና ናሬንድራ ሞዲ እጅ ለእጅ ተያይዘው ታዳሚውን ሲሰናበቱ። ይህ መድረክ በ 2020 ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ትራምፕ ትውልደ ሕንድ የሆኑ አሜሪካውያንን ድጋፍ ለማገኘት እንደሚረዳቸው ታምኗል። ለጠቅላይ ሚንስትር ሞዲ ከትራምፕ የተቸራቸው ውዳሴ በሕንድ እየቀረበባቸው ያለውን የሰላ ትችት ያለዝበዋል ተብሏል። • አሜሪካ፡ የመድኃኒት ዋጋ ሰማይ የደረሰባት ሃገር ትራምፕ በስታዲየሙ ተሰብሰበው ለነበሩት ትውልደ ሕንድ አሜሪካውያን ታዳሚዎች "አሜሪካዊ ሆናችሁ ከእኛ ጋር ስለሆናችሁ ኩራት ይሰማናል" ብለዋል። የሕንዱ ጠቅላይ ሚንሰትር አንድ ሳምንት በሚቆየው የአሜሪካ ጉብኝታቸው ከአሜሪካ ጋር በንግድ ላይ ያተኮረ ውይይት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ሲሆን በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ስብሰባ ላይም ተሳታፊ ይሆናሉ።